እውን ክርስቲያናዊው መጽሐፍ ለመለኮታዊ መረጃነት በቂ ነውን?

ሼር ያድርጉ
317 Views
ኢሊያህ ማህሙድ ክፍለ ኣንድ በኣላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያ ዘመን የመጨረሻ ነብይ ኾነው በተላኩት ሙሐመድ ላይ የኣላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ ብለን ቀጠልን፡፡ ክርስቲያናዊው መጽሐፍ ዛሬ ላይ እንደምናየው ወጥ ኾኖ ከመዘጋጀቱ በፊት ብጥስጥስ ባሉ የተለያዩ ደንገሎች (ፓፒረስ) ላይ የተጻፈ ነበር፡፡ እነዚህ እደ-ክታባት የተለያየ ቦታ የሚኖሩ፣ የተለያየ ፍላጎት ና ስነ-መለኮታዊ አረዳድ ያላቸው ግለሰቦች እንደጻፏቸው የዘርፉ ልሂቃን በምልዓት ይስማማሉ፡፡ ዛሬ ላይ የበኩር (ኦሪጂናል) የሚባሉ ጽሑፎች በሕይወት የሉም፤ስለኾነም በሕይወት የምናገኛቸው ጽሑፎች የበኩር ሳይኾኑ ከሌላ ቀደምት ጽሑፎች የተገለበጡ ናቸው፡፡ ኹሉም ጻፎች ጽሑፎቻቸውን የገለበጡበት ሌላ ቀዳሚ ጽሑፍ ኣለ፡፡ ታዲያ በኹሉም ጽሑፎች መካከል ከቀላል እስከ ከባድ ልዩነቶች እንዳሉ ልብ ይሏል!!! ፕሮፌሰር ባርት እንዲህ ይላል፡-
“ዋናዎቹ ሳይሆን ዛሬ የዋናዎቹ ቅጂዎች እንኳ የሉንም፡፡ የዋናዎቹ የቅጂ ቅጂዎችም ቢኾኑ የሉንም፡፡ ወይም ደግም የዋናዎቹ የቅጂ ቅጂ ቅጂዎችም የሉንም፡፡ አሁን ያሉን የኋላ ኋላ የተጻፉ ከክፍለ ዘመናት በኋላ የተዘጋጁ ቅጂዎች ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም ቅጂዎች ታዲያ ሺህ ቦታዎች ላይ እርስ በርስ ይጣረሳሉ፡፡ …እነዚህ ቅጂዎች ያን ያህል ከመጣረሳቸው ባሻገር ምን ያህል መጣረሶች እንኳ እንዳሉ መገመት ያዳግታል፡፡ ምናልባት በማነጻጸር ማስቀመጡ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም፤ እንዲህ ብለን፡- በእደ-ክታባቱ መካከል አዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉት ቃላት በላይ መጣረሶች አሉ፡፡” መጽሐፍ ቅዱስን ማን በረዘው/ገጽ 20
በተመሳሳይ መልኩ ዶ/ር ቄስ ሳሙኤል ሐቢብ፣ዶ/ር ቄስ ፋይዝ ፋሪስ፣ቄስ ሙኒስ ዓብዱኑር እና ጆሴፍ ሳቢር ዳኢረቱል መዓሪፍ ኣልኪታቢያ በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 297 ላይ እንዲህ ይላሉ፡-
وقد فقدت أصول أسفار العهد الجديد – بلا شك في زمن مبكر جداً ومعنى هذا أنه ليس من الممكن أن نحدد بدقة كاملة كل كلمة من الكلمات الأصلية للعهد الجديد على أساس أي مخطوطة بذاتها، ولا سبيل إلى ذلك الا بمقارنة العديد من المخطوطات ووضع أسس تحديد الشكل الدقيق – بقدر الإمكان – للنص الأصلي
“ የኣዲስ ኪዳን በኩረ ጽሑፎች ያለ ምንም ጥርጥር ገና በጠዋቱ በትክክል ጠፈተዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በየትኛውም እድ ክታብ ላይ ያሉትን ቃላት ጥርት ባለ መልኩ ሙሉ በሙሉ የመጀመሪያዎቹ ናቸው ብለን መደምደም እንዳንችል ያደርገናል፡፡ የመጀመሪያዎቹን ለመወሰን ታዲያ ጠንካራ መስፈርት አስቀምጠን የቻልነውን ያህል በኩር ናቸው የሚባሉትን በርካታ እደ-ክታባት ማመሳከር ይጠበቅብናል፡፡”
በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ በኩር የሚባሉ ጽሑፎችን በማመሳከር ወደ ትክክለኛው ጽሑፍ መድረስ ቢቻልም፣ የመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ግን ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል፡፡ ኣልመድኸል ኢላ ዓህዲል ጀዲድ ገጽ 111 እንዲህ ይላል፡-
من الأمور البديهية التي لا ينكرها اي إنسان أن نسخ الأصلية التي خرجت من يد كتاب العهد الجديد غيرموجودة. وأن أقدم المخطوطة وصلت إلى أيدينا تصل إلى النصف الأول من القرن الثاني,اي بعد الأنتهاء من كتابة كل اسفار العهد الجديد ببضع عشرات من السنين
“ማንም ሰው ከማያስተባብላቸው ግልጽ ጉዳዮች ውስጥ ኣንዱ ከአዲስ ኪዳን ጸሐፍት የተገኙ በኩረ ጽሁፎች በሕይወት ኣለመገኘታቸው ነው፡፡ እኛ ዘንድ የደረሰው ጥንታዊው እደ-ክታብ ከኹለተኛ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው ኣጋማሽ ኣካባቢ የተጻፈው ነው፡፡ ይህ ማለት ኹሉም የአዲስ ኪዳን ክታባት ከተጻፉ ከብዙ አስርተ ዓመታት በኃላ ማለት ነው፡፡”
የመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች መጥፋት ብቻም ሳይኾን ከነርሱ በኋላ በዓመታት ዘግይተው የተጻፉትም እርስ በርስ እጅጉን ይጣረሳሉ፡፡ ወደ መጀመሪያው ዋቢ መጽሐፋችን ደግመን ራሱ ገጽ ላይ ትንሽ ከፍ ብለን ስናነብ እንዲህ ይላል፡- فإن استنساخ عمل أدبي قبل عصر الطباعة يختلف عنه بعد اختراعها، فمن الممكن الآن طباعة أي عدد من النسخ المتطابقة تماماً، أما قديماً فكانت كل نسخة تكتب على حدتها باليد وفي مثل تلك الأحوال، كان لابد ألا تتطابق تماماً أي مخطوطتين من أي كتاب وبخاصة إذا كان كبيراً نوعاً “ የመተየቢያ መሳሪያ ከመፈጠሩ በፊት የቅጂ ኹኔታ በእጅ የሚፈጸም ነበር፡፡ ዛሬ ላይ የትኛውም ቁጥር ያለውን ቅጂ ፈጽሞ ኣንድ ኣይነት ኣድርጎ ማውጣት ይቻላል፡፡ ቀደም ሲል ግን እያንዳዱ ቅጂ ለብቻው በእጅ ይገለበጥ ስለ ነበር፣ ከየትኛውም መጽሐፍ የተቀዱ ኹለት ቅጂዎች -በተለይ ደግሞ ጸሑፉ ዳጎስ ካለ- ሙሉ በሙሉ ሊስማሙ በፍጹም ኣይችሉም ነበር፡፡” በረዥም የግልበጣ ዘመን ጸሐፍት በሚገለብጧቸው ጽሑፎች በርካታ ቦታዎች ላይ ልወጣዎችን ኣድረገዋል፡፡ ኣልመድኸል ኢላ ዓህዲል ጀዲደል ገጽ 13 ላይ እንዲህ ይላል፡- ومن الواضح أن ما أدخله النساخ من التبديل على مر القرون تراكم بعضه على بعضه الأخر. فكان النص الذي وصل آخر الأمر إلى عهد الطباعة مثقلا بمختلف الألوان التبديل ظهرت في عدد كبير من القرات 13. “ በዘመን ሒደት ውስጥ ገልባጮች ያስገቧቸው ቅያሮዎች እርስ በርስ ተነባብረዋል፡፡ የሕትመት ዘመን ላይ የደረሰው ሠንድ በተለያዩ የቅየራ ቀለማት የተዥጎረጎረ በርካታ የተለያዩ ንባቦች ያሉት ነበር ” ጸሐፍት ለተለያዩ ጉዳዮች የሚገለብጧቸውን ጽሑፎች ይለዋውጡ ነበር፤ለምሳሌ መለኮታዊ አቋማቸውን ለማጽናት ተቃራኒያቸውን ለመርታት ወዘተ….ዳኢረቱል መዓሪፍ ገጽ 295 ላይ እንዲህ እናነባለን፡-
وقد حدثت احيانا بعض الأضافات لتدعيم فكر لاهوتي, كما حدث في إضافت عبارة(( والذين يشهدون في السماء هم ثلاثة) حيث هذه العبارة لا توجد في اي مخطوطة يونانية ترجع إلى ماقبل القرن الخامس عشر,ولعل هذه العبارة جاءت اصلا في تعليق هامشي في مخطوطة لاتنية , وليس كاضفة مقصودة إلى نص الكتاب المقدس, ثم ادخلها احد النساخ في صلب النص
“መለኮታዊ አቋምን ለማጽናት በእደ-ክታባቱ ላይ ኣልፎ ኣልፎ ኣንዳንድ ጭማሮዎች ተደርገዋል፤ “በሰማይ የሚመሰክሩ ሦስት ኣሉ” የሚለው ጥቅስ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ይህ ጥቅስ ከኣስራ ኣምስተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ባሉ የግሪክ እደ-ክታባት ውስጥ ኣይገኝም፤ምናልባት ይህ አገላለጽ ኾን ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተደረገ ጭማሪ ሳይኾን፣ በላቲን ክታባት በህዳግ ማስታዎሻዎች ላይ የነበረ ኾኖ በኋላ ላይ የኾነ ጻሐፊ በዋናው ጽሑፍ ውስጥ የጨመረው ሊኾን ይችላል፡፡” http://t.me/religionandphylosophy