እውን ነብዩ “ﷺ” መፃፍ ይችላሉን?

ሼር ያድርጉ
156 Views

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

አንዳንድ ክርስቲያናች የተወሰኑ ሀዲሶችን በመያዝ ነብዩ ይፅፉ እንደነበር ለማስረዳት ሲደክሙ አስተውለናል። ነብዩ ማንበብና መፃፍ መቻላቸውን ለማስረዳት ለምን ይሆን እንዲህ የሚለፉት? የሚለው ጥያቄ ከተነሳ መልሱ ግልፅ ነው። ምክንያቱም ማንበብና መፃፍ የሚችሉ ከሆነ ቁርአንን ከሌሎች ጥንታዊ መፅሀፍት እያጣቀሱ ፅፈውታል ብሎ ለመከራከር ስለሚመቻቸው ነው። ለዚህም ነው መጀመሪያውኑም ዑምይ (ማንበብና መፃፍ የማይችሉ) የሆኑበት ምክንያት ይህንን ከንቱ ሀሳባቸውን ውድቅ ለማድረግ እንደነበር ቁርአን የሚነግረን።

አላህ እንዲህ ይላል፦

وَمَا كُنتَ تَتْلُو مِن قَبْلِهِ مِن كِتَابٍ وَلَا تَخُطُّهُ بِيَمِينِكَ ۖ إِذًا لَّارْتَابَ الْمُبْطِلُونَ

[ ሱረቱ አል-ዐንከቡት – 48 ]
ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፡፡ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር፡፡

በዚህ አንቀፅ አምላካችን አላህ እንደሚነግረን ነብዩ መፃፍና ማንበብ የሚችሉ ቢሆን ኖሮ ሊተቿቸው ያሰፈሰፉ ሰዎች ትልቅ እድልን ያገኙ ነበር፤ ግን ያ አልሆነም። ታዲያ ይህን መንገድ ክፍተት ለማግኘት የተለያዩ ሀዲሶችን ቢያግዙን በሚል በማዘባት ለማቅረብ ይሞክራሉ። ከነዚህ ሀዲሶች መካከል ከታች የሚገኘው ሀዲስ ዋነኛው ነው። ሀዲሱን አስቀምጠን ወደ ማብራሪያው እናልፋለን

Narrated Ibn `Abbas:

When Allah’s Messenger (ﷺ) was on his death-bed and in the house there were some people among whom was `Umar bin Al-Khattab, the Prophet (ﷺ) said, “Come, let me write for you a statement after which you will not go astray.” `Umar said, “The Prophet (ﷺ) is seriously ill and you have the Qur’an; so the Book of Allah is enough for us.” The people present in the house differed and quarrelled. Some said “Go near so that the Prophet (ﷺ) may write for you a statement after which you will not go astray,” while the others said as `Umar said. When they caused a hue and cry before the Prophet, Allah’s Messenger (ﷺ) said, “Go away!” Narrated ‘Ubaidullah: Ibn `Abbas used to say, “It was very unfortunate that Allah’s Messenger (ﷺ) was prevented from writing that statement for them because of their disagreement and noise.”

Sahih al-Bukhari 5669

በዚህ አንቀፅ ውስጥ “ልፃፍላችሁ” የምትለዋን ቃል በመያዝ ነብዩ መፃፍ እንደሚችሉ ለመግለጽ ሲደክሙ ይስተዋላል። ሀሳቡ ግን እነሱ በተረዱበት መንገድ አይደለም። ነብዩ የመልዕክቱ ባልተቤት እንደመሆናቸው መጠን የፁሁፉን ይዘት ወደራሳቸው አስጠጉት እንጅ ቃል በቃል በብዕር ይዘቱን ልፃፈው ማለታቸው አይደለም። ይህ ግልፅ እንዲሆንልን በአነስተኛ በምሳሌ እንየው፦

አንድ ያልተማረ ሰው “ፍርድ ቤት ውል ልፃፃፍ ልሄድ ነው” ቢል ቃሉን ከአፉ ላይ ነጥቀን ይህ ሰው መፃፍ እንደሚችል መግለፅ ቁምነገሩን መሳት ነው። ይህ ሰው ልፃፃፍ ሲል ማንም ቃሉን ወረቀት ላይ ያስፍረው የይዘቱ ባለቤት እርሱ እንደመሆኑ መጠን ውሉን ተፃፅፏል ተብሎ የሚወሰደው እርሱ መሆኑን ለመግለፅ ነው። በተመሳሳይ ነብዩም ይዘቱ ከሳቸው የሚመጣ እንደመሆኑ መጠን ማንም ሰው ቢፅፈውም የፁሁፉ ባለቤት እሳቸው መሆናቸውን መጠቆማቸው ነበር። ሀሳቡን በቅጡ ያልተረዱ ወገኖች ቃልን ይዞ የመሮጥ የተለመደ ስህተት ውስጥ ዛሬም ሲወድቁ እንዲህ ታዝበናል። መውደቅ የማይሰለቻቸው ፍጡሮች..!