የቅድመ ውሳኔን (ቀዷ ወል-ቀደር) ጽንሰ ሃሳብ በተመለከተ ክፍል -5

1,185 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

አቡ ሀይደር

ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡

” وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ ” سورة التكوير 29
“የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም” (ሱረቱ-ተክዊር 81፡29)፡፡

ባለፈው ክፍል አራት ላይ ‹‹አላህ የሻው እንጂ ምንም አይከሰትም›› የሚል ርእስ አንስተን ነበር፡፡ በውስጡም፡-

ሀ/ ሰው ነጻ ፈቃድ (መሻት) ያለው ፍጡር መሆኑና፡ ሆኖም ይህ ነጻ ፈቃዱ እውን የሚሆነው፡ የፈለገውን ነገር ሊያደርግበት የሚችለው አላህ ሲፈቅድለትና ይሁን ሲለው ብቻ ነው፡፡ ያለ አላህ ፈቃድ እራሳችንን ችለን የምናደርገው ምንም ነገር እንደሌለና፡ አላህም ፈቃዳችንን በፈቃዱ ስር በማድረግ የሚቆጣጠረን ጌታ መሆኑን አይተናል፡፡

ለ/ አላህ ብቻውን ፈጣሪ የሆነ አምላክ ነው፡፡ ደግሞም በዓለሙ ላይ ብቻውን የነገሰ ንጉስ ነው፡፡ ሲፈጥረን በፈቃዱና በፍላጎቱ ብቻ እንደሆነው ሁሉ፡ ንጉስ በመሆንም ሲገዛን እሱ እንደፈለገው ነው እንጂ፡ እኛ እንደሻነው አይደለም፡፡ ስለዚህም ለባሮቹ የሰጣቸው ነጻ ፈቃድ የሱ ይሁንታ ካልታከለበት ወደ ተግባር በፍጹም ሊቀየር አይችልም ማለት ነው፡፡

ሐ/ ሰው ነጻ ፈቃድ አለው ማለት፡ ያለምንም ተቆጣጣሪ የፈለገውን ነገር ይተገብራል፡ ፈላጭ ቆራጭ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ያ ቢሆን ኖሮ የሰማይና የምድር ስርአት በተበላሸ ነበር፡፡ ነገር ግን ጥበበኛው አላህ ሰውን ከፈጠረው በኋላ፡ ነጻ ፈቃድ የሚባልን ነገር ሰጥቶ በልቅ አልተወውም፡፡ ይቆጣጠረዋል፡፡ እሱ አላህ የፈለገውን ነገር እንዲሳካለት ይፈቅዳል፡፡ ያልፈለገለትን ደግሞ እውን እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ጥበቡ የሱ ብቻ ነውና የሚል ነው፡፡ ዛሬ የምናየው የዚህን ሀሳብ ቀጣይ ክፍል ሆኖ፡ ቀደምት ነቢያትና (ዐለይሂሙ-ሰላም) አማኞችም በጉዳዩ ላይ ምን አይነት እምነት እንደነበራቸው የተወሰኑትን ለናሙና በመጥቀስ ይሆናል ኢንሻአላህ፡፡ መልካም ንባብ!

1. ኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም)፡-

” قَالُوا يَا نُوحُ قَدْ جَادَلْتَنَا فَأَكْثَرْتَ جِدَالَنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِنْ كُنْتَ مِنَ الصَّادِقِينَ * قَالَ إِنَّمَا يَأْتِيكُمْ بِهِ اللَّهُ إِنْ شَاءَ وَمَا أَنْتُمْ بِمُعْجِزِينَ * وَلَا يَنْفَعُكُمْ نُصْحِي إِنْ أَرَدْتُ أَنْ أَنْصَحَ لَكُمْ إِنْ كَانَ اللَّهُ يُرِيدُ أَنْ يُغْوِيَكُمْ هُوَ رَبُّكُمْ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ” سورة هود 34-32

“ኑሕ ሆይ በእርግጥ ተከራከርከን፤ እኛን መከራከርህንም አበዛኸው፣ ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው አሉ። ፦ እርሱን የሚያመጣባችሁ የሻ እንደሆነ አላህ ብቻ ነው፤ እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም አላቸው። ለናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ሆነ ምክሬ አይጠቅማችሁም፤ እርሱ ጌታችሁ ነው፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፤ (አላቸው)።” (ሱረቱ ሁድ 11፡32-34)፡፡

ነቢዩላህ ኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም) ህዝቦቹን ወደ አላህ መንገድ በመጣራት፡ አላህን ብቻ እንዲገዙና ከጣኦት አምልኮ እራሳቸውን እንዲያገልሉ አስተማረ፡፡ ከህዝቦቹም በኩል፡- ኑሕ ሆይ! በዚህ ነገር በጣም ተከራከርከን፡፡ እኛ እንደሆነ አናምንልህምና፡ ካላመናችሁ ይመጣባችኋል እያልክ የምታስፈራራንን ቅጣት አምጣብን አሉት፡፡ እሱም፡- ነገሩ ሁሉ ያለው በአላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ቅጣቱንም ከፈለገ የሚያመጣባችሁ እሱ ነው፡፡ እኔ የቱንም ያህል እናንተን መምከር ብፈልግም፡ *አላህ ሊያጠማችሁ እስከፈለገ* ድረስ ምክሬ አይጠቅማችሁም አላቸው፡፡ የአላህ ፈቃድ የበላይ ነው፡፡ ፍላጎቱም ተፈጻሚ ነው፡፡ (ተፍሲር ኢብኑ ከሢር፣ ተፍሲር አስ-ሰዕዲይ ተይሲር ከሪሙ-ራሕማን)፡፡ በዚህ ንግግር ውስጥ ሁለት መልክቶች አልሉ፡-

ሀ/ ‹‹እርሱን የሚያመጣባችሁ የሻ እንደሆነ አላህ ብቻ ነው›› በማለት፡ ፈቃድን ወደ አላህ ማስጠጋቱ፡ ነገራት በጠቅላላ የሚፈጸሙት በአላህ ይሁንታ መሆኑን ማመኑን ያሳየናል፡፡ ኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም) ስለጠየቀ ሳይሆን አላህ ከፈለገ ብቻ ነው ቅጣቱም የሚመጣባቸው ማለት ነው፡፡

ለ/ ‹‹ለናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ሆነ ምክሬ አይጠቅማችሁም›› ማለቱም ተመሳሳይ ሀሳብን ይሰጠናል፡፡ ጌታ አላህ የሰዎችን ልብና መሻት ያውቃል፡፡ እንደ ሰው ከላይ ያለን ገጽታን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፡ የልብንም ድብቅ ሀሳብ የሚያይና የሚያውቅ አምላክ ነው (አል-ሙልክ 67፡13-14)፡፡ በመሆኑም እነዚህ ሰዎች የነቢያቸውን ኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም) ሃይማኖታዊ ጥሪ አሻፈረኝ በማለት እንደማይቀበሉ አስቀድሞውኑ የሚያውቅ አምላክ በመሆኑ፡ አላህ ጥንቱኑ እነሱን ሊያጠማቸው ከፈለገ፡ የኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም) ምክር ሊጠቅማቸው አይችልም ማለት ነው፡፡

እኛም መረዳት ያለብን፡ ህዝቦቹ የኑሕን ዳዕዋ ለመቀበል ባለመፈለጋቸው ምክንያት አላህ አጠመማቸው የሚለውን ሀሳብ እንጂ፡ ነገሩን ገልብጠነው፡- አላህ ስላጠመማቸው የኑሕን ዳዕዋ መቀበል አልቻሉም አንልም፡፡ የጌታ አላህ እነሱን ማጥመም መሻቱ እምቢተኝነታቸውን ቀድሞውኑ በማወቁ እንጂ፡ በዘፈቀደ የሆነ ነገር አይደለም፡፡ ደግሞም ባሮቹን ህግን በነቢያት በኩል ልኮላቸው፡ እነሱም አሻፈረኝ እስኪሉ ድረስ ማንንም ለጥመትና ለክህደት አይዳርግም፡፡ በሌላ ሱራ ላይ እንዲህ ይላል ጌታችን፡-

” وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِلَّ قَوْمًا بَعْدَ إِذْ هَدَاهُمْ حَتَّى يُبَيِّنَ لَهُمْ مَا يَتَّقُونَ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ ” سورة التوبة 115
“አላህም ሕዝቦችን ከአቀናቸው በኋላ፣ የሚጠነቀቁትን (ሥራ) ለርሱ እስከሚገልጽላቸዉ፣ (እስከሚተዉትም) ድረስ ጥፋተኛ የሚያደርግ አይደለም፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና።” (ሱረቱ-ተውባህ 9፡115)፡፡

የኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም) ህዝቦችንም አላህ ማጥመምን መሻቱ፡ ይህን የእንቢተኝነት ባህሪቸውን ቀድሞ በማወቁ የቀጣቸው ቅጣቱ እንጂ፡ ለነሱ መካድ እንደ ሰበብ የሚታይ አይደለም፡፡ አላህ ባያጠመን ኖሮ እምቢተኛ አንሆንም ነበር! ማለት አይችሉም፡፡ በተቃራኒው የሚባሉት፡- እምቢተኛ ባትሆኑ ኖሮ አላህ አያጠማችሁም ነበር! ቀድሞውኑ ይህን እምቢተኝነታችሁን ስላወቀ ነው ለጥመት የዳረጋችሁ እንጂ! ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

2/ ኢስማዒል (ዐለይሂ-ሰላም)፡-

” فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَى فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانْظُرْ مَاذَا تَرَى قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ سَتَجِدُنِي إِنْ شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ ” سورة الصافات 102

“ከርሱም ጋር ለስራ በደረሰ ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡

َهُوَ يُحَاوِرُهُ أَكَفَرْتَ بِالَّذِي خَلَقَكَ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ مِنْ نُطْفَةٍ ثُمَّ سَوَّاكَ رَجُلًا * لَكِنَّا هُوَ اللَّهُ رَبِّي وَلَا أُشْرِكُ بِرَبِّي أَحَدًا * وَلَوْلَا إِذْ دَخَلْتَ جَنَّتَكَ قُلْتَ مَا شَاءَ اللَّهُ لَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ إِنْ تَرَنِ أَنَا أَقَلَّ مِنْكَ مَالًا وَوَلَدًا * فَعَسَى رَبِّي أَنْ يُؤْتِيَنِ خَيْرًا مِنْ جَنَّتِكَ وَيُرْسِلَ عَلَيْهَا حُسْبَانًا مِنَ السَّمَاءِ فَتُصْبِحَ صَعِيدًا زَلَقًا” سورة الكهف 40-35

“እርሱም ነፍሱን በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ፤ ይህች ዘለዓለም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም፣ አለ። ሰዓቲቱንም ቋሚ (ኋኝ) ናት ብዬ አልጠረጥርም፤ (እንደምትለው) ወደ ጌታዬም ብመለስ ከርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ፥ (አለው)።ጓደኛው፥ (አማኙ)፣ እርሱ ለርሱ የሚመላለሰው ሲሆን ፦ በዚያ ከዐፈር ከዚያም ከፍቶት ጠብታ በፈጠረህ፣ ከዚያም ሰው ባደረገህ፥ (አምላክ) ካድህን? አለው። እኔ ግን እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፤ (እላለሁ)፤ በጌታዬም አንድንም አላጋራም። አትክልትህንም በገባህ ጊዜ፣ አላህ የሻው ይሆናል፤ በአላህ ቢሆን እንጂ ኀይል የለም፤ አትልም ኖሯልን? እኔን በገንዘብም በልጅም ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝ፥ ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በርሷም (በአትክልትህ) ላይ ከሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳላጥ ምልጥ ምድር ልትሆን ይቻላል።” (ሱረቱል ከህፍ 18፡35-40)፡፡

ከሀዲው ጓደኛ ባለው ሰፊ የአትክልታማ ስፍራና በልጆች ብዛት በመኩራራት፡ ወደ አትክልታማ ስፍራው ይገባና ‹‹ይህቺ ዘለዓለም ትጠፋለች ብዬ አላስብም፡፡ እንዲሁም ቂያማ ይመጣል የሚልም እምነት የለኝም! ብሎ ሲናገር፡ አማኙ ጓደኛው ደግሞ በአንጻሩ፡- ከአፈር እንዲሁም ከፍትወት ጠብታ ፈጥሮ ሰው ባደረገህ ጌታ ትክዳለህን? እኔ ግን ጌታዬ አላህ ነው! በጌታዬም አላጋራም ይለዋል፡፡ በመቀጥልም፡- ወደ አትክልት ስፍራህ በገባህ ጊዜ *ነገሮች ሁሉ የሚሆኑት አላህ የሻ እንደሆነ ነው* አትልም እንዴ? *ኃይልም ቢሆን በአላህ እንጂ የለም ብለህ አትናገርምን?* በማለት ይወቅሰዋል፡፡ ምክንያቱም አትክልታማው ስፍራ ከፈለገ የሚያቆያት፡ ካልሆነም የሚያጠፋት አላህ ብቻ ነውና፡፡ ይህ የአንተ ስራና ጥበብ አይደለም በማለት ገለጠለት፡፡ ‹‹አላህ የሻው ይሆናል፣ እሱ ያልሻው አይሆንም›› የሚለው እምነት፡ የቀደምት ነቢያትም የአማኞችም ትክክለኛ እሳቤ ነው ማለት ነው፡፡

እነዚህ ለናሙና የቀረቡ ስድስት ምሣሌዎች ናቸው፡፡ አጠቃላይ መልእክታቸው፡- ጌታ አላህ የራሱ የሆነ ፈቃድና ፍላጎት ያለው አምላክ መሆኑን፣ እሱ የፈለገውና የሻው ነገር በጠቅላላ ከመሆን ሊያስቀረው የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ፣ ሰውም የተሰጠውን ነጻ ፈቃድና ውስን ኃይል ተጠቅሞ አንድን ነገር ለማድረግ ቢፈልግ፡ አላህ ካልሻለትና ካልፈቀደለት በስተቀር በራሱ ፍላጎት ብቻ የፈለገውን ሁሉ ማድረግ እንደማይችል፣ የአላህ ፈቃድና ፍላጎት የሁሉንም ፈቃድና ፍላጎት ያሸነፈና የገዛ መሆኑን በአንድ ድምጽ ያሰማሉ፡፡
ይቀጥላል ኢንሻአላህ፡፡

ወአኺሩ ዳዕዋና ዐኒል-ሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን፡፡