ከመጽሀፍ ቅዱስ አስከፊ ክፍሎች መካከል

ሼር ያድርጉ
433 Views

“አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ። ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ አድኑአቸው።”
ዘኍልቁ 31፥ 17-18

ይህ አንቀፅ በአለማችን ከተላለፉ አስፈሪ የጭፍጨፋ ትዕዛዞች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን አይደለም ከአምላክ ይቅርና ከግለሰብ እንኳን የማይጠበቅ ኢ-ሰብአዊ ትዕዛዝ ነው።ጨፍጫፊ ትዕዛዝ መሆኑን ለጊዜው እናቆየውና ከዚህ ጋር ተያይዞ ግን የተወሰኑ ጥያቄዎችን ማንሳት ይኖርብናል

፩- አንቀፁ እንደሚነግረን በመኝታ ወንድ የሚያውቁት ተነጥለው እንዲገደሉ ያዛል። በመኝታ ወንድ የሚያውቁት ማለት በጋብቻም ይሁን ከዛ ውጭ ድንግልናቸው ከነሱ ጋር የሌሉ ማለት ነው። ታዲያ ጥያቄው እነዚህ ሴቶች ድንግል አለመሆናቸውን በምን መልኩ ፈትሸውና አውቀው ነው የሚገሏቸው? የሚለው ነው። “በመጠየቅ” የሚል ሰው ካለ የዋህ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ድንግል ያልሆነችን ሴት እየገደሉ እንደሆነ የምታቅ ማንኛውም ሴት ድንግል አይደለሁም ብላ ራሷን አታጋልጥም። በዚህ አንቀፅ ዙሪያ ከአንድ የክርስቲያን መምህር ጋር ውይይት ሳደርግ የመለሰልኝ መልስ “ምናልባት በእጃቸው ሙከራ እያደረጉ ይሆናል” ነበር። ጠቅለል ስናደርገው ማረጋገጫውን በእጃቸውም ይስሩት ወይንም በተግባር ይሞክሩት ለዚህ ክስተት ዋነኛ ተጠያቂው ህጉን ያስተላለፈው አምላክ ነው።

፪- አምላክ እንዴት ሴትን ልጅ በዚህ መንገድ የወሲብ መጠቀሚያ የሚያደርግ ህግ ይደነግጋል?ሴትን ያውም ድንግል ባለመሆኗ ተገላ ድንግል መሆኗ ግን ቢያንስ ህይወቷን አትርፎ የወሲብ ባሪያ የሚያደርጋትን ህግ እንዴት “ፍቅር” ነው ተብሎ የሚታሰብ አምላክ ይደነግገዋል ብለው ያምናሉ?

መልሱን ለህሊናዎ..!

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)