የእግዚአብሔር አምሳያ ማነው?

ሼር ያድርጉ
563 Views
(የሕያ ኢብኑ ኑህ) እንደመጽሀፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት የሰው ልጅ የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ነው። እኛ ሰዎች የእግዚአብሔር አምሳያ ነን ከተባለ ታዲያ የትኛው ፆታ ነው ይህንን መመሳሰሎሽ የገጠመው የሚለው ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ ነው። እንደሚታወቀው ሰው የሚባለውና መጽሀፍ ቅዱስም አያይዞ የጠቀሰው ፆታ ወንድና ሴት ነውና እግዚአብሔር ሰው ሲል የትኛው እሱን እንደሚመስል እንድንጠይቅ ያስገድደናል። አንቀጹ እንደሚከተለው ይነበባል፦ “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።”
(ኦሪት ዘፍጥረት 1:27) ይህንን አንቀጽ መሠረት በማድረግ የሚከተሉት ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እንወዳለን። 1- እግዚአብሄር በመልኩ የፈጠረው ወንዱን ወይንስ ሴቷን? 2- ወንዱን ነው ከተባለ – ሁለት ተያያዥ ጥያቄ ይፈጥራል፦ 1.1- እግዚአብሄር ፆታው ወንድ ነው ማለት ነው? 1.2- ሴት ሰው አይደለችም ማለት ነው? ምክንያቱም አንቀጹ ተፈጠረ የሚለው ወንድ ሳይሆን “ሰው” ነው። አንዳንድ ሰው የእንግሊዝኛውን “Man” የሚል ቃል “ለወንድ ብቻ ነው” መከራከሪያ አድርጎ ቢያቀርብም ይህም ሰው ከ1.1 ጥያቄ ግን መዳን አይችልም። ከዛ በዘለለ ይህንን አመለካከት አብዛኛው ወንጌላዊ አይቀበልም። Man የሚለው ቃል በጥንት ጊዜ ሁለቱንም ፆታን ለመጠቀም አገልግሎት ላይ እንደሚውል ይሞግታሉ (ይህም ሌላ ብዙ ጥያቄዎች ያሉት ቢሆንም) “Man” የሚለው በተናጠል አዳም ነው ከተባለ ግን ይህ መልዕክት ሴቷን አይመለከትም ማለት ነው፡፡ Man የሚለው ቃል ሁለቱንም ይገልፃል ከተባለ ግን ታዲያ እግዚአብሔር “መሠለ” የተባለ የቱን ሰው ነው? ወይንስ በአንዴ ሁለቱንም ፆታ ነው የመሠለው? የሚል ጥያቄ ምላሽ ይፈልጋል? “ሴት ልጅ ሰው ናት ወይንስ አይደለችም?” የሚለው አመለካከት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በክርስቲያን አማኞች ዘንድ ሲያጨቃጭቅ የኖረ ጉዳይ ሲሆን በፈረንጆቹ 1595 በጉባኤ ደረጃ ትልቅ መወያያ ሳይቀር ሁኖ ነበር። ርዕሱም “ሴት ሰው ናት ወይንስ አይደለችም?” ይሰኛል።
“Are women human?” Manfred P. Fleischer
The Sixteenth Century Journal
Vol. 12, No. 2 (Summer, 1981), pp. 107-120 ➌- እግዚአብሔር መሠለ የተባለው ሴቷን ነው ከተባለ እግዚአብሄር ፆታው የሴት ነው ማለት ነው? ❐ እነዚህ አንቀጾች በትኩረት ከተፈተሹ ተያያዥ ብዙ ጥያቄዎችን እንድናነሳ የሚገፋፉን ናቸው። ክርስቲያን ወገኖቻችን መሠል አንቀፆችን ከሰበካ መገልገያነታቸው ውጭ በትኩረት ያጠኗቸዋል ወይ? የሚለው ግን ለነሱ የሚተው ጥያቄ ነው።
ተጨማሪ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን ለመከታተል ❐ በዩቲዩብ – http://bit.ly/2ZPzYTI ❐ በቴሌግራም – t.me/yahya5 ❐ በፌስቡክ- facebook.com/yahyanuhe/ ❐ በድህረ ገጽ- www.ethio-islamic.org