ዒሳ በአንደበቱ ነብይ ነኝ …

📝 ምጥን ምላሾች 📜

ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖችን “እየሱስ በአንደበቱ እኔ አምላክ ነኝ ያለበትን ቦታ አሳዩን” ብለን ስንጠይቃቸው በአፀፋው የሚያነሱት ቃል የነበረው

“አላህ (ሱወ) በተመሳሳይ ይህንን ቃል ያለበትን ቦታ አሳዩን” የሚል ነው፡፡

ይህንን አስመልክቶ ቁርዓንን መሠረት አድረገን ስናሳያቸው አመክንዬው እንደማያስኬድ ተረድተው አዲስ መንገድ ፈጥረዋል፤ እሱም “እናንተም ዒሳ (ዐሰ) ነብይ ነኝ ያለበትን አንድ አንቀፅ ከቁርዓን አሳዩን” አሉ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ኢሳ በአንደበቱ የተናገረበትን ከወንጌል እንድታሳዩን የጠየቅነው ወንጌል የእየሱስ ንግግር ስብስብ ስለሆነ ነው፤ ቁርዓን ግን ፍፁም የአላህ ቃል እንጅ የኢሳ ወይንም የ40 ፀሀፍት ጥምር ድርሰት አይደለም፡፡ ቁርዓን ውስጥ ኢሳ ለህዝቦቹ ባሪያና ነብይ እንደሆነ በሱረቱል መርየም የገለፀበት ንግግር ቀጥታ/Direct speech/ ሳይሆን ንግግሩን መጥቀስ/Quote/ ነው፡፡ ስለዚህም የኢሳን ቀጥታ ንግግር ቁርዓን ውስጥ መፈለግ አውሮፕላን ማረፊያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው፡፡ ቁርዓን ውስጥ የአምላካችን አላህ ቀጥታ ንግግር እንጅ የፀሀፍት የግል ትርክት አይገኝም አበው እንዲሉ ጉዳዩ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነው፡፡

ሼር ያድርጉ