የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” 29 በአቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
581 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
10. ማጠቃለያ፡-
እስካሁን በቆየንባቸው ሃያ ዘጠኝ ክፍሎች ውስጥ ስለ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” መሰረታዊ የሆኑ ዘጠኝ ነገሮችን በመጠኑ ተመልክተናል አልሐምዱ ሊላህ፡፡ ለዛሬ ማጠቃለያ እንዲሆነን ስለ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” የሚናገሩ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾችን በመጠኑም ቢሆን በተወሰነ መልኩ ከፍለን እንመለከታቸዋለን፡፡
1. በቀጥታ ቃሉ የተነገረ፡-
አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ውስጥ በቀጥታ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” በማለት ከርሱ በስተቀር አምልኮ የሚገባው አምላክ አለመኖሩን በሶስት ቦታዎች ላይ ነግሮናል፡፡ እነዚህም፡-
” ﻓَﺎﻋْﻠَﻢْ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺍﺳْﺘَﻐْﻔِﺮْ ﻟِﺬَﻧْﺒِﻚَ ﻭَﻟِﻠْﻤُﺆْﻣِﻨِﻲﻥَ ﻭَﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨَﺎﺕِ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻣُﺘَﻘَﻠَّﺒَﻜُﻢْ ﻭَﻣَﺜْﻮَﺍﻛُﻢْ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻣﺤﻤﺪ 19
“እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ዕወቅ፤ ስለ ስሕተትም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፤ አላህም መዘዋወሪያችሁን መርጊያችሁንም ያውቃል።” (ሱረቱ ሙሐመድ 19)፡፡
” ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﺇِﺫَﺍ ﻗِﻴﻞَ ﻟَﻬُﻢْ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻳَﺴْﺘَﻜْﺒِﺮُﻭﻥَ * ﻭَﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺃَﺋِﻨَّﺎ ﻟَﺘَﺎﺭِﻛُﻮ ﺁﻟِﻬَﺘِﻨَﺎ ﻟِﺸَﺎﻋِﺮٍ ﻣَﺠْﻨُﻮﻥٍ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺼﺎﻓﺎﺕ 36-35
“እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ በነሩ። እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተዉ ነን? ይሉም ነበር።” (ሱረቱ-ሷፍፋት 35-36)፡፡
” ﺇِﻥَّ ﻫَﺬَﺍ ﻟَﻬُﻮَ ﺍﻟْﻘَﺼَﺺُ ﺍﻟْﺤَﻖُّ ﻭَﻣَﺎ ﻣِﻦْ ﺇِﻟَﻪٍ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﻬُﻮَ ﺍﻟْﻌَﺰِﻳﺰُ ﺍﻟْﺤَﻜِﻴﻢُ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ 62
“ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነዉ፤ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም። አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 62)፡፡
2. በእኔነት የተገለጸ፡-
ይህ ደግሞ፡- ጌታችን አላህ በቁርኣን ውስጥ ፡- ከእኔ በቀር ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም በማለት፡ በቀጥታ በ ‹‹እኔነት›› ስለ እራሱ የተናገረበት ነው፡፡
” ﻳُﻨَﺰِّﻝُ ﺍﻟْﻤَﻠَﺎﺋِﻜَﺔَ ﺑِﺎﻟﺮُّﻭﺡِ ﻣِﻦْ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ﻋَﻠَﻰ ﻣَﻦْ ﻳَﺸَﺎﺀُ ﻣِﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩِﻩِ ﺃَﻥْ ﺃَﻧْﺬِﺭُﻭﺍ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺃَﻧَﺎ ﻓَﺎﺗَّﻘُﻮﻥِ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺤﻞ 2
“ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፤ (ከሐዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም ፍሩኝም ማለትን (አሳታውቁ በማለት ያወርዳል)።” (ሱረቱ-ነሕል 2)፡፡
” ﺇِﻧَّﻨِﻲ ﺃَﻧَﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺃَﻧَﺎ ﻓَﺎﻋْﺒُﺪْﻧِﻲ ﻭَﺃَﻗِﻢِ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓَ ﻟِﺬِﻛْﺮِﻱ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻃﻪ 14
“እኔ አላህ እኔ ነኝ፣ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፤ ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ።” (ሱረቱ ጣሀ 14)፡፡
” ﻭَﻣَﺎ ﺃَﺭْﺳَﻠْﻨَﺎ ﻣِﻦْ ﻗَﺒْﻠِﻚَ ﻣِﻦْ ﺭَﺳُﻮﻝٍ ﺇِﻟَّﺎ ﻧُﻮﺣِﻲ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺃَﻧَﺎ ﻓَﺎﻋْﺒُﺪُﻭﻥِ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ 25
“ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።” (ሱረቱል አንቢያእ 25)፡፡
3. በእሱነት የተገለጸ፡-
በዚህኛው መንገድ ደግሞ፡- አላህ እሱ ብቻ እውነተኛ አምላክ መሆኑን ለሰዎች እንድናስተምርና እንድንመሰክር፡ እራሱን በ ‹‹እሱነት›› በመግለጽ፡ እሱ ብቻ ነው እውነተኛ አምላክ ይለናል፡-
” ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﺍﻟْﺤَﻲُّ ﺍﻟْﻘَﻴُّﻮﻡُ “… ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 255
“አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው…” (ሱረቱል በቀራህ 255)፡፡
” ﻫُﻮَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳُﺼَﻮِّﺭُﻛُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺣَﺎﻡِ ﻛَﻴْﻒَ ﻳَﺸَﺎﺀُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﺍﻟْﻌَﺰِﻳﺰُ ﺍﻟْﺤَﻜِﻴﻢُ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ 6
“እርሱ ያ በማሕፀኖች ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነዉ። ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 6)፡፡
” ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﻟَﻴَﺠْﻤَﻌَﻨَّﻚُﻡْ ﺇِﻟَﻰ ﻳَﻮْﻡِ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔِ ﻟَﺎ ﺭَﻳْﺐَ ﻓِﻴﻪِ ﻭَﻣَﻦْ ﺃَﺻْﺪَﻕُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺣَﺪِﻳﺜًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ 87
“አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?” (ሱረቱ-ኒሳእ 87)፡፡
4. በአንተነት የተገለጸ፡-
እዚህ ላይ ደግሞ፡- እኛ ከአንተ በቀር ሌላ እውነተኛ አምላክ የለም በማለት እንድንማጸነውና እንድንለምነው፡ እንድናወድሰውና እንድንዘክረው ይረዳን ዘንድ፡ እራሱን በ ‹‹አንተነት›› በመግለጽ ያስተምራል፡-
” ﻭَﺫَﺍ ﺍﻟﻨُّﻮﻥِ ﺇِﺫْ ﺫَﻫَﺐَ ﻣُﻐَﺎﺿِﺒًﺎ ﻓَﻈَﻦَّ ﺃَﻥْ ﻟَﻦْ ﻧَﻘْﺪِﺭَ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻓَﻨَﺎﺩَﻯ ﻓِﻲ ﺍﻟﻈُّﻠُﻤَﺎﺕِ ﺃَﻥْ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺃَﻧْﺖَ ﺳُﺒْﺤَﺎﻧَﻚَ ﺇِﻧِّﻲ ﻛُﻨْﺖُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻈَّﺎﻟِﻤِﻴﻦَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ 87
“የዐሣውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፤ እርሱም ላይ ፍጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ፤ (ዐሳም ዋጠው)፤ በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ ፦ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ።” (ሱረቱል አንቢያእ 87)፡፡
በመጨረሻም ከሊመቱ ሸሀዳህ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ከከንፈር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳይኖረው (የላይኛው ከንፈር ከታችኛው ሳይገናኝ) ማንም ሰው ሊናገረው የሚችል መሆኑ እጅጉኑ የሚገርም ነገር ነው፡፡፡ ሱብሓነላህ፡፡ ሌሎች አይነት ዚክሮችን (ሱብሓነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ አላሁ አክበር…) ያለ ከንፈር ንክኪ በምንም መልኩ መናገር አንችልም፡፡ እስኪ በግል ሞክሩት፡፡ ከኢስላም መልእክት የመጀመሪያው ክፍል የሆነውን የ”ላ-ኢላሀ ኢለሏህ”ን ትምሕርት በዚሁ እናጠናቅቅና ከተወሰኑ ቀናት እረፍት በኋላ ደግሞ ሁለተኛውን ክፍል ይዤ እቀርባለሁ ኢንሻአላህ፡፡ አላህ በሰላም ያቆየን፡፡ ተፈጸመ!!