ወዳጀ

ሼር ያድርጉ
353 Views
ኢሊያህ ማህሙድ ለምትሰራው መልካም ስራ ቄጤማ እንዲጎዘጎዝልህ ምትጠብቅ ከሆነ ወይም ሰው ኹሉ ሐሳብህን እንዲጋራ ምትከጅል ከሆነ በሥራህ ከአላህ ሰለመከጀልህ ያጠራጥራል፠ባንተ መገኘት ሥራዎች አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚሉ በመቅረትህ ደግሞ ዝቅ እንደሚሉ ወይም እንደሚጠፉ ካሰብክ አሁንም ኢኽላሥህን መርምር፠ኹላችንም ከፊት ለፊት የሚጠብቀን የትየለሌ የቤት ሥራዎች አሉብን፠ከፈጸምነው ለቀጣዩ ትውልድ ይቀልለታል፠ካልኾነ በራሱ እዳ ላይ እዳ ደርበንለት እናልፋል፠ትውልድም እየወቀሰን ይኖራል፠ ወዳጄ ምትሠራው መልካም ሥራ ለነፍሥህ እንጂ ለማን ኾኖ የሰዎች ጉዳይ ያስጨንቅሃል? እውነት ነው ሰዎች ሐሳብሕን ፈጽሞ በተቃራኒው ሲረዱ ግራ ትጋባ ይሆናል፠ግን ወዳጄ አንተ በተቻለህ አቅም ሰዎችን ቀድመህ ሮጠሕ ዞረህ ለመጣራት ሞክር እንጂ ከሚያዘግሙት ጋር ማዝገም ብሎም ከቆሙት ጋር መቆም ባሕሪሕ አይሁን፠ ምናልባት ጥቂቶች ገንቢ ኾነው ብዙዎች አፍራሽ መሆናቸው መገንባት የተያዘው ግንብ ከፍ ብሎ እንዲታይ ባያደርገውም ወዳጄ አንተ ብቻ ሚጠበቅብሕን አድርግ ለግንቡ የራሱ ቀን አለው፠