የነብያችን “ﷺ” የመጨረሻ (የመሰናበቻ) ንግግር !!

ሼር ያድርጉ
426 Views

(አቡ ዩስራ)

“ሰዎች ሆይ !

ከዚህ ዓመት ብሁዋላ በመካከላችሁ እንደገና ለመገኘት መብቃቴን አላውቅምና ልብ ብሎ የሚያዳምጥ ጆሮ አዉሱኝ።ዛሬ የምናግራችሁን ቁም ነገር በጥሞና አድምጡ።በዕለቱ ከመካከላችሁ ለመገኘት ዕድል ላልገጠማቸው መልክቴን አድርሱ።

ሰዎች ሆይ!

የዛሬው ወር፣የዛሬው ቀን፣ይህች ከተማ የተቀደሱና የተከበሩ መሆናቸውን የምታውቁትን ያህል የእያንዳንዱን ሙስሊም ሕይዎትና ንብረት በክብር እንድትይዙ አደራ ተጥሎባችሁዋል።በእጆቻችሁ የሚገኙ የ አደራ እቃዎች ለባለቤቶቻቸው መልሱ።ማንም ሰው እንዳያጠቃቹ በማንም ሰው ላይ ጥቃት አታድርሱ።ያለምንም ጥርጥር ፈጣሪያችሁ ፊት እንደምትቀርቡ አስታዉሱ።እርሱም ተግባራችሁን ይመዝናል።አራጣ እንዳትበሉ አላህ ከልክሎዋቺሁዋል።ስለዚህ ለመክፈል ቃል የገባችሁትን የብድር ወለድ መክፈል ከእንግዲህ እርም ተደርጎባችሁዋል።ሃይማኖታችሁን ለመንከባከብ ከሰይጣን ተጠንቀቁ።በትልልቅ ጉዳዮች እናንተን አሳስቶ በዚህች ምድር ላይ (መካ)አዘቅት ዉስጥ ለመጣል በሚያደርጋው ሙከራ ተስፋ ስለቆረጠ #በጥቃቅን ጉዳዮች ሰይጣንን ተከታዮች እንዳትሆኑ ነቅታችሁ ጠብቁ።

ሰዎች ሆይ!

በሴቶቻችሁ ላይ የተወሰኑ መብት ያላችሁ መሆኑ እርግጥ ነው።ነገር ግን እነሱም በናንተ ላይ መብት አላቸው።በናንተ ቁጥጥር ስር እስካሉ ድረስ የመመገብ፣የማልበስና በርህራሄ የመያዝ ግዴታ ይኖርባችሁዋል።ሴቶቻችሁ የኑሮ ጘደኞቻችሁና የቅርብ ደጋፊዎቻችሁ በመሆናቸው በርህራሄ አግባብ ባለው መልኩ ተንከባከቡዋቸው። እናንተ ከማትፈልጉት ሰው ጋር ጓደኝነት እንዳይመሰርቱ ቤታችሁ በጭራሽ እንዳይደፈር ማድረግ የናንተ መብት ነው።

ሰዎች ሆይ!

በሚገባ አድምጡ፡አላህን ተገዙ። በቀን አምስት ጊዜ ሶላታችሁን ስገዱ።የረመዳንን ወር ፁሙ።ከሀብታችሁም ዘካን ስጡለት።እንዲሁም ከተቻላችሁ ሃጅ አድርጉ።እያንድንዱ ሙስሊም ለሌላው ሙስሊም ወንድም መሆኑን ታውቃላችሁ።ሁላችሁም እኩል ናችሁ።ማንም ሰው ካሌላው የሚበልጥበት መንገድ የለም፣አላህን በመፍራት እና በጥሩ ምግባሩ እና ተግባሩ ቢሆን እንጂ!!!አስታዉሱ! አንድ ቀን በአላህ ፊት ቀርባችሁ ለሰራችሁት ስራ ትጠየቃላችሁ።ስለዚህ ተጠንቀቁ።እኔ ካለፍኩ ብሁዋላ አላህ ከመፍራት ጎዳና እንዳታፈነግጡ።

ሰዎች ሆይ!

ከእኔ በሁዋላ አዲስ ነቢይ ወይም መልክተኛ አይመጣም።አዲስ እምነትም አይወለድም።በሚገባ ተመራመሩ።

Ref:-

1- Al-Bukhari, Hadith 1623, 1626, 6361

2- Sahih of Imam Muslim in Hadith number 98.

3- Imam al-Tirmidhi in Hadith nos. 1628, 2046, 2085.

4- Imam Ahmed bin Hanbal, Hadith no. 19774

Shortlink http://q.gs/Ewi6f