እየሱስ አምላክ ላለመሆኑ 10 ወሳኝ ማስረጃዎች

1- እየሱስ ሁሉን አዋቂ አልነበረም

እንደሚታወቀው አምላክ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ ከዕውቀቱ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም፡፡ እየሱስ ግን እንደ መፅሀፍ “ቅዱስ” ገለፃ ይህንን መስፈርት አያሟላም፡፡

” ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።” (የማርቆስ ወንጌል 13:32)

2- እየሱስ አንዲትም ጊዜ እኔ አምላክ ነኝ ብሎ አያቅም

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር እጅግ ብዙ ቦታዎች ላይ አምላክነቱን ሲያውጅና ሲገልፅ እንመለከታለን እየሱስ ግን በተቃራኒው ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽ አላለም፡፡ እስኪ ከብሉይ ኪዳን ለአብነት እንመልከት

” እግዚአብሔርም አለው። ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዛ፥ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።” (ኦሪት ዘፍጥረት 35:11)

” አለውም። የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና።” (ኦሪት ዘፍጥረት 46:3)

“እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ። ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው። “
(ኦሪት ዘጸአት 16:11,12)

” ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ” (ኦሪት ዘጸአት 20:2)

3- እየሱስ በአዲስ ኪዳን የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቷል እራሱ መፅሀፍ “ቅዱስ” እንደሚነግረን ደግሞ የሰውን ልጅ ማመን እንደሌለብን ይነግረናል

” ኢየሱስም። ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።” (የማቴዎስ ወንጌል 8:20)

” ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን። ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።” (የማቴዎስ ወንጌል 9:6)

” የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።” (የማቴዎስ ወንጌል 12:8)

” ለደቀ መዛሙርቱ። የሰው ልጅ በሰው እጅ ይሰጥ ዘንድ አለውና እናንተ ይህን ቃል በጆሮአችሁ አኑሩ አለ።”
(የሉቃስ ወንጌል 9:44)

ሌላ ቦታ ባይብልን ስናነብ ደግሞ የሰው ልጅ መታመን እንደሌለበት ይነግረናል፡፡

(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 146)
———-
1፤ ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ።

2፤ በሕይወቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።

3፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ።

4- እየሱስ የነበረው ስልጣንና ሀይል የእርሱ አልነበረም፡፡

” ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥”
(የዮሐንስ ወንጌል 13:3)

” እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።”
(የዮሐንስ ወንጌል 12:49)

” እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።” (የዮሐንስ ወንጌል 5:30)

” ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤” (የዮሐንስ ወንጌል 7:16)

5- እየሱስ የተላከው ለእስራኤላውያን እንጅ ለዓለም አልነበረም፡፡

” እርሱም መልሶ። ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።” (የማቴዎስ ወንጌል 15:24)

6- እየሱስ መልካም ተብሎ መጠራትን አልፈልገም ነበር ምክንያቱም መልካም የሚባለው አምላክ ብቻ ነውና

” እርሱም። ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።” (የማቴዎስ ወንጌል 19:17)

7- እየሱስ በራሱ አቅም ማንንም ማዳን አይችልም ነበር፡፡

” እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤” (ወደ ዕብራውያን 5:7)

በዚህ አንቀፅ እንደምንመለከተው እየሱስ ሲጨንቀው ፊቱን ያዞረው ሊያድነው ወደሚችል አካል ነበር እንጅ እራሱ አዳኝ ቢሆን መጠየቅ ባላስፈለገው ነበር፡፡

8- በእየሱስ ጊዜ የነበሩና በእርሱ ያመኑ ሰዎች እርሱ አምላክ መሆኑን አያምኑም ነበር፡፡

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 16)
———-
13፤ ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።

14፤ እነርሱም። አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።

9- አምላክ ከሴት ማህፀን ተወልዷል ብለው ያምናሉ? ምን ይሄ ብቻ ከዚያም ጡት ጠብቶ ምግብ በልቶ ተፀዳድቶ ኑሯል ብለው ያምናሉ? እውን የአምላክ ባህሪ ይሄ ነውን?
አላህ ከዚህ ቅጥፈት ይጠብቀን፡፡

10- እየሱስ እያለቀሰ አምላኩን በልመና ይገዛ ነበር፡፡

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 26)
———-
36፤ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ ደቀ መዛሙርቱንም። ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ አላቸው።

37፤ ጴጥሮስንም ሁለቱንም የዘብዴዎስን ልጆች ወስዶ ሊያዝን ሊተክዝም ጀመር።

38፤ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋ0ር ትጉ አላቸው።

39፤ ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ። አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።

ታዲያ እየሱስን ያመልካሉ ወይንስ እየሱስ ያመለከውን ብቸኛ አምላክ ያመልካሉ? ፍርዱን ለርስዎ

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

ሼር ያድርጉ
  • 47
    Shares