ይህች ጣትና የስላሴ ምሳሌ

የጣት ምልክቷን አስመልክቶ አንዳንድ ሰዎች ስላሴን ይገልጻል ከሚለው ምሳሌ በመነሳት በሶሻል ሚዲያ ሲቀባበሏት አይተን ታዝበናል አንዳንዶች አዝነናል ፕሮፋይል አድርገው አይተንም ስቀናል። እስኪ ጥቂት ነጥቦችን ከዚህ በታች እየዘረዘርን ሲያሻቸው እንቁላል ሲያሻቸው ጣት የሚያደርጉት “ስላሴ” ጋር እናመሳክረዋለን።

1- ስላሴ እንደ ክርስትና እሳቤ አምላክ ነው። ታዲያ አምላክን የሚያክል አካል በተራ ፍጡራን እየመሰሉ ማስተማር ክብሩን ማላሸቅ አይሆንም? አምላክስ ምን ምሳሌ አለውና? መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

“፤ በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ? ” 

(ትንቢተ ኢሳይያስ 46: 5)

2- የጣቱ ምልክት እነሱ እንደሚሉን ሶስት አንጓዎች ስላሉት ስላሴን ይጠቁማል ነው 🙂 አንጓው ሶስት ስለሆነ ስላሴን ከጠቆሙ ጥፍሩስ የትኛውን መለኮት ይጠቁማል? የአንጓዎች ውፍረትና ቅጥነትስ የስላሴን የስልጣን ደረጃዎች ይጠቁማል? መሠል አስቂኝ ትርክቶችን እያነሳን ሀሳቡን ውድቅ ማድረግ ቀላል ነው።

 3- የስላሴ ጽንሰ ሀሳብስ እስከመቼ ብቻውን ማስረዳት ቸግሮን በምሳሌ ሲደገፍ ይኖራል? የክርስትና ዋነኛ የእምነት ክፍል የሆነው ይህ አርዕስት ሁሌም በአማኙ መካከል ውዝግብን መፍጠሩስ ምን ይጠቁማል? ፍርዱን ለህሊና

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

ሼር ያድርጉ