ክርስትናና ክርስቲያን ቀጣይ ዲስኩር

ሼር ያድርጉ
323 Views
በኢሊያህ ማህሙድ بسم الله الرحمن الرحيم በአላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነውእንጀምርና እንቀጥላለን፡፡ ወዳጄ እንዴት ከረመዋል? ወትሮው የጀመርነው ያልተቋጨ ጉዳይ እንዳለ ድንገት ላብቶፔን (ላብጠቤንም ማለት ይቻላል) ሳነሳ ትዝ አለኝ፡፡ ስላለኝም መተየቤን ጀምርኩ፡፡ ወዳጄ ዛሬ ትንሽ አዲስና አዳዲስ የሚመስሉ ጉዳዮችን ላወጋዎ መልካም መስሎ ታይቶኛል እርሶስ? ባይመስሎትም ግድ የለም እኔ ስለመሰለኝና ስለምጽፍ፡፡ግን እባኮ ከማንበብ እንዳይሰንፉ፡፡ ምን ከማንበብ ብቻ ዋቢ ያደርግኋቸውንም መረጃዎችለመቃረም አይፍሩ፡፡አመስግኖታለሁ! ፡፡ ባለፈው ባላጠናቀቅነው ጽኁፍ መጨረሻ የኢሳ (ዐ.ሰ) ስማ ዙሪያ የተወሰነ መዘውሮችን ዞረን እንደከመን ቆም ብለን ነበር፡፡ የኢየሱስ ትክክለኛ ስያሜ ማን ነው በሚለው ላይ በሌላ ጽኁፍ እንመለሳለን ዛሬ ግን አስቀድሜ እንዳወጋሆ ክርስቲያን የሚለው ቃል የግሪክ አፍ እንጂ የኢየሱስ (ዐ.ሰ) አፍ እንዳልነበር ስላልነበረም ምድር ላይ ሲንቀሳቀስ ወደዚህ ሀይማኖት እንዳልተጣራ ደቀመዛሙርቱም ይሕን ሀይማኖታዊ ስያሜ ተጠቅመው ሰዎችን እንዳላጠመቁ የተረዱኝ ይመስለኛል፡፡ ካልተረዱኝም አሁኑኑ ይረዱኝ፡፡ ለዚህና ለመስል ወጎቻችን ዊኪፒዲያንም እንደ ማጣቀሻ ወሰደናል፡፡እስኪ ደግሞ ወደ መጽሀፉ እንዝለቅና ይሕ ክርስቲያን የሚለው ቃል ከየት መጣ እንበለው፡-) የሀዋርያት ስራ 11/26 … (ሀዋርያት) በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ። ልብ ይብሉ ወዳጄ ደቀ መዛሙርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንጻኪያ ክርስቲያን ተባሉ ሲል መጽኀፉ የርሶ ጥያቄ መሆን ያለበት ”በፊትስ ማን ነበር መጠሪያቸው?” ይሁን፡፡ ለዚህ ተገቢ ጥያቄዎ ምናልባት ከክርስቲያን ወጎኖ “ እንዴ በፊትም እኮ ስማቸው ክርስቲያን ነበር… ግን አጋጣሚ ሆነና በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ” የሚል ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ አይነት መልስ ብጤ ምናምን ሊሰሙ ይችሉ ይሆናል፡፡ እንደ ወትሮ እርሶም አሪፍነቶን ተጠቅመው “ ማስረጃ” ከማለቶ በፊት “ መጽሀፉ ራሱ መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉይል የለ እንዴ? ብለው ይጠይቁ፡፡ “አይ ያ ማለት እኮ…” የሚል ሌላ አንጃ ግራንጃ ከገጠሞ፣ “መጀመሪያ” ማለት ምን ማለት ነው ብለው ደግመው ምሁራዊ ጥያቄዎን ያስከትሉ፡፡ እንግሊዘኛውንም ይþውሎ እንዲህ ይላል ብለው ያስነብቡ And the disciples were called Christians first in Antioch በቃበርግጠኛነት ተከራካሪዎ በበቃኝ ይወጣል ካልሆነም ይዘረራል፡፡አሸናፊነቶን የበለጠ ለማስረገጥ ክርስቲያን የሚለው ቃል በአረብኛው መጽኀፍ ቅዱስ እንደማይገኝም ያንብቡልት እንዲህ ብለው ፡-
سنة كاملة وعلما جمعا غفيرا ودعي التلاميذ مسيحين في انطاكية اولافحدث انهما اجتمعا في الكنيسة
ልብ ይበሉ ወዳጄ ጥያቄያችን ለምን በተለያየ ቋንቋ የተለያየ ስያሜ ኖረ አይደለም፡፡ ግና ክርስቲያን የሚለው መጠሪያ ሰብአዊ ነው ስለሆነም በግሪኩና ከሱ በቀጥታ ቃሉን የወሰዱ ቋንቋዎች “ክርስቲያን” የሚለውን ቃል ይጠቀማሉ አረብኛው ደግሞ “መሲሂይን” የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡ ለምን? ከተባለ አሁንም መልሱ ስያሜው ሰማያዊና መለኮታዊ ስላልሆነ ነው፡፡ ትዝ ካሎ ወዳጄ ስለኢስላም አስቀድመን ስናወራ የትም ሀገር በየትኛውም ጊዜና ሰዓት እምነቱ “ኢስላም” ይባላል ምክንያቱም ስያሜውም ከፈጣሪ አላህ የተሰጠ ስለሆነ ተመጣጣኝ በሆነ ቃል እንኳ መቀየር አይቻልምና፡፡
ሁለተኛ ምሁራዊ ጥያቄዎ “ ይህን ክርስቲያን የሚለውን ስያሜ ማነው ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው?” የሚል ይሁን፡፡ አደራ ወዳጄ ለዚህ ጥያቄዎ ከተከራካሪዎ መልስ አይጠብቁ፡፡ በበቃኝ ወይም በዝረራ ወጥቷልና አይጨቅጭቁት፡፡ ስለሆነም እራሶ መልሱን ይስጡት፡፡ ይበሉም፡- “ ስያሜውማ ደቀመዛሙርቱ ራሳቸው ሲያስተምሩት የነበረው ህዝብ ሰጣቸው ፤ ስለሆነም ስያሜው ሰብአዊ እና ምድራዊ እንጂ መለኮታዊና ሰማያዊ አይደለም፡፡” አራት ነጥብ፡፡ ለዚህ ጠንካራ አምክንዮአዊ ማጠቃለያዎ ይህንንም ጥቅስ በላዩ ላይ ይከልሱበት፡፡
) የሀዋርያት ስራ 26/28
አግሪጳም ጳውሎስን። በጥቂት ክርስቲያን ልታደርገኝ ትወዳለህ አለው።
ወዳጄ ይህንን ጥቅስ ልብ ካሉ ንጉስ አግሪጳ የጳውሎስን ሰበካ ካዳመጠ በኋላ እንዲያው በቀላሉ ክርስቲያን ሊያደርገው መፈለጉን በመተቸት ሲያናግረው እናነባለን፡፡ አሁን በተራ ቁጥር አንድ ያስቀደምነው አምክንዮ ግልጽ ሆነሎ አይደለም ወዳጄ? እንዴታ ይሆናል እንጂ፡፡ ስለዚህ አሁንም እንዲህ ብለን ደግመን እናጠቃል “በቃ ክርስቲያን የሚለው ስያሜ ሰብአዊ ብቻ ነው፡፡” ሰብአዊ ከሆነ ዘንዳ እንደ ሌሎቹ እምነቶች ለምሳሌ ቡድሂዝም፣ ሂንዱኢዝም፣ሚዝሬይዝም ወዘተና አከተ ከጀማሪዎቹ ወይም ከተጀመሩበት አካባቢ አኳያ ስያሜያቸውን ማግኘታቸው የሚያስኮንን አይደለም፡፡ የሚገርመው ግን እነዚህን ስያሜዎች አንዳንድ ክርስቲያን ሰባኪያን ሲኮንኑ እንሰማለን፡፡ሰምተንም የራሷ እያረረባት የሌላውን እራሪ ብላ ትሳደባለች የሚለውን ያልተጻፈውን ተረት እንተረታለን፡፡ሶስተኛና ከመጨረሻ በፊት ያለው ጥቅሳችን እንዲህ ይነበባል፡-
 ) 1ኛ ወደ ጢማቴዎስ 3/6
በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።
ይህ መጽሀፍ የጳውሎስ መልዕክት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አስቀድመን ባየናቸው ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ የነበረበት የደቀመዛሙርቱ ስብስብ ክርስቲያን ተብሎ ተሰየመ፡፡ ቀጥሎ ጳውሎስ ብቻውን በአግሪጳ “ክርስቲያን” ተባለ፡፡ ይþውሎ እዚህ ጋር ደግሞ ጳውሎስ ራሱ ክርስቲያን የሚለውን ቃል ለሀይማኖት ስያሜነት ሲጠቀምበት እናነባለን፡፡ በትዕቢት የሚነፋውና በዲያብሎስ ፍርድ የሚወድቀው አዲስ ክርስቲያን ብቻ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ወዳጄ በዚህ ጥቅስ ላይ ወደ ኋላ የምናነሳው ነገር ይኖራል ለጊዜው እንዳለ እንቀበለው፡፡ የመጨረሻው ጥቅስ ሲተቀስ፡-
 ) 1 ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4/16
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር። ይሕንየጴጥሮስ መልእክት ስንፈታታው አንድ አማኝ እንደማንኛውም ክርስቲያን መከራን ቢቀበል፣ ክርስቲያን በመሆኑ ደስ ይበለው እንጂ አይፈር ማለት ይሆናል፡፡ እንግዲህ ወዳጄ እስከ አሁን በእጃችን የሚገኘውን መጸኀፍ በመግለጽ አወራን፡፡ እስቲ ወደ ጥንቱ የጠዋቱ መጽሀፍ እንወርወርና እውን እጅግ በጣም ጥንት የሚባሉት ቅጂዎች “ክርስቲያን” የሚለውን ቃል ይጠቀሙታል?ለዚህ መልስ ይሰጠን ዘንድ ይሕንን ድረ-ገጽ ጠቅ እናድርግ www.natzraya.org
በጣም የጥንት የሚባለው የአዲስ-ኪዳን የእጅ ጽኁፍ “ሲኔቲከስ” የሚባለው ሲሆን ከርሱ በመቀጠል “ቫቲካነስ” የሚባለው እንደሆነ ምሁራን በጅምላ ይስማማሉ፡፡ ይሁንና በነዚህ በሁለቱም መዛግብት “ክርስቲያን” የሚለው የግሪክ ቃል አይገኝም፡፡
በኋላ ላይ የተዘጋጁ ቅጂዎች ግን “Χρnστιαν” ¡_e+Á” የሚለውን ቃል“Χριστιαν” ክርስቲያን ወደ ሚል ለወጡት፡፡ ታዲያ እውነታው ያ ከሆነ ክርስቲያን የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ መቼ ተጻፈ?
The earliest extant Greek New Testament to explicitly contain the name “Christian” is the Codex Alexandrinus dated ca. 450 c.e… In fact, some lineages of Greek manuscripts (Minuscule 81) were still faithfully copying Chrestian up until 1044 c.e. የመጀመሪያው“ክርስቲያን” የሚለውን ቃል ግልጽ ባለ መልኩ የያዘው የግሪክ አዲስ-ኪዳን ኮዴክስ አሌክሳንድሪነስ የሚባለው ሲሆን የተጻፈበት ዘመንም 450 ክ.ዘ. (ዘመነ-ክርስቲያን) አካባቢ ነው… በርግጥ አንዳንድ የግሪክ መዛግብትንየተከተሉ እንደ ሚኒስኩል 81 አይነት ክሬስቲያን የሚለውን ቃል እስከ 1044 ክ.ዘ ድረስ በእምነት እየገለበጡ ኖረዋል፡፡
ልብ ይበሉ ወዳጄ እነዚህ ሁለት ቃላት “ክሬስቲያን” እና “ ክርስቲያን” በትርጉም ደረጃ የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን ትርጉሞቻቸውን ተከትለን ከመጽኀፉ በጠቀስናቸው ጥቅሶች ውስጥ ስናስገባቸው ትርጉማቸውን በትክክል መረዳት ብቻ ሳይሆን የትኛውስ ቃል አውዱን የጠበቀ ነው የሚለውንም በግልጽ ማየት እንችላለን፡፡ በመጀመሪያ “ክሬስቲያን” ምን ማለት ነው… “ክርስቲያንስ”??
“ክሬስቲያን” የሚለው “ክሬስቶስ” ከሚለው ግሪክኛ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም መልካም ስነ-ምግባር፣አስደሳች፣ የተሻለ፣ጠቃሚ፣ቸርእንደ ማለት ሲሆን “ክርስቲያን” የሚለው ቃል ደግሞ በአንጻሩ “ክርስቶስ” ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ሆኖ ትርጓሜውም የተቀባ እንደማለት ይሆናል፡፡
ወዳጄ አሁን ጥቅሶቹን እንደርድርና ቃላቱን በማስገባት የትኛው አውዱን እንደሚጠብቅ አብረን እናወዳድ፡፡
{) የሀዋርያት ስራ 11/26}
(በርናባስ)ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። (በቤተ ክርስቲያንም) (በደጋጎች ቤትም) አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ (ክርስቲያን) (መልካም ሰዎች) ተባሉ።
“For he [Barnabas] was a good [man], and full of the Holy Ghost and of faith: and much people was added unto the Lord. Then departed Barnabas to Tarsus, for to seek Saul: And when he had found him, he brought him unto Antioch. And it came to pass, that a whole year they assembled themselves with the church, and taught much people. And the disciples were called good [men] first in Antioch.” – KJV
{) የሀዋርያት ስራ 26/28}
አግሪጳም ጳውሎስን። በጥቂት (ክርስቲያን)(ቀና) ልታደርገኝ ትወዳለህ አለው።
“King Agrippa, believest thou the prophets? I know that thou believest. Then Agrippa said unto Paul, Almost thou persuadest me to begracious. …And when they were gone aside, they talked between themselves, saying, This man doeth nothing worthy of death or of bonds.” – KJV
{ ) 1ኛ ወደ ጢማቴዎስ 3/6}
በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።
Not a novice, lest being lifted up with pride he fall into the condemnation of the devil.
ወዳጄ እዚህ ጋር ፍሬን ይያዙልኝ፡፡ ለምን? ካሉኝ በአማርኛችን ክርስቲያን አይሁን የሚል ሀረግ ስናነብ በእንግሊዘኛው Not a novice የሚል እናነባለን፡፡ ትርጉሙም ያው አዲስ ጀማሪ፣ ተለዋጭ እንደማለት ነው፡፡ እስቲ የግሪኩን መጽኀፍ እዚህ ጋር ምን እንደሚል እንጠይቀው
μὴνεόφυτον, ἵναμὴτυφωθεὶςεἰςκρίμαἐμπέσῃτοῦδιαβόλου.
μὴ νεόφυτον ይþውሎ ወዳጄ የግሪከኛውም ቢሆን “ሜ ኒዮፉቶን” በሚል ቃል ነው የሚገልጸው ትርጓሜውም “አዲስ ገቢ( ተለዋጭ) አይሁን”እንደማለት ነው፡፡ ልብ ይበሉ ጎግል ውስጥ ገብተው ክርስቲያን የሚለው ቃል ስንት ጊዜ በመጽኀፍ ቅዱስ ተጠቅሷል ብለው ቢጠይቁ ይችኛዋን 1 ኛ ወደ ጢማቴዎስ ጥቅስ አያመጣሎትም፡፡ ምናልባት በአማርኛው ጎግል ውስጥ ሊኖር ይችላል ብለን ብንስቅስ፡፡
{ ) 1 ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4/16}
(ክርስቲያን) (መልካም ሰው) እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር። “But let none of you suffer as a murderer, or [as] a thief, or [as] an evildoer, or as a busybody in other men’s matters. Yet if [any man suffer] as a good [man], let him not be ashamed; but let him glorify God on this behalf.” – KJV
ተመለከቱ ወዳጄ ምን ያሕል የትርጉም ለውጥ እንዳለ! እኛ እንደ ሙስሊም የዚህ አይነት የቃላትና የሀረግ ልወጣዎች በክርስቲያኑ መጽሀፍ እንዳለ ቁርዐን ምስክር ሆኖ ይነግረናል፡፡ ግን ወዳጄ አሁን ትንሽ ድካም ብጤ ተስምቶኛል፡፡ እውነት እውነት እሎታለሁ እርሶ ብቻ ለማንበብ ያብቃዎ ብዙ ከዋዛ ጋር እስፕሪስ እያደረግን ምንደሰኩረው ቁም ነገር አለ፡፡ ቸር እንሰብት في امان الله