ምስጢረ-ሥላሴ

843 Views

“ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ባሳተሙት መጽሀፍ ገፅ 37 ላይ የሚከተለው ቃል ሰፍሮ ይገኛል። እንደ እሳቸው ገለፃ መሠረት ምስጢር ማለት ድብቅ ወይንም ሽሽግ ማለት ሲሆን በሀይማኖታዊ እሳቤው ደግሞ የሰው ልጅ አእምሮ አስቦና መርምሮ የማይደርስበት ማለት ነው።

photo_2020-09-04_04-43-07

እዚህ ውስጥ “ምስጢረ ሥላሴ” እንደሚካተተም ገልፀዋል። እንደ አንድ የንፅፅር ሰው የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማንሳት አስፈላጊ ነው ብየ አምናለሁ፦

፩- ይህ መሠረታዊ የክርስትና እሳቤና የእምነቱ መሠረት እንዴት በግልፅ ተቀምጦ ሳይብራራና በደፈናው “አይገባችሁም” የሚባል ሚስጥር ሊሆን ቻለ?

፪- ይህንን እሳቸው እንዳሉት ለአእምሮ መረዳት ከባድ የሆነ አስተምህሮና ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚገለጥ ሚስጥር ሌላው ያልገባው ማህበረሰብ ባያምንበትና ባይቀበለው ጥፋቱ የማነው? የተገለጸው ለጥቂት ሰው ከሆነና ያልተገለፀለት ካልተቀበለው ችግሩ የማን ነው?

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)