ከአጀንዳ መቀበል ወደ አጀንዳ መስጠት ተሸጋግረናል

(ሰልማን)

ከአጀንዳ መቀበል ወደ አጀንዳ መስጠት ተሸጋግረናል ይላሉ ፖለቲከኞች 😀😀😀 ይሄው ሚሽነሪዎች በቅጥፈታቸው ቢዚ ሲያደርጉን እንዳልኖሩ ዛሬ የእኛን መጽሐፍ ቁጭ ብለው ማንበብ ይዘዋል… አልሐምዱሊላህ።

እና ንቁ! የምትለውን በኩሬን “አብዱልሃቅ ጃሚል” የሚባል (የከፈረ ይሁን ስሙን ያሰለመ እንጃ) ሂስ ነገር ሀስሶ መጽሐፍም አዘጋጅቶ አየሁ።

እና ምን አለ “ንቁ!” ከይሆዋ ምስክሮች የተኮረጀ ነው አለኝ 😀😀😀
በነገራችን ላይ ቃል አይኮረጅም ሀሳብ እንጅ። ሀሳቡን ኮርጄ ከሆነ እሰየው ቃል ከሆነ ግን ቃል የግል ንብረት አይደለም። ሲቀጥል ንቁ! የሚለው ቃል በይበልጥ የቁርኣን ቃል ነው ብዬ ስለማምን ነው የተጠቀምኩት። ቁርኣን ከ35 ጊዜ በላይ “ንቁ!” የሚለውን ቃል ሲጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ ግን 5 ጊዜ ብቻ ነው የጠቀሰው። እና ይሄ ቃል ተገቢነቱ ለእኛ ነው ብዬ አስቤበት የመረጥኩት ነው።

በመቀጠል “መጽሐፍ ቅዱስን ማን ፃፈው?” ከሚለው የመጀመሪያው ምዕራፍ (መጽሐፉ 8 ምዕራፎች ነው ያሉት) “ኦሪት” ለሚለው ርዕስ ረጂም ማስተባበሪያ ፅፏል። ባጭሩ ፀሀፊው አይታወቅም ማለትህ ዋሽተሃል ነው። ላነሳኋቸው ተጨባጭ ማስረጃዎች ግን አንድም መልስ ሳይሰጥ በተፃፈበት ዓመት ላይ ብቻ ብዙ ሀተታ ከትቧት። ለአብነት ኦሪትን ሙሴ ፃፈው ካላችሁ ሙሴ ከሞተ በኋላ ያለውን ታሪክ ማን ፃፈው ሲባሉ መልስ የለም። ሌላው ቀርቶ ከሙሴ በኋላ ከብዙ መቶ ዓመታት ወዲህ የተፈፀሙትን ክስተቶችስ ማን ከኦሪት ጨመራቸው ሲባል አይታወቅም። እንዲሁ ብቻ ነቢያት ይላሉ። የትኛው ነቢይ የሚታወቅ የለም። የመጽሐፉ ኮፒ አለ ወይ ሲባሉም የለም። የኮፒ ኮፒም የለም። በዚህ ሁኔታ መጽሐፉ የሙሴ ነው ማለት አይቻልም ብዬ ጥሬ ሀቁን ነው ያስቀመጥኩት። ሀያሲው ግን ጥያቄዎቹን ትቶ በዚህ ዘመን ነቢያት ተነስተው በዚህ ዘመን አርመውት የሚል ከአውዱ የወጣ ትችት አቅርቧል። ፀሀፊው ካልታወቀ አራሚ ነቢያቱ ስማቸው እንኳን ካልቸጠቀሰ አበቃ ስለ ዘመንም ስለ ዓመትም ማውራት ትርጉም የለውም እኮ።

ይቀጥልና መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ግሪክኛ የተረጎሙት 72 ሊቃውንት ሲሆኑ 70 ብሎ አሳስቷል ሲል ተችቶኛል። ጉዳዩ እኮ ቁጥሩ ሳይሆን የመተርጎሙ ነበር። እንደዛም ሆኖ ትክክል ነኝ። ሰዎቹ በተለምዶ 70ዎቹ ነው የሚባሉት። ምሳሌ ደርግ 60ዎቹ የሚባሉ ባለስልጣናትን ረሽኗል። ግን ቁጥራቸው ከዚያ በላይ ነው። እኔም በዚህ አጠራር የተጠቀምኩት በተለምዶ 70ዎቹ ስለሚባሉና ለአጠቃቀም ምቹም ስለሆነ ነው።

ሌላው ስድብ ነው። ገና ለመጀመሪያ ገፅ ሂስ ይሄን ያህል ትችትና ስድብ ሲያወርድብኝ የእውነት ይቺ ሀቅ እንዴት ትከብዳለች ነው ያልኩት 😊😊😊 በዚህ ከቀጠለ ለ270 ገፅ ሂስ 5ሺህ ገፅ ፅፎም የሚበቃው አይመስለኝም። አንድ እውነት ግን የምነግራችሁ 5ሺህ መጽሐፍ ቢፅፍ እንኳን የመጀመሪያዋን አንዷን ገፅ ማስተባበል እንደማይችል እርግጠኛ ሆኘ ነው። ምክንያቱም ይሄ አላህ በቁርኣኑ የነገረን ሀቅ ነው።

ሌላው እንደምታዩት ሲጨንቃቸው ማደናገሪያ መጽሐፍ አዘጋጅተዋል። ቅድም ቃል ኮርጀሃል እንዳላለኝ እሱ ርዕሱን “ኢስልምና መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?” ብሎ ኮፒውን ይዞት መጥቷል 😀😀😀😀

መጽሐፉ ያው ገና ስላልወጣ ለጊዜው ጀርባውን ነው ያሳዩን። ባጭሩ ኢስላም ሃይማኖት ሳይሆን ፖለቲካ ነው የሚል ነው። እርግጥ ነው ኢስላም ለሰው ልጅ መመሪያነት የወረደ ዲን ስለሆነ ፖለቲካዊም መንፈሳዊም ነው። አምልኮ ብቻ ሳይሆን አስተዳደራዊ ጉዳዮችንም መርህ የሚያበጅላቸው ሃይማኖት ነው። ለዚህም ነው ኢስላም የተሟላ መመሪያ ነው የምንለው።

ነገርግን ሌሎች እምነቶች አስተዳደራዊ መመሪያ ስለሌላቸው ሴኩላሪዝም በሚል ፍልስፍና እምነትን ከፖለቲካ ይለያሉ። ከዚህ ውጭ አማራጭ ስለሌላቸውም ነው። በኢስላም ግን ሴኩላሪዝም አይሰራም። ኢስላም የሰው ልጆች ምልዑ መመሪያ እንጅ በፖለቲካ በትምህርት እየተባለ ከማዕቀፍ ማውጣት አይቻልም። እናም እውነት ነው ፖለቲካም ሃይማኖትም ነው።

ሌላው “እኔ የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ” የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ ጠቅሶ ኢስልምና በነቢዩ ሙሐመድ (ዐሰወ) የተጀመረ ነው ይላል። ይህንን በማስመልከት ቁርኣን ራሱ “አላህ ፍጥረታትን የፈጠረበትን እምነት (ኢስልምናን) ያዙ” በማለት ኢስላም የፍጥረታት ሁሉ መፈጠሪያ መንገድ መሆኑን ገልጿል። ነቢዩ (ዐሰወ) እና ሌሎችም ነቢያት ደግሞ የሙስሊሞች መጀመሪያ የተባሉት ለነበረው ትውልድ ኢስልምናን በመቀበል የመጀመሪያ መሆናቸውን ለመግለፅ እንደሆነ ሙፈሲሮች ፅፈዋል። ለዚህ አይነት ጥያቄዎች የየህያን “ገለባ ክሶች” PDF ገለጥ አድርጎ ከብናኝ የቀለሉ ማደናገሪያዎች እንደሆኑ ማየት ይቻላል።

እኔን የገረመኝ ግን ጠንካራ ሀሳቡን ቋጭቶ ይይዛል በሚባለው የጀርባ ሽፋን እንኳን እንዲህ የቀለለ ሀሳብ ካነሱ ውስጡ ምን ሊሆን እንደሚችል ነው። እንዳውም ሰው በጀርባውም ይዋሻል እንዴ ነው ያልኩት 😀😀😀

ዞሮ አሁንም ለንፅፅር ልጆች የምላችሁ ፃፉ ነው። እውነት ለመናገር ሰሞኑን እየወጡ ያሉት የንፅፅር መጽሐፎች በይዘታቸውም በቅርፃቸውም በጣም ጠንካራ ናቸው። መጽሐፎቹን ያነበበ ሰው የትኛውንም ፓስተር ወይም ሰባኪ አንገት ማስደፋት ይችላል። እውነት ለባጢል ፊትና እንጅ ባጢል ለሀቅ ፊትና ሊሆን አይገባውም። አጀንዳ ሰጪ እንጅ አጀንዳ ተቀባይ መሆን የለብንም። ስለዚህ ሁላችሁም መፃፍ ስለምትችሉ ፃፉና ድምፃቸውን አጥፉት።

«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።»
(ኢስራ 81)

ሼር ያድርጉ
  • 2
    Shares