እውን ኢየሱስ ይወደናል?

ሼር ያድርጉ
418 Views

ክርስቲያኖችን እየሱስ እንደሚወደንና እንደማይወደን ስንጠይቃቸው እጅግ በሚያማልል መልኩ እየሸነገሉ በጣም እንደሚወደን ከዛም ብሶ “እንደተሰቀለልን” ይነግሩናል። ጥሩ እንግዲህ መወደድ መልካም ነው እንበልና እንቀጥል ..

ታዲያ ተያያዥ ጥያቄያችን የሚሆነው እንዲህ ወዶን በእሱ መለኮታዊነት ሳናምን ብንሄድ መንግስተ ሰማያትን እንወርሳለን? ስንላቸው ፍሬን ይይዛሉ፤ እንደማይሆን ያውቁታል። እውነታውን ለምን አናወራም? እውነታው እንዲህ ነው።

1- እግዚአብሄር መጀመሪያውኑ ከቃላት ጨዋታ ውጭ ትክክለኛ ማንነቱ ፍቅርን ያዘለ አይደለም። የፍቅር አምላክ ቢሆን ህጻናትና ሴቶችን ባላስጨፈጨፈ ነበር። አህያ ሳይቀር እንዲገደል የሚያዝ አምላክ የጭካኔ እንጅ የርህራሄ አምላክ አይደለም።

“፤ ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።”
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 9: 6)

“፤ አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።”
(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15: 3)

2- ክርስቲያኖችም ይህች መንገድ ሌላውን ለመሳብ ታግዘናለች ብለው አስበው እንጅ አማኝ ያልሆነን አካል አይደለም ሊወዱ ይቅርና በቤታቸው እንኳን እንዳይቀበሉ ጭራሽም ሰላም እንዳይሉት መፅሀፉ እንደሚያዝ ያቁታል።

“፤ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤”
(2ኛ የዮሐንስ መልእክት 1: 10)

እውነታው ይኸው ነው።

وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

[ አል-በቀራህ – 120 ]
አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡

በርግጥም አላህ እውነት ተናገረ

Shortlink http://q.gs/Ewiea