ጳዉሎስ እና እየሱስ -1

በማቴዎስ ወንጌል 10፡23 እንደተጠቀሰዉ እየሱስ ሃዋሪቶቹን ከእስራኤል ከተማ ዉስጥ ሆነዉ ከአንድ ቦታ ከተባረሩ ወደ ሌላ ከተማ እየሄዱ ወንጌልን እንዲሰብኩ እንደዉም እሱ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች እንደማይዘልቁት ወይንም እንደማይጨርሱት ጭምር ነግሮዋቸዋል። በተጨማሪም ከእስራኤል ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም ብሎም ተናግሯል ወደ አህዛብም መንገድ ወደ ሳምራዉያንም ከተማ እንዳይገቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥጠቷቸዋል ።ለዚህም ስራቸዉ ዉጤት በአስራሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንደሚፈርዱ በማቴ 19፡28 ላይ ተናግሯል (28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ)

ማቴ10፡23 በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።

ማቴ 15፡ 24 እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
5 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤
ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።

ጳዉሎስ ግን በራሱ ዉሳኔ በሐዋሪያት ስራ 18፡5-6 መሰረት ( ነገር ግን በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፥ ልብሱን እያራገፈ፦ ደማችሁ በራሳችሁ ነው፤ እኔ ንጹሕ ነኝ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ #አሕዛብ #እሄዳለሁ አላቸው።)

ጥያቄ፡-ታዲያ ማን ነዉ ትክክል?

© አቡ ዩስራ

ሼር ያድርጉ
  • 38
    Shares