የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” 11 በኡስታዝ አቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
399 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
7. አፍራሽ ተግባራት፡-
1. ሺርክ (ማጋራት)
ሀ. ትልቁ ሺርክ፡-
2. ኸውፍ፡- “አላህን መፍራት” የኢባዳዎች ሁሉ ቁንጮና ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ የአኼራ ስንቅም ነው፡- “…ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው…” (ሱረቱል በቀራህ 197)፡፡ ከልብሶች ሁሉ ያማረ ልብስ፡ አላህን የመፍራት ልብስ ነው፡- “የአደም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፤ አላህን የመፍራትም ልብስ፣ ይህ የተሻለ ነው፤ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፤ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)” (ሱረቱል አዕራፍ 26)፡፡ ውጫዊው ልብስ ገላችን እንዳይታይ ነውራችን እንዳይገለጽ እንደሚሸፍነው ሁሉ፡ ውስጣዊው ልብስ “ተቅዋ” ደግሞ ቀልባችንን በምቀኝነትና መሰል በሽታዎች እንዳንለከፍና እንዳንዋረድ ይሸፍነናል፡፡ “ተቅዋ” ታላቅ የዒባዳ ዘርፍ በመሆኑ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ተላልፎ ሊሰጥ አይገባም፡፡ አላህ እንዲህ ይለናል፡- “…ሰዎችንም አትፍሩ፤ ፍሩኝም፤ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፤ አላህም ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሐዲዎች እነርሱ ናቸው” (ሱረቱል ማኢዳህ 44)። “…አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም…” (ሱረቱል በቀራህ150)፡፡ “ይሃችሁ፣ ሰይጣን ብቻ ነዉ፣ ወዳጆቹን (ብዙ እንደሆኑ በመግለጽ) ያስፈራራችኋል፤ አትፍሩዋቸውም፤ ምእምናንም እንደሆናችሁ ፍሩኝ” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 175)፡፡ “…ዛሬ እነዚያ የካዱት ከሐይማኖታችሁ ተስፋ ቆረጡ፤ ስለዚህ አትፍሩዋቸው፤ ፍሩኝም…” (ሱረቱል ማኢዳህ 3)፡፡
ከነዚህ አንቀጾች በመነሳት ከአላህ ውጪ ያሉ ፍጡራንን በሩቁና በማይችሉት ነገር ላይ መፍራት ‹‹ሺርክ›› እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ አሱም፡- ሰው ከዱንያ ነገራት እንደ ዱር አውሬ እንዲሁም ሽፍታና የለሊት ሌባን ቢፈራ ይህ ፍርሐቱ ከአላህ ፍራቻ ጋር ተጋጭቶ ዒባዳን ለፍጡር አሳልፎ ሰጠ ያሰኘዋልን? መልስ፡- ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት አላህን መፍራት ፍጡርን ከመፍራት የሚለይባቸውን ነጥቦች መመልክቱ ጠቃሚ ነው፡፡ አንድ ሙስሊም የአላህ ባሪያ የሆነ ፡ አላህን የሚፈራባቸው መገለጫዎቹ ከፍጡራን ጋር በምንም የማይገናኝ መሆኑን ለናሙና ያህል ቀጥሎ ባሉት ሶስት ነጥቦች መረዳት ይችላል፡-
ሀ. የሩቅ ፍራቻ መሆኑ፡- ሙስሊም አላህን የሚፈራው በሩቅ ነው፡፡ ገና ጌታውን በመለኮታዊ ክብሩ ሳያየው፡ ሰማያት የተንቀጠቀጡለትን ታላቁን ንግግሩን ሳይሰማው እንዲሁ በልቡ አምኖ ይፈራዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ፍራቻ ደግሞ የሚመነጨው ከትክክለኛ እምነት ነው፡፡ ስለሆነም አላህን መፍራት በሩቅ ነው፡፡ ቅድም የተጠቀሱትን ነገራት የሚፈራ ከሆነ ደግሞ በቅርቡ የሚታዩ በመሆናቸው ነው፡፡ አውሬ አፉን ከፍቶ እየጮኸ ወዳንተ ቢመጣ ሊበላህ እንጂ ሊስምህ እንዳልሆነ ታውቃለህ፡፡ ወሰን አላፊ ሽፍታንና የለሊት ሌባን ብትፈራ በእጁ ተሸክሞ የያዘው ነገር በመኖሩና ያም አንተን ለጉዳት ሊዳርግህ እንደሚችል በመስጋት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ፍርሐት ምክንያቱን ከማየት በኋላ የሚመነጭ ስለሆነ ዒባዳ ተደርጎ አይታይም፡፡ ጌታህን ግን ሳታየውና ሳትሰማው አምነህ ፈርተኸዋል፡፡ ምክንያቱም በሩቁ ባንተ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው እሱ ብቻ ነውና፡፡ እንዲህ አይነቱ ፍርሐት “ኸውፉን ዐላ-ገይብ” ይሰኛል፡፡ ለዚህ አካሄድ ተከታዩን ማስረጃ እንመለከት፡-
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻟَﻴَﺒْﻠُﻮَﻧَّﻚُﻡُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﺸَﻲْﺀٍ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺼَّﻴْﺪِ ﺗَﻨَﺎﻟُﻪُ ﺃَﻳْﺪِﻳﻜُﻢْ ﻭَﺭِﻣَﺎﺣُﻜُﻢْ ﻟِﻴَﻌْﻠَﻢَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﻦْ ﻳَﺨَﺎﻓُﻪُ ﺑِﺎﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻓَﻤَﻦِ ﺍﻋْﺘَﺪَﻯ ﺑَﻌْﺪَ ﺫَﻟِﻚَ ﻓَﻠَﻪُ ﻋَﺬَﺍﺏٌ ﺃَﻟِﻴﻢٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ 94
“እላንተ ያመናችሁ ሆይ! (በሐጅ ጊዜ) እጆቻችሁና ጦሮቻችሁ በሚያገኙት ታዳኝ አውሬ አላህ ይሞክራችኋል፤ በሩቅ ሆኖ የሚፈራውን ሰው አላህ ሊገልጽ፣ (ይሞክራችኋል) ከዚህም በኋላ ወሰንን ያለፈና ያደነ ሰው ለርሱ አሳማሚ ቅጣት አለው።” (ሱረቱል ማኢዳህ 91)፡፡
” ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺨْﺸَﻮْﻥَ ﺭَﺑَّﻬُﻢْ ﺑِﺎﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻭَﻫُﻢْ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﺎﻋَﺔِ ﻣُﺸْﻔِﻘُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ 49
“ለነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት፣ እነሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለሆኑት (መገሠጫን ሰጠን)።” (ሱረቱል አንቢያእ 49)፡፡
…” ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺗُﻨْﺬِﺭُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺨْﺸَﻮْﻥَ ﺭَﺑَّﻬُﻢْ ﺑِﺎﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻭَﺃَﻗَﺎﻣُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓَ ﻭَﻣَﻦْ ﺗَﺰَﻛَّﻰ ﻓَﺈِﻧَّﻤَﺎ ﻳَﺘَﺰَﻛَّﻰ ﻟِﻨَﻔْﺴِﻪِ ﻭَﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟْﻤَﺼِﻴﺮُ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻓﺎﻃﺮ 18
“…የምታስጠነቅቀው፣ እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሦላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፤ የተጥራራም ሰው፣ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው፤ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው።” (ሱረቱ ፋጢር 18)፡፡
” ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺗُﻨْﺬِﺭُ ﻣَﻦِ ﺍﺗَّﺒَﻊَ ﺍﻟﺬِّﻛْﺮَ ﻭَﺧَﺸِﻲَ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦَ ﺑِﺎﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻓَﺒَﺸِّﺮْﻩُ ﺑِﻤَﻐْﻔِﺮَﺓٍ ﻭَﺃَﺟْﺮٍ ﻛَﺮِﻳﻢٍ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻳﺲ 11
“የምታስጠነቅቀው ግሣጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው ፤ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው።” (ሱረቱ ያሲን 11)፡፡
” ﻭَﺃُﺯْﻟِﻔَﺖِ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔُ ﻟِﻠْﻤُﺘَّﻘِﻴﻦَ ﻏَﻴْﺮَ ﺑَﻌِﻴﺪٍ * ﻫَﺬَﺍ ﻣَﺎ ﺗُﻮﻋَﺪُﻭﻥَ ﻟِﻜُﻞِّ ﺃَﻭَّﺍﺏٍ ﺣَﻔِﻴﻆٍ * ﻣَﻦْ ﺧَﺸِﻲَ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦَ ﺑِﺎﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻭَﺟَﺎﺀَ ﺑِﻘَﻠْﺐٍ ﻣُﻨِﻴﺐٍ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻕ 31-33
“ጀነትም አላህን ለፈሩት እሩቅ ባልኾነ ስፍራ ትቅቀረባለች፡፡ ይህ ወደ አላህ ተመላሽና (ሕግጋቱን) ጠባቂ ለኾነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው (ይባላሉ)፡፡ አልረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራና በንጹሕ ልብ ለመጣ (ትቅቀረባለች)፡፡” (ሱረቱ ቃፍ 31-33)፡፡
” ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺨْﺸَﻮْﻥَ ﺭَﺑَّﻬُﻢْ ﺑِﺎﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻟَﻬُﻢْ ﻣَﻐْﻔِﺮَﺓٌ ﻭَﺃَﺟْﺮٌ ﻛَﺒِﻴﺮٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﻠﻚ 12
“እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለነሱ ምሕረትና ምንዳ አላቸው።” (ሱረቱል ሙልክ 12)፡፡
በነዚህ ስድስት ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾች መሰረት የአምልኮ አካል ተደርጎ የሚቆጠረው ፍርሐት አላህን በሩቁ (በገይብ) መፍራት ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን የሩቅ ፍርሐት ከሆነ ለፍጡር አሳልፈን የምንሰጠው ፡ሺርክ ላይ ወድቀናል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ በምኖርበት አካባቢ አንድ ጠንቋይ ቢኖርና እኔም፡- ይህ ጠንቋይ በዛው የጥንቁልና ቤቱ ሁኖ አንድ ነገር ሊያደርገኝ ይችላል፣ ጂኒዎቹን በመላክ ሊተናኮለኝ ይችላል ብይ ከፈራሁት በአላህ ላይ አሻረኩት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ጠንቋይ ሩቅን የመቆጣጠር ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ እንኳን ሊቆጣጠረን መች ሊሰማንና ሊያየን ችሎ? ነገር ግን በዛው ሰፈር ውስጥ የምትኖር አንዲት ደጋሚ ሴት ብትኖርና ከዕለታት አንድ ቀን ይህች ሴት ወደቤቴ ምግብ ሰርታ በመምጣት ብትሰጠኝ፡- ምናልባት በምግቡ ላይ ድግምት ሰርታበት ይሆናል ብዬ በመስጋት ባልቀበላት ይህ ፍርሐቴ ሽርክ አይሰኝም፡፡ ምክንያቱም ድግምት (ሲሕር) በዓለማችን ውስጥ ያለ ተግባር በመሆኑና አፈጻጸሙም የሚታይ (በምግብ፣በጸጉር፣በልብስ) በመሆኑ ነው፡፡ ከገይብ ጋር ግኑኝነት የለውም፡፡ እናም ፍጡርን በሩቅ መፍራት አይገባም፡፡ ጌታ አላህ ግን በሩቁ የሚገዛን ተቆጣጣሪያችን ስለሆነ፡ እንያንዳንዷንም እንቅስቃሴያችንን የሚመለከት በመሆኑ ልንፈራው ይገባል፡፡
ለ. ያልተገደበ መሆኑ፡- ሌላው ሁለተኛው ምክንያት አንድ ሙስሊም አላህን የሚፈራው ከሱ ውጪ ሌላ መሸሻ ስለሌለው ነው፡፡ አላህ እኛን በጉዳት ቢፈልገን ከሱ ቅጣት ሊያስጥለን የሚችል ሌላ ኃይል እንደሌለ በማመን ነው የምንፈራው፡፡ ቅድም የተጠቀሱት የፍጡራን ፍርሐት ግን ከነሱ እስክንሸሽ ብቻ ነው፡፡ እኔን ለመምታት ሲያባረኝ የነበረው የአንድ ሰፈር ዱርዬ አሯሩጦ አሯሩጦኝ ልክ ሰፈሬ ስደርስ ፍርሐቴ ይወገድና ፊቴን ወደሱ በማዞር፡- ና ወንድ ከሆንክ አሁን ተጠጋኝ! እለዋለሁ፡፡ ምንም አቅሜ እሱን መቋቋም ባይችልም ሊያግዙልኝ የሚችሉ የሰፈር ጓዶች አሉኝና፡፡ አውሬ ፈርቼ ብሮጥም ወይ ተደብቄ ወይንም ዘልዬ ወደ ሰው ቤት በመግባት ማምለጥ እንደምችል ውስጤ ያምናል፡፡ ይህ አይነቱ ፍርሐት በምክንያት የተገደበ ፍርሐት ይባላል፡፡ አላህን መፍራት ግን ከሱ ውጪ ማንም ከቁጣው ሊያተርፈን እንደማይችል በማመን ስለሆነ ዒባዳህ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ሃሳብ ደግሞ ተከታዩን ማስረጃዎች እንመልከት፡-
” ﻭَﺇِﻥْ ﻳَﻤْﺴَﺴْﻚَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻀُﺮٍّ ﻓَﻠَﺎ ﻛَﺎﺷِﻒَ ﻟَﻪُ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﻭَﺇِﻥْ ﻳَﻤْﺴَﺴْﻚَ ﺑِﺨَﻴْﺮٍ ﻓَﻬُﻮَ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮٌ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﻧﻌﺎﻡ 17
“አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡” (ሱረቱል አንዓም 17)፡፡
” ﻭَﺇِﻥْ ﻳَﻤْﺴَﺴْﻚَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻀُﺮٍّ ﻓَﻠَﺎ ﻛَﺎﺷِﻒَ ﻟَﻪُ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﻭَﺇِﻥْ ﻳُﺮِﺩْﻙَ ﺑِﺨَﻴْﺮٍ ﻓَﻠَﺎ ﺭَﺍﺩَّ ﻟِﻔَﻀْﻠِﻪِ ﻳُﺼِﻴﺐُ ﺑِﻪِ ﻣَﻦْ ﻳَﺸَﺎﺀُ ﻣِﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩِﻩِ ﻭَﻫُﻮَ ﺍﻟْﻐَﻔُﻮﺭُ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢُ ” ﺳﻮﺭﺓ ﻳﻮﻧﺲ 107
“አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም፡፡ በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፡፡ ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል፡፡ እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡” (ሱረቱ ዩኑስ 107)፡፡
” ﻗُﻞْ ﻣَﻦْ ﻳَﻜْﻠَﺆُﻛُﻢْ ﺑِﺎﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺑَﻞْ ﻫُﻢْ ﻋَﻦْ ﺫِﻛْﺮِ ﺭَﺑِّﻬِﻢْ ﻣُﻌْﺮِﺿُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ 42
“ከአልረሕማን (ቅጣት) በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው? በላቸው፤ በውነቱ እነሱ ከጌታቸው ግሣጼ (ከቁርአን) ዘንጊዎች ናቸው።” (ሱረቱል አንቢያእ 42)
…” ﻗُﻞْ ﺃَﻓَﺮَﺃَﻳْﺘُﻢْ ﻣَﺎ ﺗَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻥْ ﺃَﺭَﺍﺩَﻧِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻀُﺮٍّ ﻫَﻞْ ﻫُﻦَّ ﻛَﺎﺷِﻔَﺎﺕُ ﺿُﺮِّﻩِ ﺃَﻭْ ﺃَﺭَﺍﺩَﻧِﻲ ﺑِﺮَﺣْﻤَﺔٍ ﻫَﻞْ ﻫُﻦَّ ﻣُﻤْﺴِﻜَﺎﺕُ ﺭَﺣْﻤَﺘِﻪِ ﻗُﻞْ ﺣَﺴْﺒِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻳَﺘَﻮَﻛَّﻞُ ﺍﻟْﻤُﺘَﻮَﻛِّﻠُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺰﻣﺮ 38
“ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ነገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አዘጋጆች ናቸውን? በላቸው። አላህ በቂዬ ነው፤ በርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ፤ በል።” (ሱረቱ-ዙመር 38)፡፡
” ﻟَﻘَﺪْ ﻛَﻔَﺮَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻫُﻮَ ﺍﻟْﻤَﺴِﻴﺢُ ﺍﺑْﻦُ ﻣَﺮْﻳَﻢَ ﻗُﻞْ ﻓَﻤَﻦْ ﻳَﻤْﻠِﻚُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﺇِﻥْ ﺃَﺭَﺍﺩَ ﺃَﻥْ ﻳُﻬْﻠِﻚَ ﺍﻟْﻤَﺴِﻴﺢَ ﺍﺑْﻦَ ﻣَﺮْﻳَﻢَ ﻭَﺃُﻣَّﻪُ ﻭَﻣَﻦْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ “… ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ 17
“እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ፣ በእርግጥ ካዱ፤ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው? በላቸው።” (ሱረቱል ማኢዳህ 17)፡፡
እነዚህ አምስት ቅዱስ ጥቅሶች በመላ ለኛ የሚያስተላልፉት መልእክት፡- አላህ ባሮቹን በጥሩም ይሁን በመጥፎ ከፈለጋቸው፡ ያ እንዳይሆን ሊከላከል የሚችል አንድም ኃይል አለመኖሩን ነው፡፡ ፍጡራን እኛን በጉዳት ቢፈልጉን እራስን በመከላከል፣ ሮጦ በማምለጥ ወይም የተሻለ ኃይል ያለውን ሰው ለእርዳታ በመጥራት መከላከል ይቻላል፡፡ ከዛ በበለጠ መልኩ ደግሞ ወደ አላህ በመጠጋት ከሁሉም ነገር መትረፍ ይቻላል፡፡ ጌታ አላህም እንዲህ ይለናል፡-
” ﻗُﻞْ ﻣَﻦْ ﻳُﻨَﺠِّﻴﻜُﻢْ ﻣِﻦْ ﻇُﻠُﻤَﺎﺕِ ﺍﻟْﺒَﺮِّ ﻭَﺍﻟْﺒَﺤْﺮِ ﺗَﺪْﻋُﻮﻧَﻪُ ﺗَﻀَﺮُّﻋًﺎ ﻭَﺧُﻔْﻴَﺔً ﻟَﺌِﻦْ ﺃَﻧْﺠَﺎﻧَﺎ ﻣِﻦْ ﻫَﺬِﻩِ ﻟَﻨَﻜُﻮﻧَﻦَّ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺸَّﺎﻛِﺮِﻳﻦَ ‏( 63 ‏) ﻗُﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻳُﻨَﺠِّﻴﻜُﻢْ ﻣِﻨْﻬَﺎ ﻭَﻣِﻦْ ﻛُﻞِّ ﻛَﺮْﺏٍ ﺛُﻢَّ ﺃَﻧْﺘُﻢْ ﺗُﺸْﺮِﻛُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﻧﻌﺎﻡ 63-64
“ከየብስና ከባሕር ጨለማዎች በግልጽና በምስጢር የምትጠሩት ስትኾኑ «ከነዚህ ቢያድነን በእርግጥ ከአመስጋኞች እንኾናለን (ስትሉ) የሚያድናችሁ ማነው» በላቸው፡፡አላህ ከሷና ከጭንቅም ሁሉ ያድናችኋል፡፡ ከዚያም እናንተ ታጋራላችሁ በላቸው፡፡” (ሱረቱል አንዓም 63-64)፡፡
በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ፡- አንድን ነገር ስትፈራው ከሱ ትሸሻለህ፡ አላህን ስትፈራው ግን ወደሱ ትጠጋለህ፡- “ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለናንተ ከርሱ ግልፅ አስጠንቃቂ ነኝና (በላቸው)።” (ሱረቱ-ዛሪያት 50)፡፡
ለፍጡራን የሚኖረው ፍርሐት ገደብ ያለውና ልንከላከለው የምንችል መሆኑን በማመን ከሆነ ዒባዳ አይሆንብንም ማለት ነው፡፡ አለዚያ ከእንትና እጅ ሊያስጥለኝ የሚችል የለም፣ እሱ ከዛተብኝ በቃ አለቀልኝ፣ መትረፌንም እንጃ አይነት ፍርሐት የምናሳድር ከሆነ ሺርክ ውስጥ እንወድቃለን ማለት ነው፡፡ ያለ አላህ ፈቃድ ባንተ ላይ ፍጡር ምንም አይነት ጉዳት ሊያደርሱብህ እንደማይችል ማወቅ ከፈለክ ተከታዩን ሃዲስ አስተውል፡-
ﻋﻦ ﺑﻦ ﻋﺒﺎﺱ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ﻗﺎﻝ ﻛﻨﺖ ﺧﻠﻒ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭ ﺳﻠﻢ ﻳﻮﻣﺎ ﻓﻘﺎﻝ ﻟﻲ ” -: ﻳﺎ ﻏﻼﻡ ﺇﻧﻲ ﺃﻋﻠﻤﻚ ﻛﻠﻤﺎﺕ ﺍﺣﻔﻆ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺤﻔﻈﻚ ﺍﺣﻔﻆ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﺠﺪﻩ ﺗﺠﺎﻫﻚ ﺇﺫﺍ ﺳﺄﻟﺖ ﻓﺎﺳﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺇﺫﺍ ﺍﺳﺘﻌﻨﺖ ﻓﺎﺳﺘﻌﻦ ﺑﺎﻟﻠﻪ ﻭﺍﻋﻠﻢ ﺃﻥ ﺍﻷﻣﺔ ﻟﻮ ﺍﺟﺘﻤﻌﺖ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﻳﻨﻔﻌﻮﻙ ﺑﺸﻲﺀ ﻟﻢ ﻳﻨﻔﻌﻮﻙ ﺇﻻ ﺑﺸﻲﺀ ﻗﺪ ﻛﺘﺒﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﻟﻚ ﺇﻥ ﺍﺟﺘﻤﻌﻮﺍ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﻳﻀﺮﻭﻙ ﺑﺸﻲﺀ ﻟﻢ ﻳﻀﺮﻭﻙ ﺇﻻ ﺑﺸﻲﺀ ﻗﺪ ﻛﺘﺒﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻚ ﺭﻓﻌﺖ ﺍﻷﻗﻼﻡ ﻭﺟﻔﺖ ﺍﻟﺼﺤﻒ ” ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﻗﺎﻝ ﺣﺪﻳﺚ ﺣﺴﻦ ﺻﺤﻴﺢ .
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- “ከአላህ መልክተኛ ኋላ ሁኜ እያለ እንዲህ አሉኝ፡- አንተ ልጅ ሆይ! እኔ እነዚህን ቃላት አስተምርሃለሁ፡፡አላህን (ህጉን) ጠብቅ ይጠብቅሃልና፣ አላህን (ህጉን) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህና፣ ስትለምን አላህን ብቻ ለምን፣ እገዛን ስትሻ በአላህ ብቻ ታገዝ፣ ህዝቦች አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ አላህ የጻፈልህን ካልሆነ በስተቀር በምንም ነገር ሊጠቅሙህ እንደማይችሉ እወቅ፡፡ አንተን ለመጉዳትም ቢሰባሰቡ አላህ የጻፈብህን ካልሆነ በስተቀር በምንም ነገር ሊጎዱህ እንደማይችሉ እወቅ፡፡” (ቲርሚዚይ 2516)፡፡
ሐ. ዘውታሪ መሆኑ፡- ሌላው ሶስተኛው መለያ በአንድ ሙስሊም ልብ ውስጥ አላህን መፍራት በግዜና በቦታ የተገደበ አይደለም፡፡ የሆነ ቅጣት ሲመጣ አደጋ ሲከሰት ብቻ አይደለም አላህን የሚፈራው፡፡ ሁሌም የትም ስፍራ ቢሆን አላህን ከመፍራት ልቡ መወገድ የለበትም፡፡ በሃሳቡ፣ በንግግሩ፣ በስራውና በሁኔታዎቹ በጠቅላላ አላህን ፈሪ ነው፡፡ በመኖሪያው ሰፈር ሆነም በሌላ ሀገር አላህን ፈሪ እንዲሆን መልክተኛው እንዲህ ሲሉ ይመክሩታል፡-
” ﺍﺗّﻖ ﺍﻟﻠﻪَ ﺣﻴﺚ ﻣﺎ ﻛﻨﺖ ، ﻭﺃﺗﺒﻊ ﺍﻟﺴﻴﺌﺔ ﺍﻟﺤﺴﻨﺔَ ﺗَﻤْﺤﻬﺎ ، ﻭﺧﺎﻟﻖ ﺍﻟﻨﺎﺱَ ﺑﺨُﻠُﻖٍ ﺣَﺴَﻦ ” ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ 1987
“አላህን የትም ስፍራ ሁነህ ፍራው፡፡ መጥፎ ነገር ስትሰራ መልካምን ስራ ወዲያው አስከትል ታጠፋልሃለችና፡፡ ሰዎችንም በጥሩ ስነ-ምግባር ቅረባቸው” (ሶሒሕ ቲርሚዚይ 1987)፡፡
ፍጡራንን የምትፈራው ግን ፊት ለፊት ስታገኛቸው ብቻ ነው፡፡ አውሬውም ሆነ ሽፍታው በሌሉበት ስፍራ እነሱን አስበህ አትፈራቸውም እንደውም አታስታውሳቸውም፡፡ ያንተ ፍርሐት የነበረው በወቅቱ የተገናኛችሁ ሰዓት ብቻ ነበርና፡፡ ስለዚህ ይህ ዒባዳን ለፍጡር አሳልፎ መስጠት አይባልም ወላሁ አዕለም፡፡ ለናሙና ያክል እነዚህን ሶስት መለያዎች ካየናቸው እኛም ሁሌም አላህን ፈሪዎች ሁነን መኖር አለብን፡-
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺍﺗَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺣَﻖَّ ﺗُﻘَﺎﺗِﻪِ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻤُﻮﺗُﻦَّ ﺇِﻟَّﺎ ﻭَﺃَﻧْﺘُﻢْ ﻣُﺴْﻠِﻤُﻮﻥَ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ 102
“እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢዉን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፤ እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ።” (ሱረቱ አለ ዒምራን 102)
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﺍﺗَّﻘُﻮﺍ ﺭَﺑَّﻜُﻢُ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻘَﻜُﻢْ ﻣِﻦْ ﻧَﻔْﺲٍ ﻭَﺍﺣِﺪَﺓٍ “… ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ 1
“እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን… ጌታችሁን ፍሩ።” (ሱረቱ-ኒሳእ 1)
” ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺍﺗَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻗُﻮﻟُﻮﺍ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺳَﺪِﻳﺪًﺍ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻷﺣﺰﺍﺏ 70
“እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ ትክክለኛውንም ንግግር ተናገሩ።” (ሱረቱል አሕዛብ 70)፡፡