ክርስቲያን….ኢየሱስ

ሼር ያድርጉ
344 Views

ኢሊያህ ማህሙድ

በኣላህ ስም እጅግ ኣዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ዘመን ነብይ ኾነው በተላኩ የመጨረሻው ነብይ ሙሐመድ (ሠ) ላይ ሰላም ይኹን ብለን እንቀጥላለን፡፡
ለወትሮው እንሰማው የነበረው “ክርስትና” እና “ ክርስቲያን” “ክርስቶስ” ከሚለው ቃል የተፈበረኩ ሆነው ትርጓሜቸውም የክርስቶስ ተከታይ ማለት ነው” የሚል መረጃ አልባ አፈ ታሪክ ነበር፡፡ ባይገርማችሁ ይህን አፈ-ታሪክ ዊኪፒዲያ የተባለው መደበለ-እውቀትም ይደግመዋል፡፡ እናብብለት እስኪ ፡-
A Christian is a person who adheres to Christianity, an Abrahamic, monotheistic religion based on the life and teachings of Jesus of Nazareth. “Christian” derives from the Koine Greek word Christós (Χριστός), a translation of the Biblical Hebrew term mashiach.
በግርድፉም “ ክርሰቲያን የአብራሃምን አሀዳዊ እምነት በናዝሬቱ ኢየሱስ ህይወትና አስተምህሮ መሰረት መተግበርን የሚሰብከውን ክርስትና የሚከተል ግለሰብ ማለት ነው፡፡ “ክርስቲያን” ክርስቶስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተፈለቀቀ ሆኖ መሲህ ለሚለው የሂብሩ ቃል ትርጓሜ ነው፡፡
ለዚህ አፈ – ታሪክ የምናነሳቸው አምክንዮአዊ ጥያቄዎች እንደሚከተለው ይከተላሉ ፡- 1) እውን ኢየሱስ ምድር ላይ ሲንቀሳቀስ ስሙ ክርስቶስ ነበርን? 2) ስያሜውን ሲጀምር ማን ምን ቁርጥ አድርጎት ነው ለእምነቱና ለተከታዮቹ የለገሰው? 2) የኢየሱስ መጠሪያ ክርስቶስ ባይሆንስ የስሙን ትርጉም ይዘን ለተከታዮቹ ስያሜ ማድረግ እንችላልን?
1) እውን ኢየሱስ ምድር ላይ ሲንቀሳቀስ ስሙ ክርስቶስ ነበርን?
ይህንን ጥያቄ ለለመለስ በመጀመሪያ ኢየሱስ (ዐ.ሰ) በምድር ሲንቀሳቀስ ይጠቀመው የነበረው ቋንቋ ምን ነበር? የሚለውን መመለስ የግድ ይላል፡፡ ይህን ጥያቄ ይመልስልን ዘንድ ራሱን ዊኪፒዲያን እንዲህ ብለን እንጠይቀው” what was the language of Jesus?“ እንዲህ ብሎ ይመልስልናል፡-
Aramaic was the common language of the Eastern Mediterranean during and after the Neo-Assyrian, Neo-Babylonian, and Achaemenid Empires (722–330 BC) and remained a common language of the region in the first century AD. In spite of the increasing importance of Greek, the use of Aramaic was also expanding, and it would eventually be dominant among Jews both in the Holy Land and elsewhere in the Middle East around 200 and would remain so until the Arab conquest in the seventh century.
በኒዮ አሲራውያን ፣ በኒዮ ባቢሎናውያን እና በአኬሜኒድ ንጉሰ-ነገስት (722-330 BC ) ዘመንና ከዛም በኋላ አርማይክ በሜዲትራኒያን በስተምስራቅ ለነበሩ ሀገሮች የጋራ ቋንቋ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን እስከ አንድኛውም ክ.ዘ. (ክርስቶስ ከአረገ) የጋራ ቋንቋ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ምንም እንኳ የግሪክ ቋንቋ አስፈላጊነት እየተስፋፋ ቢመጣም የአርማይክ ቋንቋም በስፊው እየተነገረ መጥቶ በአይሁዶች መካከል በቅዱስ መሬቱም በሌሎችም መካከለኛው ምስራቅ አገሮች ውስጥ እስከ 200 AD አካባቢ ድረስ ማዕከላዊ ቋንቋ ሆኖ ከቆየ በኋላ አረቦች በሰባተኛው ክ.ዘ. አካባቢውን ሲቆጣጠሩ ግብዓተ-መሬቱ ተፈጽሟል፡፡
እንግዲህ ወዳጆቼ ኢየሱስ የግሪክ ቋንቋን እንዳልተናገረበት፣ እንዳልሰበከበትና በግንባሩም ተደፍቶ እንዳልጸለየበት በግልጽ የተረዳን ይመስለኛል፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ በግሪክ ቋንቋ ክርስቶስ ሆይ! ብለው ደቀማዛሙርቱ ወይም ተራው ህዝብ እንዳልጠሩትም፣ ቢጠሩትም ሊመልስላቸው እንደማይችል- ቆይ እዝች ጋር ቅንፍ እንክፈትና (ስሙ ስላልነበር) – የሚል ሀረግ እንጨምርና ጨምረንም ምንረዳ ይሁን፡፡ አሜን!፡፡
ኢሊያህ ሆይ! በሉኝ፡፡ አቤት እላችኋለሁ ስሜ ስለሆነ፡፡ ታዲያ በአርማይክ ቋንቋ የኢየሱስ ስም ማን ነበር? ብላችሁም ተይቁኝ? እኔም ይኀችሁ እስኪ መድበለ-ዕውቀቱን አብረን ደግመን እናንብበው እላችኋለሁ፡፡
In English, the name Yeshua is extensively used by followers of Messianic Judaism, whereas East Syrian Christian denominations use the name Isho in order to preserve the Aramaic or Syriac name of Jesus.
በእግሊዘኛ ዮሹዋ የሚለው ስም ኢየሱስን በሚቀበሉ አይሁዶች ዘንድ በሰፊው ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ቢሆንም በምስራቃዊ ሶሪያ የሚገኙት እውቅ የክርስቲያን ቡድኖች ግን የኢየሱስን የአርማይክኛውን ወይም የሶሪያኛውን ስም ለመጠበቅ ኢሾ የሚለውን ቃል ይጠቀማሉ፡፡
መልሱን በሚገባ አገኘን አይደል? ግን እስኪ አንዴ ስሙን እንድገመው ኢሾ! አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ ኢሾ!ኢሾ! ኢሾ!

ወዳጆቼ ይህ ኢሾ የሚለው ስም ኢሳ ከሚለው ቁርዓናዊ እና አረብኛዊ ስም ጋር አልተቀራረበባችሁም? እንዴታ ይቀራረባሉ እንጂ፡፡ ይþውላችሁ ራበርት የሚባል አንድ ፈረንጅ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢመጣ እሮበርት በሚል አማረኛዊ ቅላጼ ባለው መልኩ ሊጠራ ይችላል፡፡ መሀመድ የሚባል ጸይም ሀበሻ እነጮቹ ጋር ቢቀላቀል ደግሞ “ማሜድ” ጠና ካለም ምጻረ -ቃል በሚመስል “ማድ” ወይም “ሞህ” ብለው ሊጠሩት ይችላሉ፡፡ ግና ስሙን ሙሉ በሙሉ ወደ እንግሊዘኛ ለውጠው Thankful ብለው ቢጠሩት ሰውዬው ራሱ ግራ ሊጋባ ይችላል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ስሙ ስላልሆነ ነው፡፡ ሌላ አንድ ምሳሌ እንይ፡፡ አንዲት “ነፊሳ ከማል” የምትባል ወጣት “እባክሽ ስምሽ “ሐበሻ” “ሐበሻ “ስለማይል እንተርጉመውና “ ጥሩነሽ ሞላ” ወደ ሚል አማርኛዊ ቃል እንከርብተው ብትባል ምትስማማ ይመስላችኋል?

ስንጠቀልለው አንድ ቃል ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ሲንከባለል ትንሽ የድምጽ ለውጥ መኖሩ የግድ ነው፡፡ ኢሾ የሚለውን ስያሜ ወደ ክርስቶስ ማምጣት ግን በየትኛውም የሂሳብ ስሌትና ቀመር እማይቃለል ( unsolved) ጥያቄ ነው፡፡ ወዳጆቼ ይገርማችኋል በትርጉም ደረጃ እንኳ ብናይ ኢሾ ማለት ህይወትን ለጋሽ ማለት ሲኾን ክርስቶስ ማለት ደግሞ የተቀባ እንደማለት ነው፡፡ ይህንን የስም ዝውውር “አራባ እና ቆቦ” ብንለውስ በካፒታል ሌተር፡፡
ወዳጆቼ እስኪ እዚህ ጋር ትንሽ ትንፋሽ እንውሰድና በሚቀጥለው የሚቀጥለውን ብንቀጥልስ ? ,والسلام عليكم ورحمة الله
ዋቢ መጽሀፍት
ጎግልን ጎልጉሉና ዊኪፒዲያ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ