የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” 13 በኡስታዝ አቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
400 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
7. አፍራሽ ተግባራት፡-
1. ሺርክ (ማጋራት)
ሀ. ትልቁ ሺርክ፡-
4. ፍጡራንን እንደ አላህ መውደድ፡-
ለአላህ ያለንን ፍቅር ለፍጡር አሳልፎ መስጠት የ‹‹ሺርክ›› ተግባር መሆኑን ለመረዳት፡ ቅድሚያ አላህን መውደድ ዒባዳህ መሆኑን እንመልከት፡፡
አላህን መውደድ በልብ ከሚፈጸሙ ታላላቅ የዒባዳህ ክፍሎች የሚመደብ ነው፡፡ ደግሞስ እንዴት አይወደድ? እኛ በዚህ ዓለም ላይ የምንፈልጋቸውንም ሆነ የምንወዳቸውን ነገራት ማነው አሟልቶ የለገሰን? ከራሳችን ብንጀምር፡- ከባዶነት ወደ ሕያውነት በማምጣት በምድር ላይ ፈጠረን፣ ለመኖር እንዲያስችለንም ከበላያችን ዝናብን በማዝነብ፡ ምድር ደግሞ ተቀብላ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እንድታበቅል፡ ያበቀለችውን ደግሞ ለኛም ለእንሰሳትም ሲሳይ አደረገልን፡፡ (ሱረቱ ዐበሰ 24-32)፡፡
ማሰብ የሚችል አእምሮ፣ መስማት የሚችል ጆሮ፣ መመልከት የሚችል ዓይን፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ መንቀሳቀስ የሚችል እግር፣ መያዝና መጨበጥ፡ መስጠትና መለገስ የሚችል እጅ የሰጠን እሱ አይደለምን? (ሱረቱ-ነሕል 78)፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ በነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አማካይነት በምድራዊ ሕይወታችን የቀልብ እርጋታ፡ በአኼራው ደግሞ ዘላለማዊ ደስታ ሊያስገኝልን የሚችለውን ዲነል-ኢስላምን ለገሰን፡፡ ታዲያ እሱ ጌታችን አላህ ያልተወደደ ማን ይወደድ? እስኪ እነዚህን ጸጋዎቹን የገለጸባቸውን አንቀጾች በከፊሉም ቢሆን በመመልከት እናስተንትን፡-
” ﻓَﻠْﻴَﻨْﻈُﺮِ ﺍﻟْﺈِﻧْﺴَﺎﻥُ ﺇِﻟَﻰ ﻃَﻌَﺎﻣِﻪِ * ﺃَﻧَّﺎ ﺻَﺒَﺒْﻨَﺎ ﺍﻟْﻤَﺎﺀَ ﺻَﺒًّﺎ * ﺛُﻢَّ ﺷَﻘَﻘْﻨَﺎ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﺷَﻘًّﺎ * ﻓَﺄَﻧْﺒَﺘْﻨَﺎ ﻓِﻴﻬَﺎ ﺣَﺒًّﺎ * ﻭَﻋِﻨَﺒًﺎ ﻭَﻗَﻀْﺒًﺎ * ﻭَﺯَﻳْﺘُﻮﻧًﺎ ﻭَﻧَﺨْﻠًﺎ * ﻭَﺣَﺪَﺍﺋِﻖَ ﻏُﻠْﺒًﺎ * ﻭَﻓَﺎﻛِﻬَﺔً ﻭَﺃَﺑًّﺎ * ﻣَﺘَﺎﻋًﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻭَﻟِﺄَﻧْﻌَﺎﻣِﻚُﻡْ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻋﺒﺲ 24-32
“ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፤እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ወይንንም፤ እርጥብ ሳርንም፤የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)።ለናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)።” (ሱረቱ ዐበሰ 24-32)፡፡
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﺍﻋْﺒُﺪُﻭﺍ ﺭَﺑَّﻜُﻢُ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻘَﻜُﻢْ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻣِﻦْ ﻗَﺒْﻠِﻜُﻢْ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗَﺘَّﻘُﻮﻥَ * ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺟَﻌَﻞَ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﻓِﺮَﺍﺷًﺎ ﻭَﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀَ ﺑِﻨَﺎﺀً ﻭَﺃَﻧْﺰَﻝَ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻣَﺎﺀً ﻓَﺄَﺧْﺮَﺝَ ﺑِﻪِ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺜَّﻤَﺮَﺍﺕِ ﺭِﺯْﻗًﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻓَﻠَﺎ ﺗَﺠْﻌَﻠُﻮﺍ ﻟِﻠَّﻪِ ﺃَﻧْﺪَﺍﺩًﺍ ﻭَﺃَﻧْﺘُﻢْ ﺗَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 21-22
“እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡(እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 21-22)፡፡
” ﺃَﻟَﻢْ ﻧَﺠْﻌَﻞْ ﻟَﻪُ ﻋَﻴْﻨَﻴْﻦِ * ﻭَﻟِﺴَﺎﻧًﺎ ﻭَﺷَﻔَﺘَﻴْﻦِ * ﻭَﻫَﺪَﻳْﻨَﺎﻩُ ﺍﻟﻨَّﺠْﺪَﻳْﻦِ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺒﻠﺪ 8-10
“ለርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፤ሁለት መንገዶችም አልመራነውምን?” (ሱረቱል በለድ 8-10)፡፡
…” ﺍﻟْﻴَﻮْﻡَ ﺃَﻛْﻤَﻠْﺖُ ﻟَﻜُﻢْ ﺩِﻳﻨَﻜُﻢْ ﻭَﺃَﺗْﻤَﻤْﺖُ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﻧِﻌْﻤَﺘِﻲ ﻭَﺭَﺿِﻴﺖُ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻟْﺈِﺳْﻠَﺎﻡَ ﺩِﻳﻨًﺎ ” … ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ 3
“…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ..” (ሱረቱል ማኢዳህ 3)፡፡
” ﻭَﺁﺗَﺎﻛُﻢْ ﻣِﻦْ ﻛُﻞِّ ﻣَﺎ ﺳَﺄَﻟْﺘُﻤُﻮﻩُ ﻭَﺇِﻥْ ﺗَﻌُﺪُّﻭﺍ ﻧِﻌْﻤَﺖَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻟَﺎ ﺗُﺤْﺼُﻮﻫَﺎ ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﺈِﻧْﺴَﺎﻥَ ﻟَﻈَﻠُﻮﻡٌ ﻛَﻔَّﺎﺭٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ 34
“ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፤ የአላህን ጸጋ ብትቆጥሩ፣ አትዘልቋትም፤ ሰው በጣም በደለኛ ከሐዲ ነው።” (ሱረቱ ኢብራሂም 34)፡፡
” ﻭَﺇِﻥْ ﺗَﻌُﺪُّﻭﺍ ﻧِﻌْﻤَﺔَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻟَﺎ ﺗُﺤْﺼُﻮﻫَﺎ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﻐَﻔُﻮﺭٌ ﺭَﺣِﻴﻢٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺤﻞ 18
“የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፤ አላህ በእርግጥም መሐሪ አዛኝ ነውና።” (ሱረቱ-ነሕል 18)፡፡
በነዚህ አንቀጾች ብቻ እንኳ እኛ የጌታችን አላህ የውለታው ባለ-ዕዳዎች መሆናችንን መረዳት ይቻላል፡፡ አላህ ለውለታው ክፍያን ቢጠይቀን ኖሮ ምን ይሆን መልሳችን? ለዚህ ውለታ የተጠየቅነው ክፍያ “ምስጋና” ብቻ ነው፡፡ የምናመሰግነውም በጸጋ ላይ ሌላ ጸጋ ሊጨመርልን እንጂ ጌታችን የምስጋና እጥረት ኖሮበት አይደለም፡-
“ጌታችሁም፦ ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋላሁ)፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)።” (ሱረቱ ኢብራሂም 7)፡፡
አላህን ከማመን ብናፈገፍግ እራሳችንን እንጎዳለን እንጂ እሱን አንጎዳውም፡፡ እሱ ከፈለገ የሚወዳቸውንና የሚወዱትን መልካም ባሮች መፍጠር ይችላል፡-
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው፣ አላህ (በነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን፣ በምእመናን ላይ ትሁቶች፣ በከሐዲዎች ላይ ኃያላን የኾኑን፣ በአላህ መንገድ የሚታገሉን፣ የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩን ሕዝቦች በእርግጥ ያመጣል፤ ይኽ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው።” (ሱረቱል በቀራህ 54)፡፡
አላህን መውደድ ከምንም ነገር በፊት ተቀዳሚው ተግባራችን መሆን ይኖርበታል፡፡ ጌታችንን የምንወደውን ያህል ፍጡራንን የምንወድ ከሆነ አሁንም ‹‹ሺርክ›› ውስጥ ወድቀናል ማለት ነው፡፡ የአላህን ውዴታ በምንም አይነት መልኩ ከፍጡር ጋር ማስተካከል አይታሰብም፡፡ እውነተኛ ሙእሚኖች ለአላህ ያላቸው ውዴታ እጅግ የበረታ ነውና፡-
“ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው…” (ሱረቱል በቀራህ 165)፡፡
ይህ በመሆኑም ከምንም በፊት የአላህን ውዴታ ማስቀደም ይገባናል፡፡ ቤተሰቦቻችን፣ ንብረቶቻችን፣ መኖሪያ ቤቶቻችን ሁሉ የአላህ ናቸው፡፡ የሰጠን እሱ እንደሆነ ሁሉ በፈለገው ቀንም ሊወስዳቸው ይችላል፡-
“ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 155)፡፡ እነዚህን ነገራቶች ከአላህና ከመልክተኛው አብልጠን የምንወዳቸው ከሆነ የሚጠብቀን ምን እንደሆነ አላህ በቃሉ እንዲህ ይለናል፡-
“አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸዉ ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛዉ በርሱ መንገድም ከመታገል፣ ይበልጥ የተወደዱ እንደሆኑ፣ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ፣ በላቸው፤ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።” (ሱረቱ-ተውባህ 24)፡፡ በምን እናረጋግጥ?
ምናልባትም አንድ ሰው፡- አላህን በትክክል መውደዴን ማወቅ ከፈለግሁ፡ ወይም አላህን መውደድ የሚገለጽባቸው መንገዶች ምንድናቸው? ብሎ ቢጠይቅ መልሱ፡- ነገሩን አጠር ለማድረግ እራሳችንን ሶስት ቦታዎች ላይ እንፈልግ የሚል ይሆናል፡፡ እነሱም፡-
ሀ. መልክተኛውን መከተል፡- በትክክል አላህን እወዳለሁ የሚል አንድ የአላህ ባሪያ ውዴታው ከልቡ መሆኑን ማወቅ ከፈለገ ነቢያችንን (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ተከትያለሁ ወይ? ብሎ እራሱን ይጠይቅ፡፡ የሳቸውን ፈለግ መከተል፣ ትዕዛዛቸውን ማክበር፣ የከለከሉትን መከልከል፣ ሱናቸውን መተግበር አላህን የመውደድ ፍሬ ነውና፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
“በላቸዉ- አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ፣ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኅጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነዉ።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 31)፡፡
ለ. አላህ የሚወደውን ሆኖ መገኘት፡- እውነተኛ ወዳጅ የሆነ ሰው ወዳጁን ለማስደሰት እንጂ ለማስከፋት አያስብምና፡ አላህን የሚወድ ሙስሊምም አላህ የሚወዳቸውን ነገሮች ለመተግበርና እሱ ከሚጠላቸው ነገሮች ለመራቅ መጣር አለበት፡፡ ለምሳሌ፡-
1. ፍትሕን ይወዳል፡- በዳኝነት ስራ ውስጥ ሆነን ስንፈርድም ሆነ ስንመሰክር፡ በፍትህ ከፈረድንና ከመሰከርን አላህ ዘንድ ውዴታን ያስገኝልናል፡-
“ከነዛ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጧችሁ (ከሐዲዎች) መልካም ብትውሉላቸውና ወደነሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፤ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና” (ሱረቱል ሙምተሒናህ 8)፡፡
“ከምእምናንም የሆኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፤ ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትእዛዝ እስክትመለስ ድረስ ተጋደሉ፤ ብትመለስም በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ፤ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፤ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና።” (ሱረቱል ሑጁራት 9)፡፡ በዛው ተቃራኒ በደልና በደለኞችን አይወድም፡-
“እነዚያማ ያመኑትማ፥ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት፣ ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፤ አላህም በዳዮችን አይወድም።” (ሱረቱ አለ-ዒምራን 57)፡፡
“…አላህም በዳዮችን አይወድም።” (ሱረቱ አለ-ዒምራን 140)፡፡
2. ተመላሾችን ይወዳል፡- ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን፡፡ ወደ አላህ ተጸጽተን ብንመለስ አላህ ሊምረን ቃል ገብቷል፡፡ መማር ብቻም አይደለም ወደ እኔ የሚመለሱትንም እወዳቸዋለሁ ነው ያለው፡-
“ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ አስጠያፊ ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ አትቅረቡዋቸው፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ ተገናኙዋቸው፡፡ አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 222)፡፡
“በርሱ ዉስጥ በፍጹም አትስገድ፤ ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ) መስጂድ በዉስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው በሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አልሉ፤ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል።” (ሱረቱ-ተውባህ 108)፡፡
3. እሱን የሚፈሩትን ይወዳል፡- አላህ እንዲወደን የምንፈልግ ከሆነ በየትም ስፍራ ልንፈራውና ልንጠነቀቀው ይገባናል፡፡ እሱ የሚጠነቀቁትን ይወዳልና፡-
“ከአጋሪዎቹ እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸዉና ከዚያም ምንም ያላጎደሉባችሁ በናንተ ላይም አንድንም ያልረዱባችሁ ሲቀሩ፤ (እነዚህን) ቃል ኪዳናቸዉን እስከ ጊዚያታቸዉ (መጨረሻ) ሙሉላቸዉ፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።” (ሱረቱ-ተውባህ 4)፡፡
“…በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰዉ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 76)፡፡
4. መልካም ስራን ይወዳል፡- ሌላው አላህ ዘንድ የሚያስወድደን ነገር ስራችንን መልካም አድርገን መገኘታችን ነው፡-
“አላህም የቅርቢቱን ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸዉ። አላህም በጐ አድራጊዎችን ይወዳል።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 148)፡፡
“በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 195)፡፡ “ቃልኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው ረገምናቸው፤ ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን፤ ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ። በርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተዉ። ከነሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከነርሱ የሆነን ክዳት የምታውቅባቸው ከመሆን አትወገድም፤ ከነርሱም ይቅርታ አድርግ፤ እለፋቸውም፤ አላህ መልካም ሠሪዎችን ይወዳልና።” (ሱረቱል ማኢዳህ 13)፡፡
በዛው ተቃራኒ አላህ ብልሹነትንና አበላሾችንም አይወድም፡-
“…አላህም ማበላሸትን አይወድም፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 205)፡፡
“…አላህም አበላሺዎችን አይወድም።” (ሱረቱል ማኢዳህ 64)፡፡
5. ትግስተኞችን ይወዳል፡- በሚደርስባቸው ችግርና መከራ የሚታገሱ መልካም ባርያዎቹን ይወዳቸዋል፡-
“ከነቢይም ብዙ ሊቃዉንት ከርሱ ጋር ሆነዉ የተዋጉ ብዙ ናቸዉ፤ በአላህም መንገድ ለሚደርስባቸዉ ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፤ (ለጠላት) አልተዋረዱምም አላህም ትዕግሥተኞችን ይወዳል።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 146)፡፡
6. በርሱ የሚመኩትን ይወዳቸዋል፡- ያሰብናቸው ነገራት በመላ እንዲሳኩ የአላህን እገዛ በመሻት በርሱ ላይ ከተመካን የርሱን ውዴታ እናተርፋለን፡- “ከአላህም በሆነች ችሮታ ለዘብክላቸዉ። ዐመለ መጥፎ ልበ ደረቅም በሆንክ ኖሮ ከዙርያህ በተበተኑ ነበር። ከነርሱም ይቅር በል። ለነርሱም ምሕረት ለምንላቸዉ። በነገሩም ሁሉ አማክራቸዉ። ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ። አላህ በራሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 159)፡፡
7. ለሱ ብለው የሚዋደዱትን ይወዳል፡- ለዱንያ ጥቅም ወይም በስጋ ዝምድና ሳይሆን ለአላህ ብቻ ብለው የሚዋደዱትን አላህም ይወዳቸዋል፡-
ሙዐዝ ኢብኑ-ጀበል (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- “የአላህ መልከተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፡- አላህ (በሐዲሠል ቁድሲይ ላይ) ‹‹ለኔ ብለው የሚዋደዱ፣ ለኔ ብለው የሚቀማመጡና የሚዘያየሩ፣ ለኔ ብለው የሚሰጣጡ በነሱ ላይ ውዴታዬ ግድ ሆኗል›› አለ” (ማሊክና ሌሎችም የዘገቡት)፡፡
8. ከፈርድ ቀጥሎ ሱንና ተግባራትን ማዘውተር፡- አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሐዲሥ የአላህ መልከተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አላህ እንዲህ ይላል፡- የኔን ወዳጅ ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው ጦርነት ከኔ ጋር እንደከፈተ አሳውቄዋለሁ፡፡ ባሪያዬ ግዳጅ ያረኩበትን ነገር ከመፈጸም የበለጠ ወደኔ የሚያቃርበው ነገር የለም፡፡ ባሪያዬ እኔ እስክወደው ድረስም በተጨማሪ (በሱንና) ነገሮችም ወደኔ ከመቃረብ አይቦዝንም፡፡ የወደድኩት ጊዜ የሚሰማበት ጆሮው (ሐቅን እንዲሰማ)፣ የሚመለከትበት አይኑ (አላህ የሚወደውን እንዲያይ)፣ የሚይዝበ