የመጽሀፍ ቅዱስ ስህተቶች -2

ሼር ያድርጉ
321 Views
ካለፈው የቀጠለ – ዘፍጥረት በዘፍጥረት 1:27 እንደተገለፀው እግዚአብሄር የሰው ልጅን በአምሳሉ ፈጥሮታል፤ ነገር ግን በዘፍጥረት 3:22 እንደተገለፀው ” እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ #እንደ #አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤ “
(ኦሪት ዘፍጥረት 3:22) ⚠️ ጥያቄዎች የመጀመሪያው አንቀፅ እንደሚገልፀው አዳም መጀመሪያውኑ በእግዚአብሄር አምሳል መፈጠሩን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ፍሬዋን ከበላ በኃላ እንደ እግዚአብሄር እንደሆነ ይገልፃል.! 🤔 1- ታዲያ እንዲያ ከሆነ እግዚአብሄር በአምሳሉ ሲፈጥረው ክፉና ደጉን መለየት አይችልም ነበር? ክፉና ደግ የማይለይን ፍጡርስ ነው እግዚአብሄር አምሳሌ ሲለው የነበረው?
..
🤔 2- አዳም ፍሬዋን ባይበላ ኖሮ ልክ እንደ እንስሳ ክፉና ደግ የማንለይ ግዑዛን ሆነን እንቀር ነበር ማለት ነው? ታዲያ አዳም በጎ ሰራ እንጅ እንዴት አጠፋ ይባላል?

🤔 3- “ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” ሲልስ አዳም የመላዕክት ወይንም የአምላክን ስልጣን ያዘ ማለት ነው? ከፉና ደግ ማወቅ ብቻ እንደ እግዚአብሄር ያደርጋል?
…🤔 4- አዳምና ሔዋንስ ፍሬዋን ከመብላታቸው በፊት ክፉና ደጉን መለየት ይችሉ ነበር? መለየት የማይችሉ ከነበረ በማይችሉት ጉዳይ ለምን ተጠያቂ ይሆናሉ?