የማቴዎስ ወንጌል እና ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 7

ሼር ያድርጉ
365 Views
ኢሊያህ ማህሙድ በኣላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ዘመን በተላኩ የዓላህ የመጨረሻው ነብይ ሙሐመድ ላይ ሰላም ይሁን ብለን እንቀጥላለን፡፡ ወዳጄ ዛሬ ማወጋዎ በማቴዎስ ወንጌል ዙሪያ ሲኾን፣ከወንጌሉ ጸሐፊ ማንነት ተነስተን እስከ ትንቢተ ኢሳያስ እንዘልቃለን፡፡ ዳኢረቱል መዓሪፍ በሚል በአራት ስመ-ጥር ቄሶች የተዘጋጀ የአረብኛ መጽሀፍ ቅዱስ ድንቡሽቃ (ሶፍት ዌር) እንዲህ ይላል፡- يأتى إنجيل متى أو الإنجيل بحسب رواية متى أول الأناجيل القانونية طبقاً للترتيب التقليدى وإن لم يكن فى جميع الحالات، وينسب هذا الإنجيل- حسب شهادة الكنيسة الأولى بالإجماع- إلى متى الرسول رغم أن عنوانه لا يدل بالضرورة على مصدره المباشر ስንገረድፈው፡- “ የማቴዎስ ወይም ማቴዎስ የዘገበው ወንጌል ከኹሉም መስፈርቶች አንጻር ባይኾንም በተለምዶ ካለው አሰዳደር አኳያ የቀኖናው የመጀመሪያ ወንጌል ኾኖ ይገኛል፡፡ የወንጌሉ ስም በቀጥታ ጸሐፊውን ≠ባያመላክትም≠ ከመጀመሪያዎቹ አብያተ-ክረስትያናት ህሳቦ አኳያ ወደ ሐዋርያው ማቴዎስ ተጠግቶ እናገኘዋለን” ወዳጄ የወንጌሉ ስም ጸሐፊውን በቀጥታ አያመላክትም የሚለውን ሃስብ ያስምሩበት፡፡ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ቁጥር 9 ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፡-
“ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ≠ማቴዎስ የሚባል≠ አንድ ሰው አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።” ኃይለ ቃል ያደረግነው “ማቴዎስ የሚባል” የሚለውን ሐረግ ልብ ካልን ኣንድ ሰው ስለማቴዎስ እየጻፈ እንደነበር በግልጽ እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ ዛሬ ጁምዓ ሰይድ ያሲን መስጂድ የሰገደ ሰው፣ሰይድ ያሲን መስጂድ ሼኽ መሐመድ ሐሚዲን ≠አሰገዱን≠ በማለት ራሱን የስግደቱ ተካፋይ አድርጎ ይናገራል እንጂ፣ ራሱ አብሮ ሰግዶ እያለ ≠…አሰገዷቸው≠ ብሎ አይናገርም፡፡ አይ ይሄ የማቴዎስ የራሱ አነጋገር ብሒል ነው የሚል ጥራዝ ነጠቅ ሙግት ከቀረበ ደግሞ፣ በጄ! ማቴዎስ ራሱ ነው የሚለውን ሙግት እንቀበልና እንዲህ ብለን እንጠይቅ፡- እስከ ምዕራፍ ዘጠኝ ድረስ ያለውን ወሬ ማቴዎስ ከየት አምጥቶ ነው ወንጌሉ ውስጥ የከተበው ኢየሱስ እርሱን ያገኘው ምዕራፍ ዘጠኝ ቁጥር ዘጠኝ ላይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ስምንት ምዕራፎች ከስምንት ጥቅሶች አለፈዋል፤ እነዚህን ምዕራፎች ከየት አምጥቶ ጻፋቸው እንደተለመደው “በመንፈስ ተመርቶ” ከተባለ እስኪ ትንሽ ወደ ኋላ እንደርደርና በመንፈስ የተባለውን እንዳሰው፡፡ [ማቴዎስ 1/ 1-16] “የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤” ወዳጄ “ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ” የሚለውን ዓ/ነገር ዘፍ/38/12 ላይ ገብተው ሲያነቡ ይሁዳ በዝሙት ፋሬስን እንደወለደ ይረዳሉ፡፡ እንግዲህ “ፋሬስ” ህጋዊ ልጅ እንዳልሆነ ልብ ይሏል!!!ይቀጥልና ከፋሬስ ሰልሞን(ሰለሞን እንዳይመስሎ) አምስተኛ የልጅ ልጅ ሆኖ ተወለደ፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ “ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ” ወዳጄ እዚህ ጋር አሁንም ቆም ይበሉ! በአማርኛ ትርጉሞችና በኪንግ ጄምስ ቨረዝን “ራኬብ” የሚል ስም ተቀምጧል፡፡ ለምን መሰሎ? በ New International Version“Salmon the father of Boaz, whose mother was Rahab” “ሰልሞን ከረዓብ ቦኤዝን ወለደ” የሚል ነበር የሰፈረው፡፡ ግን “ረዓብ” በመጽሀፉ በተለያየ ቦታ እንደተጠቀሰችው ጋለሞታ ነበረች፡፡ ለምሳሌ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 2/1፣6/25 ዕብራ 11/31፣ የያዕቆብ መልእክት 2/25 ለአብነት መመልከት ይቻላል፡፡ ይህች ሴት ጋለሞታ ስለነበረች ከሰልሞን ሚስትነት ተሰረዘች፡፡ ወደ አረብኛው መጽሀፍ-ቅዱስ ስንገባ እንዲህ ይለናል “وسلمون ولد بوغز من راحب`”ሰልሞን ከራሂብ ቦጌዝን ወለደ” በግሪኩም “” “ ረሃብ” ይላታል፡፡ ወዳጄ አስቀደምን ለአብነት የጠቀስናቸውን መጽሀፎች ውስጥ ገብተው ቢመረምሩ በአረብኛውም በግሪኩም “ራሂብ” ወይም “ረሃብ” የሚል ስም ነው የሰፈረው፡፡ የበለጠ ለማስረገጥ “ዳኢረቱል መዓሪፍ አልኪታቢያ” “ራሂብ” ስለሚለው ስም ስንጠይቀው፡-
وكل هذا يدعونا إلى القول بأن راحاب سفر يشوع هى نفسها راحاب التى يورد اسمها متى البشير فى سلسلة نسب الرب يسوع
“መረጃዎች በአጠቃላይ በትንቢተ -ሆሴእ- የተጠቀሰችው “ራሂብ” ወንጌላዊው ማቴዎስ ስለ ጌታ እየሱስ የዘር ሃረግ ሲጠቀስ ያወሳት ሴት ራሷ ስለመሆኗ እንድንቀበል ያስገድዱናል፡፡“ ይላል፡፡ ወዳጄ በማቴዎስ ወንጌል የተዘረዘረውን የኢየሱስ የዘር ሐረግ በሙሉ ማን ምንድር ነው እያሉ በመርመር ሲያጠኑ የኢየሱስን ሐረግ ለማጋነን “የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ..” በማለት የተጠቀሰው ዳዊት ራሱ የሰው ሚስት ቀምቶ “ጠቢቡ ሰለሞንን” እንደወለደ ይረዳሉ፡፡ ይህን ኹሉ የዝሙት ቅሌት የተሸከሙ ግለሰቦች የኢየሱስ አባቶች እንደኾኑ ተደርጎ መጻፉን ዊሊያም ባርክሌይ የመጽሀፍ ቅዱስ ሊቁ commentaries on the new testament በሚል መጽሐፉ ገጽ 30 ላይ እንዲህ በማለት ይጠይቃል፡- “ማቴዎስ እነዚህ ስሞች ካላቸው የታሪክ ቅሌትና ነውር ጋር የእየሱስ የዘር ሃረግ ውስጥ እንዲገቡ መፍቀዱ ምን አነሳስቶት ይሆን ” መቼም ኢየሱስ ኣባት እንደሌለው ኹላችንም እናውቃልን፡፡ እናምናለንም፡፡ ነገር ግን ይህ ኹሉ የዝሙት ቅሌታ ላለበት ሰው “ቅድስቲቷና በስጋም በሃሳብም ድንግል” የኾነቸው እናቱ መታጨቷ ኦሪት ዘዳግም 23/2 “ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ” የሚለው ጥቅስ ሳይታወቅ ቀርቶ ነው ወይስ ለማቴዎስ የገለጠለት መንፈስ ራሱ…. ወዳጄ በማቴዎስ 1 ላይ የተዘረዘረውን የኢየሱስ የዘር ሐረግ ከሉቃስ 3/23 የዘር ሐረግ ዝርዝር ጋር እያስተያዩ ያንብቡት፡፡ ከዮሴፍ እሰከ አዳም ድረስ የስምና የኣባቶች ቁጥርም ልዩነት አለ፡፡ የትኛው ጸሐፊ ትክክለኛውን እንደነገረን በፍጹም መፍረድ አይቻልም፡፡ በዚህ ዙሪያ ልሂቃኑ ብዙ ለማለት ቢሞክሩም የኣንዱን ሃሳብ ሌላኛው እያፈረሰ መስማማት አልቻሉም፡፡ ማርከስ ጄ ቦርግና ጃን ዳሚኒክ ክሮሳን “ዘ ፈርስት ክሪስማስ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 95 ላይ እንዲህ ይላሉ፡- “Both genealogies are inventions to support Messianic claims“ ስንገረድፈው፡- “ኹለቱም የዘር ሐረጎች የሚጠበቀውን መሲህ ለማስረገጥ ≠የተፈጠሩ≠ ናቸው” ———–ይቀጥላል———–