የተታለለው ነብይ

ሼር ያድርጉ
243 Views

“ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።”
(ኦሪት ዘዳግም 18: 22)

1- እንዴት አንድ የተመረጠ የእግዚአብሄር ነብይ በድፍረት የማይሆን ትንቢት ይናገራል?

2- ከዛ በኃላስ ያ ሰው ነብይ ሁኖ ይቀጥላል ወይንስ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ስልጣን ይቀማል?

3- ስልጣኑ የሚቀጥል ከሆነ ሀሠተኛ ሰውን እንዴት እግዚአብሄር ይቀባል? ሰውስ ውሸታምነቱን አይቷልና ባይቀበለው ጥፋቱ የማነው?

4- ስልጣኑ የማይቀጥል ከሆነ እግዚአብሄር ልክ እንደምድራዊ ነገስታት ሲሾም የሚሾመውን ሰው ማንነት ቀድሞ አያውቀውም ወይ? ከሾመ በኃላ የሚያባርርስ ምን አይነት ሁሉን አዋቂ አምላክ ነው?

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)