የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” 24 በአቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
404 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
7. አፍራሽ ተግባራት፡-
3. ኒፋቅ (አስመሳይነት)፡-
ለ. ኒፋቁን አስገር (ትንሹ ንፍቅና)፡-
ባለፈው ከመናፍቃን ባሕሪ ከሆነው ውስጥ ወደ ስምንት ነጥቦችን ተመልክተን ነበር፡፡ ከዛ የቀጠለውን ክፍል ‹‹ትንሹን ኒፋቅ›› በተመለከተ በአላህ ፈቃድ ዛሬ እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡፡
ስራውና ተግባሩ የመናፍቃን ሆኖ፡ ባለቤቱን ከኢስላም የማያስወጣው፡ ነገር ግን በኃጢአት የሚያስከስስ ተግባር የሆነው ‹‹ኒፋቁን ዐመሊይ›› (በስራ የሚታይ መናፍቅነት) ይሰኛል፡፡ የዚህ ባሕሪ ባለቤት በልቡ ክህደትን አልያዘም፡፡ ውስጡ አማኝ ነው፡፡ ሆኖም ከኢማኑ ድክመት የተነሳ በንግግሩና በተግባሩ ከፊል የመናፍቃን ባሕሪ ይታይበታል፡፡ ያም ኃጢአተኛ ያደርገዋል እንጂ ከኢስላም አጥር አያስወጣውም፡፡
እነዚህን ባሕሪያት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በአንድ ሐዲሥ ጠቅለል አድርገው እንዲህ ይገልጹታል፡-
ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አራት ነገሮች ያሉበት ሰው፡ ግልጽ ሙናፊቅ ሆኗል፡፡ ከአራቱ ውስጥ አንዱ ያለበት ሰው ደግሞ እስኪተወው ድረስ ከኒፋቅ ከፊሉ ባሕሪ አለበት ማለት ነው፡፡ (እነሱም)፡- ሲታመን ይከዳል፣ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ገብቶ ያፈርሳል፣ ሲከራከር ያምጻል” (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
መናፍቃንን በተመለከተ በተወሰነ ደረጃ እንዲህ ከተመለከትን፡ ከዚህ በመቀጠል እነሱን በተመለከተ የኛ አቋም ምን መሆን እንዳለበት በተወሰነ መልኩ እንመልከት፡- የሙስሊም አቋም፡-
1. እነሱን አለመታዘዝ፡-
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺍﺗَّﻖِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﻄِﻊِ ﺍﻟْﻜَﺎﻓِﺮِﻳﻦَ ﻭَﺍﻟْﻤُﻨَﺎﻓِﻘِﻲﻥَ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻛَﺎﻥَ ﻋَﻠِﻴﻤًﺎ ﺣَﻜِﻴﻤًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﺣﺰﺍﺏ 1
“አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህን ፍራ፤ ከሐዲዎችንና መናፍቃንንም አትታዘዝ። አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና።” (ሱረቱል አሕዛብ 1)፡፡
2. እነሱን መገሰጽና ከነሱ መራቅ፡-
” ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻓَﺄَﻋْﺮِﺽْ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻭَﻋِﻈْﻬُﻢْ ﻭَﻗُﻞْ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺑَﻠِﻴﻐًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ 63
“እነዚህ፣ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው። እነርሱንም ተዋቸው፤ ገሥጻቸውም፤ ለነርሱም በነፍሶቻቸው፣ ውስጥ ስሜት ያለውን (የሚያጭር) ቃል ተናገራቸው።” (ሱረቱ-ኒሳእ 63)፡፡
3. ስለነሱ አለመከራከር፡-
” ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺠَﺎﺩِﻝْ ﻋَﻦِ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺨْﺘَﺎﻧُﻮﻥَ ﺃَﻧْﻔُﺴَﻬُﻢْ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﺎ ﻳُﺤِﺐُّ ﻣَﻦْ ﻛَﺎﻥَ ﺧَﻮَّﺍﻧًﺎ ﺃَﺛِﻴﻤًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ 107
“ከነዚያም ነፍሶቻቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር፤ አላህ ከዳተኛ ኀጢአተኛ የሆነን ሰው አይወድምና።” (ሱረቱ-ኒሳእ 107)፡፡
4. እነሱን ወዳጅ አድርጎ አለመያዝ፡-
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻟَﺎ ﺗَﺘَّﺨِﺬُﻭﺍ ﺑِﻄَﺎﻧَﺔً ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻧِﻜُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﺄْﻟُﻮﻧَﻜُﻢْ ﺧَﺒَﺎﻟًﺎ ﻭَﺩُّﻭﺍ ﻣَﺎ ﻋَﻨِﺘُّﻢْ ﻗَﺪْ ﺑَﺪَﺕِ ﺍﻟْﺒَﻐْﻀَﺎﺀُ ﻣِﻦْ ﺃَﻓْﻮَﺍﻫِﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﺗُﺨْﻔِﻲ ﺻُﺪُﻭﺭُﻫُﻢْ ﺃَﻛْﺒَﺮُ ﻗَﺪْ ﺑَﻴَّﻨَّﺎ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻟْﺂﻳَﺎﺕِ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺗَﻌْﻘِﻠُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ 118
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን።” (ሱረቱ አለ-ዒምራን 118)፡፡
5. እነሱን መታገል እና በነሱ ላይ መጠንከር፡-
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺟَﺎﻫِﺪِ ﺍﻟْﻜُﻔَّﺎﺭَ ﻭَﺍﻟْﻤُﻨَﺎﻓِﻘِﻲﻥَ ﻭَﺍﻏْﻠُﻆْ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺄْﻭَﺍﻫُﻢْ ﺟَﻬَﻨَّﻢُ ﻭَﺑِﺌْﺲَ ﺍﻟْﻤَﺼِﻴﺮُ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺘﻮﺑﺔ 73
“አንተ ነቢዩ ሆይ ከሐዲዎችንና መናፍቃንን ታገል፤ በነሱም ላይ ጨክን፤ መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት፤ መመለሻይቱም ከፋች።” (ሱረቱ-ተውባህ 73)፡፡
6. ቦታ አለመስጠት፡ አሳንሶ ማየት፡-
ቡረይዳ ከአባቱ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ለሙናፊቅ ያ ሰይድ! (አለቃ ሆይ!) አትበሉት፡፡ እሱ አለቃና መሪ ከሆነ ጌታችሁን አስቆጣችሁት ማለት ነው” (አቡ ዳዉድ 4979)፡፡
7. ከሞቱ በነሱ ላይ አለመስገድ፡-
” ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺼَﻞِّ ﻋَﻠَﻰ ﺃَﺣَﺪٍ ﻣِﻨْﻬُﻢْ ﻣَﺎﺕَ ﺃَﺑَﺪًﺍ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻘُﻢْ ﻋَﻠَﻰ ﻗَﺒْﺮِﻩِ ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻪِ ﻭَﻣَﺎﺗُﻮﺍ ﻭَﻫُﻢْ ﻓَﺎﺳِﻘُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺘﻮﺑﺔ 84
“ከነሱም በአንድም በሞተ ሰው ላይ ፈጽሞ አትሥገድ፤ በመቃብሩም ላይ አትቁም፤ እነሱ በአላህና በመልክተኛው ክደዋልና፤ እነሱም አመጠኞች ሆነው ሞተዋልና።” (ሱረቱ-ተውባህ 84)፡፡