ጋብቻና ክርስትና

እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ሲናገር “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዋት” ይላል። ይህ ትዕዛዝ የሰው ልጅን ከማብዛት አላማ ጋር የተሳሰረ ነው። በቃሉ ውስጥ የጋብቻን አስፈላጊነት እናስተውላለን። ሰው ምድርን የሚሞላት በአምላክ ቡራኬ ውስጥ ባለ ስርአት ውስጥ ነውና ጋብቻ መልካም ነገር ነው። ጻውሎስ በመልዕክቱ ደግሞ እንዲህ ይላል፦

” ስለ ጻፋችሁልኝስ ነገር፥ ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው።”
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7: 1)

ጋብቻ በክርስትናው አለም ስሜት ካላስቸገረ በስተቀር ብዙም የሚበረታታ አይደለም።

ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው-፤ ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:8-9

በጋብቻ ውስጥ ያሉ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ መስተጋብሮች ለጻውሎስ ምንም ናቸው። ጋብቻ ማለት ለጳውሎስ ተራ ፍትወት ማርኪያ ብቻ ነው። ይህ የጋብቻን ትርጉም ያልተረዳ ሰው የሚሰነዝረው ዝቅ ያለ ሀሳብ ነው። ቤተሰብ የሚመሰረተው በጋብቻ ነው፤ ትውልድ መሠረቱን የሚይዘው ጋብቻ ውስጥ ነው። ጋብቻ ከወሲብ በላይ ነው፤ ጳውሎስ ግን ይህን አልተረዳም። ከዚህ በተጨማሪ ሌላ መሠረታዊ ጉዳይም ዘንግቷል። እግዚአብሄር ለሰው ልጅ “ምድርን ሙሉዋት” ብሎ ሲያዝ በረከሰው ዝሙት ሳይሆን በተቀደሰው ጋብቻ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ታዲያ ጳውሎስ አለመጋባትን የተሻለ ነው ሲል ከእግዚአብሄር ትዕዛዝ ጋር መላተሙን ረስቶት ይሆን? ምድር ካለ ጋብቻ እንዴትስ ትሞላለች? የቸገረ ነገር

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)ሼር ያድርጉ
  • 50
    Shares