የደቀመዛሙርት ሽሽት

1,036 Views

ከእየሱስ ጋር የነበሩት ደቀመዛሙርት ሊሰቀል ገደማ አንድ እንኳን ሳይቀር ሁሉም ሸሽተውት እንደነበር ወንጌላት ይነግሩናል።

“ሁሉም ትተውት ሸሹ።” ማርቆስ 14፥50

እስኪ አስቡት እነዚህ ተማሪዎቹ ኢየሱስ እንደሚሰቀል እያወቁ ነበር ጥለውት የሚሸሹት? ይህ ጠንካራ እምነት አላቸው ለሚባሉት ደቀመዛሙርት የሚመጥን ትርክት ነው? እንዲህ በጥቃት ወቅት መምህራቸውን እንኳ መከላከል የሚይችሉ “ፈሪ” ነበሩ ብላችሁ ታስባላችሁ? የመሸሻቸው መንስኤ ወጣም ወረደ ከሚከተሉት ሁለት ነጥቦች አያልፍም፦

፩- የሚሰቀለው እርሱ አለመሆኑን ተረድተው ቀድመው ሂደው ነበር። ይህም የሚሰቀለው እርሱ ካልሆነ መስዋዕትነት የሚከፍሉበት ምንም ምክንያት አልነበረምና ጥለው ሒደዋል።

፪- አይ እርሱ እንደሚሰቀል እያወቁ ነበር የሸሹት ካልን ግን ደቀመዛሙርት “ፈሪዎች” እንደነበሩ እየመሰከርን ነው ማለት ነው። ከዛም በዘለለ ግን ኢየሱስ የቅርብ ሰዎቹ ሳይቀር ለእምነት የሚደረግን መስዋእትነት የሚያውቁበት ጠንካራ ትምህርት ያልነበረው መምህር እንደነበር በተዘዋዋሪ እየገለፅን ማለት ነው። ያ ማለት ደቀመዛሙርቱም “ፈሪዎች” ነበሩ፤ ኢየሱስም መንፈሳዊ ስብእናቸውን የሚያደረጅ ትምህርት ሳይሆን ልፍስፍስ የሚያደርግ ትምህርት ነበር እድሜ ልካቸውን ያስተማራቸው እያልን ነው።

ከሁለቱ የተሻለውን እናንተ ታቃላችሁ …!

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)