የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” 6 በኡስታዝ አቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
499 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
4. መስፈርቶቹ፡-
ባለፉት ቀናት የ”ላ-ኢላሀ ኢለሏህ”ን መስፈርቶች ጀምረን አራቱን ተመልክተናቸው ነበር፡፡ እነሱም፡- ስለ “ላ-ኢላሀ ኢለሏህ” ትርጉምና መልእክት ማወቅ፣ ባወቅነውም ነገር እርግጠኛ መሆን፣ ከዛም ከልብ ወዶ መቀበል እና ስንቀበልም አስመሳይ ሳንሆን ፍጹም እውነተኛ መሆን የሚሉት ነበሩ፡፡ ቀሪ ነጥቦቹን ደግሞ ዛሬ እንመለከታቸዋለን ኢንሻአላህ፡፡ መልካም ቆይታ፡፡

ሠ. ‹‹በኢኽላስ ሳያጋሩ መሆኑ››፡-
ሌላው ዋናውና አንገብጋቢው መስፈርት ነው፡፡ የ”ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ”ን እምነት ያወቀና የተቀበለ ሙስሊም ኢኽላስ ሊኖረው ይገባል፡፡ ኢኽላስ ማለት በአንደኛው ትርጉሙ፡- አምልኮን ለአላህ ብቻ በማድረግ በርሱ ላይ ምንንም ማንንም አለማጋራት ማለት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም በ”ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” እምነቱ ላይ ማንንም ሊያጋራ አይገባም፡፡ አላህን በብቸኝነት ለማምለክ ቃል እስከ-ገባ ድረስ፡ በጌታው አምልኮ ላይ ማንንም ጣልቃ በመክተት ማጋራት የለበትም፡፡ እሱ የታዘዘው በጌታው አምልኮ ላይ ማንንም ሳያጋራ በኢኽላስ እንዲኖር ብቻ ነው፡-
” ﻗُﻞْ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺃَﻧَﺎ ﺑَﺸَﺮٌ ﻣِﺜْﻠُﻜُﻢْ ﻳُﻮﺣَﻰ ﺇِﻟَﻲَّ ﺃَﻧَّﻤَﺎ ﺇِﻟَﻬُﻜُﻢْ ﺇِﻟَﻪٌ ﻭَﺍﺣِﺪٌ ﻓَﻤَﻦْ ﻛَﺎﻥَ ﻳَﺮْﺟُﻮ ﻟِﻘَﺎﺀَ ﺭَﺑِّﻪِ ﻓَﻠْﻴَﻌْﻤَﻞْ ﻋَﻤَﻠًﺎ ﺻَﺎﻟِﺤًﺎ ﻭَﻟَﺎ ﻳُﺸْﺮِﻙْ ﺑِﻌِﺒَﺎﺩَﺓِ ﺭَﺑِّﻪِ ﺃَﺣَﺪًﺍ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻜﻬﻒ 110
“እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት፥ ወደኔ የሚወርድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ፤ ነኝ፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፤ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ፣ በላቸው።” (ሱረቱል ከህፍ 110)፡፡
” ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﻤُﻨَﺎﻓِﻘِﻴﻦَ ﻓِﻲ ﺍﻟﺪَّﺭْﻙِ ﺍﻟْﺄَﺳْﻔَﻞِ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺭِ ﻭَﻟَﻦْ ﺗَﺠِﺪَ ﻟَﻬُﻢْ ﻧَﺼِﻴﺮًﺍ * ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺗَﺎﺑُﻮﺍ ﻭَﺃَﺻْﻠَﺤُﻮﺍ ﻭَﺍﻋْﺘَﺼَﻤُﻮﺍ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺃَﺧْﻠَﺼُﻮﺍ ﺩِﻳﻨَﻬُﻢْ ﻟِﻠَّﻪِ ﻓَﺄُﻭﻟَﺌِﻚَ ﻣَﻊَ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻭَﺳَﻮْﻑَ ﻳُﺆْﺕِ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﺃَﺟْﺮًﺍ ﻋَﻈِﻴﻤًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ 145-146
“መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፤ ለነሱም ረዳትን አታገኝላቸውም። እነዚያ የተመለሱ (ሥራቸውን) ያሳመሩም፤ በአላህም የተጠበቁ፤ ሀይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉ ሲቀሩ፣ እነዚያስ ከምእመናን ጋር ናቸው፤ ለምእመናንም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል።” (ሱረቱ-ኒሳእ 145-146)፡፡
” ﻗُﻞْ ﺇِﻧِّﻲ ﺃُﻣِﺮْﺕُ ﺃَﻥْ ﺃَﻋْﺒُﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻣُﺨْﻠِﺼًﺎ ﻟَﻪُ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺰﻣﺮ 11
“በል፦ እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ሆኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ” (ሱረቱ-ዙመር 11)፡፡
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- “የአላህ መልክተኛን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሰዎች ሁሉ በርሶ ሸፋዐ (የትንሳኤ ቀን ምልጃ) እድለኛው ማነው? ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹በኔ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ እድለኛ የሚሆነው ከልቡ በኢኽላስ ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ ያለ ሰው ነው›› በማለት መለሱልኝ” (ቡኻሪይ 6570)፡፡
ረ. ‹‹ፍቅርና ውዴታ መኖሩ››፡-
“ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” የሚለውን የእምነት ቃል የሚመሰክር ሙስሊም ወዶና አፍቅሮ እንጂ፡ ጠልቶና ተገዶ መሆን የለበትም፡፡ ያለ-ምርጫው ተገዶ፡ ሳይፈልገውና ሳይወደው የጠላ ሆኖ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” የሚል ሰው፡ ምስክርነቱ አላህ ዘንድ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ አላህ ተወዶና ተፈቅሮ የሚመለክ አምላክ እንጂ ተጠልቶ የሚመለክ አምላክ አይደለምና፡፡ ምክንያቱም እሱ በኛ አምልኮ የሚጨምረው ወይም በክህደታችን የሚቀነስው የሆነ ነገር የለውምና፡፡ የአማኞችም ባሕሪ ይህ እንደሆነ ቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ይገልጻል፡-
” ﻭَﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻣَﻦْ ﻳَﺘَّﺨِﺬُ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻧْﺪَﺍﺩًﺍ ﻳُﺤِﺒُّﻮﻧَﻬُﻢْ ﻛَﺤُﺐِّ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺃَﺷَﺪُّ ﺣُﺒًّﺎ ﻟِﻠَّﻪِ “… ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 165
“ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው…” (ሱረቱል በቀራህ 165)፡፡
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻣَﻦْ ﻳَﺮْﺗَﺪَّ ﻣِﻨْﻜُﻢْ ﻋَﻦْ ﺩِﻳﻨِﻪِ ﻓَﺴَﻮْﻑَ ﻳَﺄْﺗِﻲ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻘَﻮْﻡٍ ﻳُﺤِﺒُّﻬُﻢْ ﻭَﻳُﺤِﺒُّﻮﻧَﻪُ ﺃَﺫِﻟَّﺔٍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﺃَﻋِﺰَّﺓٍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻜَﺎﻓِﺮِﻳﻦَ ﻳُﺠَﺎﻫِﺪُﻭﻥَ ﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻟَﺎ ﻳَﺨَﺎﻓُﻮﻥَ ﻟَﻮْﻣَﺔَ ﻟَﺎﺋِﻢٍ ﺫَﻟِﻚَ ﻓَﻀْﻞُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻳُﺆْﺗِﻴﻪِ ﻣَﻦْ ﻳَﺸَﺎﺀُ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺍﺳِﻊٌ ﻋَﻠِﻴﻢٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ 54
“እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው፣ አላህ (በነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን፣ በምእመናን ላይ ትሁቶች፣ በከሐዲዎች ላይ ኃያላን የኾኑን፣ በአላህ መንገድ የሚታገሉን፣ የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩን ሕዝቦች በእርግጥ ያመጣል፤ ይኽ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው።” (ሱረቱል ማኢዳህ 54)፡፡
አላህን የመውደድ ምልክቱም፡- መልክተኛውን መከተል፣ አላህ የወደደውን መውደድ፣ እሱ የጠላውን መጥላት ነው፡-
” ﻗُﻞْ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺗُﺤِﺒُّﻮﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻓَﺎﺗَّﺒِﻌُﻮﻧِﻲ ﻳُﺤْﺒِﺒْﻜُﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ ﺫُﻧُﻮﺑَﻜُﻢْ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَﺣِﻴﻢٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ 31
“በላቸዉ- አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ፣ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኅጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነዉ።” (ሱረቱ አለ-ዒምራን 31)፡፡
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻟَﺎ ﺗَﺘَّﺨِﺬُﻭﺍ ﺁﺑَﺎﺀَﻛُﻢْ ﻭَﺇِﺧْﻮَﺍﻧَﻜُﻢْ ﺃَﻭْﻟِﻴَﺎﺀَ ﺇِﻥِ ﺍﺳْﺘَﺤَﺒُّﻮﺍ ﺍﻟْﻜُﻔْﺮَ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﺈِﻳﻤَﺎﻥِ ﻭَﻣَﻦْ ﻳَﺘَﻮَﻟَّﻬُﻢْ ﻣِﻨْﻜُﻢْ ﻓَﺄُﻭﻟَﺌِﻚَ ﻫُﻢُ ﺍﻟﻈَّﺎﻟِﻤُﻮﻥَ * ﻗُﻞْ ﺇِﻥْ ﻛَﺎﻥَ ﺁﺑَﺎﺅُﻛُﻢْ ﻭَﺃَﺑْﻨَﺎﺅُﻛُﻢْ ﻭَﺇِﺧْﻮَﺍﻧُﻜُﻢْ ﻭَﺃَﺯْﻭَﺍﺟُﻜُﻢْ ﻭَﻋَﺸِﻴﺮَﺗُﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻣْﻮَﺍﻝٌ ﺍﻗْﺘَﺮَﻓْﺘُﻤُﻮﻩﺍَ ﻭَﺗِﺠَﺎﺭَﺓٌ ﺗَﺨْﺸَﻮْﻥَ ﻛَﺴَﺎﺩَﻫَﺎ ﻭَﻣَﺴَﺎﻛِﻦُ ﺗَﺮْﺿَﻮْﻧَﻬَﺎ ﺃَﺣَﺐَّ ﺇِﻟَﻴْﻜُﻢْ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻪِ ﻭَﺟِﻬَﺎﺩٍ ﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻠِﻪِ ﻓَﺘَﺮَﺑَّﺼُﻮﺍ ﺣَﺘَّﻰ ﻳَﺄْﺗِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﺄَﻣْﺮِﻩِ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﻬْﺪِﻱ ﺍﻟْﻘَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻔَﺎﺳِﻘِﻴﻦَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺘﻮﺑﺔ 23-24
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክሕደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ፣ ወዳጆች አድርጋቸሁ አትያዙዋቸው፤ ከናንተም ዉስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው፣ እነዚያ እርሱ በዳዮች ናቸው፤ አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸዉ ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛዉ በርሱ መንገድም ከመታገል፣ ይበልጥ የተወደዱ እንደሆኑ፣ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ፣ በላቸው፤ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።” (ሱረቱ-ተውባህ 23-24)፡፡
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ሶስት ነገሮች የተገኙበት ሰው፡ እሱም በነሱ የኢማንን ጥፍጥና አገኘ፡፡(አንደኛው) አላህና መልክተኛው ከተቀሩ ነገሮች ሁሉ በልጠው እሱ ዘንድ የተወደዱ ከሆነ፣ (ሁለተኛው) ሙስሊም ወንድሙን ሲወደው ለአላህ ብሎ እንጂ ለሌላ የማይወደው ከሆነ፣ (ሶስተኛው) አላህ ከክህደት ካተረፈው በኋላ ተመልሶ ወደ ኩፍር መግባትን እሳት ላይ የመወርወርን ያህል የሚጠላ ከሆነ ነው” (ሙስሊም 174)፡፡
ሰ. ‹‹ከአላህ ውጭ ባለው መካድ››፡-
ከ”ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” መስፈርቶች አንዱ፡- ከአላህ ውጪ የሚመለኩ በሆኑ ነገሮች ሁሉ መካድ ማለት ነው፡፡ ከርሱ ውጪ ያሉ አምልኮቶች ሁሉ ከንቱ መሆናቸውን በማመን ከነሱ መራቅ፡ የሚያመልኳቸውም ሰዎች ሙሽሪኮች በመሆናቸው ከነሱ መራቅና በሽርካቸው እነሱን ጠላት አድርጎ መያዝ (ወደ ተውሒድ ጥሪ ከማድረግ ጋር) ግድ ነው፡፡
” ﻗَﺪْ ﻛَﺎﻧَﺖْ ﻟَﻜُﻢْ ﺃُﺳْﻮَﺓٌ ﺣَﺴَﻨَﺔٌ ﻓِﻲ ﺇِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢَ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻣَﻌَﻪُ ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﻟِﻘَﻮْﻣِﻬِﻢْ ﺇِﻧَّﺎ ﺑُﺮَﺁﺀُ ﻣِﻨْﻜُﻢْ ﻭَﻣِﻤَّﺎ ﺗَﻌْﺒُﺪُﻭﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻛَﻔَﺮْﻧَﺎ ﺑِﻜُﻢْ ﻭَﺑَﺪَﺍ ﺑَﻴْﻨَﻨَﺎ ﻭَﺑَﻴْﻨَﻜُﻢُ ﺍﻟْﻌَﺪَﺍﻭَﺓُ ﻭَﺍﻟْﺒَﻐْﻀَﺎﺀُ ﺃَﺑَﺪًﺍ ﺣَﺘَّﻰ ﺗُﺆْﻣِﻨُﻮﺍ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺣْﺪَﻩُ “… ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﻤﺘﺤﻨﺔ 4
“በኢብራሂምና በነዚያ ከርሱ ጋር በነበሩት (ምእመናን) መካከል መከተል አለቻችሁ። ለሕዝቦቻቸው፦ እኛ ከናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን በናንተ ካድን፤ በላህ አንድ ብቻ ሲሆን እስከምታምኑ ድረስ በኛና በናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፤ ባሉ ጊዜ( መልካም መከተል አለቻችሁ) …” (ሱረቱል ሙምተሒናህ 4)፡፡
” ﻟَﺎ ﺇِﻛْﺮَﺍﻩَ ﻓِﻲ ﺍﻟﺪِّﻳﻦِ ﻗَﺪْ ﺗَﺒَﻴَّﻦَ ﺍﻟﺮُّﺷْﺪُ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻐَﻲِّ ﻓَﻤَﻦْ ﻳَﻜْﻔُﺮْ ﺑِﺎﻟﻄَّﺎﻏُﻮﺕِ ﻭَﻳُﺆْﻣِﻦْ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻘَﺪِ ﺍﺳْﺘَﻤْﺴَﻚَ ﺑِﺎﻟْﻌُﺮْﻭَﺓِ ﺍﻟْﻮُﺛْﻘَﻰ ﻟَﺎ ﺍﻧْﻔِﺼَﺎﻡَ ﻟَﻬَﺎ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﺳَﻤِﻴﻊٌ ﻋَﻠِﻴﻢٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 256
“በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 256)፡፡
የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በአንድ ሐዲሣቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡- “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ ያለና ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ደሙን ማፍሰስም ሆነ ንብረቱን መውረስ ሐራም ነው፡፡ ምርመራውም (ያለው ከልቡ ይሁን አይሁን) በጌታው ላይ ብቻ ነው” (ሙስሊም 139)፡፡ ይቀጥላል ኢንሻአላህ፡፡