እውን ነብዩ “ﷺ” ሀጥያትን ሰርተዋልን?

2,567 Views

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

ይህንን ክስ በአብዛኛው የምንሰማው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሀጥያት የጸዱ አለመሆናቸውንና ኢየሱስ (ዐ.ሰ) ግን ከሀጥያት የጸዳ መሆኑን ለማሳመን ከሚሞክሩ ሚሽነሪዎች ነው፡፡ በርግጥ እንደ ኢስላም አስተምህሮ ሁሉም ነብያት እየሱስ (ዐ.ሰ) ና ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጨምሮ ሌሎችም ነብያት ከሀጥያት የጸዱ ነበሩ፡፡ እዚህ ግባ ከማይባሉና ከሀጥያት ከማይቆጠሩ ስህተቶች በስተቀር ሀጥያት ውስጥ የሚገቡ አልነበሩም፡፡ ከዚህ በታች ሁሉንም ነጥቦች እየዘረዘርን የሚሽነሪዎችን ቅጥፈት እናጋልጣለን፡፡

1. አንዳንድ የቁርዐን አንቀጾችን ትክክለኛ ትርጓሜያቸው፦

‹‹فَاصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ [٤٠:٥٥]

‹‹(ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፡፡ ለስህተትህም ምሕረትን ለምን፡፡ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታሀን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡›› 40፡55

فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مُتَقَلَّبَكُمْ وَمَثْوَاكُمْ [٤٧:١٩]

‹‹እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህም መዘዋወሪያችሁን፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡›› 47፡19

لِّيَغْفِرَ لَكَ اللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعْمَتَهُ عَلَيْكَ وَيَهْدِيَكَ صِرَاطًا مُّسْتَقِيمًا [٤٨:٢]

‹‹አላህ ከኃጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ) ፡፡›› 48፡2

2. የመተናነስና ራስን ያለመካብ ምልክት

በእስልምና ውስጥ ለአንድ ሰው ከሚሰጠው የሞራል ትምህርት ውስጥ አንዱ ይህ ነው፡፡ሰውየው አምላኩን ለማስደሰት ጠንክሮ መስራቱና በአምልኮ መበርታቱ ከሱ የሚፈለገውን በጠቅላላ እያሟላ እንደሆነ አስቦ እንዳይኩራራና በራሱ እንዳይመጻደቅ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይልቅ ሰውየው ውስጡ ሊያድር የሚገባው ስሜት ከአምላኩ የሚጠበቀውን አሟልቶ አለመፈጸሙን መገንዘብ ነው፡፡ ይህም በሰራው ስራ እንዳይመጻደቅ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህም ጥፋቱን በመናዘዝ በተደጋጋሚ ‹‹አላህ ሆይ! በአንተ ጥበቃ ስር ሆኘ የሰራኋቸውን ስህተቶች ማረኝ›› እያለ መማጸን ይኖርበታል፡፡ በዚህ ምክንያት አላህ (ሱ.ወ) ‹‹አንተ ነብይ ሆይ! ለስህተትህም ምህረት ጠይቅ›› ሲል አዘዘ፡፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሀዲስ በዚህ መልኩ አላህን ምህረት ይጠይቁት እንደነበር ተገልጸዋል።

ለምሳሌ፦

‹‹አላህ ሆይ! ከዚህ በፊት የሠራኋቸውን ወደ ፊትም የምሰራቸውን ስህተቶች ማረኝ! እንዲሁም በድብቅም በግልጽም የሰራሁትን ስህተቴን ማረኝ!›› ቡኻሪ 5919

ይህ ማለት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በፍቃዳቸው ሀጥያት ይሰሩ ነበር ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሀዲስ የሚሰጠን መልዕክት

‹‹በምድር ላይ ታላቁ የአምልኮ ሰው ቅንጣት ታክል ኩራት ሳይኖርበት ምህረትን የሚለምን ከሆነ እኛ ሀጥያተኞችማ ለዚህ ተግባር ይበልጥ ተገቢዎች ነን›› የሚል ነው።

እኛ ወንጀለኛ ከመሆናችን አንጻር የበለጠ ለዚህ ተግባር መትጋት እንዳለብን ቁምነገር የሚያስጨብጠን ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ማየት የሚኖርብን የበለጠ ሀላፊነቶችን የተሸከመ ሰው መስፈርቱም ለየት እንደሚልበት ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቀጥታ ከአምላክ መለኮታዊ ራዕይ የሚቀበሉ ነብይና በአምላክ የተመረጡ ግለሰብም ነበሩ፡፡ በጊዜያቸው ምንም ሀጥያት አልሰሩም ያም ሆኖ ግን ከመተናነሳቸውን ከአምልኳቸው ብዛት ለክብራቸው ሳይጨነቁ ዝቅብለው ምህረትን ይጠይቁ ነበር፡፡ “እኔስ” የሚለውን አንስቶ ሌላው ራሱን እንዲፈትሽ ያደርጋል፡፡ አስተምህሮቱ ከቃላት በዘለለ እንዲህ በተግባር ሲሆን ይበልጥ ልብ ውስጥ ይሰርጻል፡፡

ከዝህም አልፎ የዚህ ሁሉ አምልኳቸውና መተናነሳቸው ምክንያት በሀዲስ ተቀምጦልን እናገኛለን፦

‹‹ ሙጊራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ፡- የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እግራቸው እስኪያብጥ ድረስ የሌሊትን ሶላት (ስግደት) ይቆሙ ነበር፡፡ አንድ ሰውም እንዲህ አላቸው ‹‹አላህ ያለፈውንም የሚመጣውንም ወንጀል ምሮልዎት የለምን›› እሳቸውም ሲመልሱ ‹‹ታዲያ አመስጋኝ ባሪያ መሆን የለብኝምን›› ቡኻሪ 4459

3. ለተከታዮቻቸው አስተምህሮ ሲባል

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መተናነሳቸውን ለመግለጽና ተከታዮቻቸውም ይህን አስተምህሮ እንዲወስዱ በሚል ምህረትን ሲጠይቁ እናስተውላለን፡፡

‹‹ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ‹‹ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ‹‹በአላህ እምላለሁ በቀን ከሰባ ጊዜ በላይ አላህን ምህረት እየጠየቅኩ ወደርሱ እመለሳለሁ›› ቡኻሪ 5832

ሌላ ዘገባ ይህንን ሀሳብ ይበልጥ ያጠናክርልናል፡፡ ይህ ተግባራቸው ለሰዎች አስተምህሮ እንደሆነ እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፡-

‹‹ ኢብኑ ኡመር(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ‹‹ሰዎች ሆይ! አላህን ምህረት ጠይቁት እኔ በቀን መቶ ጊዜ አላህን ምህረት እጠይቀዋለሁ›› ሙስነድ አህመድ 17173

ከዚህ ጋር በተያያዘ ጉዳዩን ይበልጥ የሚያጠናክረው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለፈውም የወደፊቱም ወንጀላቸው እንደተማረ የሚገልጸው የቁርዐን አንቀጽ የወረደው በ6ኛው ዓመተ ሂጅራ ሲሆን አቡ ሁረይራ የዘገበው በቀን ከ70 ጊዜ በላይ ምህረት እንደሚጠይቁ የሚገልጸውን ሀዲስ የተናገሩት ደግሞ ከ አንድ ኣመት በኋላ በ 7ኛው ኣመተ ሂጅራ ነው፡፡ ይህ የሚያረጋግጥልን የሳቸው ምህረት መጠየቅ ያለምንም ጥርጥር ለተከታዮቻቸው ዓርዓያ ለመሆንና ለማስተማር እንደነበር ነው፡፡

3. የተጠቀመው አረብኛ ቃል ሰፊ ትርጓሜ

በኢስፋሀኒ የተጻፈው ‹‹ሙፋረዳት ፊገሪቢል ቁርዐን›› የተሰኘው መጽሀፍ ‹‹ጋፋር›› የሚለውን ቃል እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፡፡

‹‹ከቆሻሻ ነገር ይጠበቅ ዘንድ መሸፈን›› (1/362)

ይህን ከያዝን ታዲያ አንቀጾቹ ምን እንደሚሉ እንመልከት፡፡ አንቀጾቹ የሚያወሩት በሌላ አገላጽ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሀጥያት ይጠበቁ ዘንድ አላህን (ሱ.ወ) ይማጸኑ እንደነበር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹ዘንብ›› የሚለው ቃል አቻ የአማርኛ ትርጉሙ ‹‹ሀጥያት ወይንም ወንጀል›› የሚል ሲሆን ከላይ በጠቀስነው የኢስፋሀኒ መጽሀፍ እንዲህ ተገልጾ እናገኘዋለን፡፡

‹‹ ማንኛውም የሚያመጣው ውጤት ጥሩ ላልሆነ ተግባር እንጠቀመዋለን›› (1/181)

ይህ የሚያረጋግጥልን ቃሉ በተጨማሪ የሚያገለግለው አንድ ሰው በጠበቀው መልኩ ላልገጠመው ማንኛውም (መልካምም ሊሆን ይችላል) ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ እሳቸውም ያልጠበቁት መልካም ያልሆነ ተግባር እንዳይገጥማቸው አላህን ይማጸኑ እንደነበሩ እንረዳለን፡፡

4. ‹‹ሀጥያት›› ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስንወስደው የነበረው ምንነት

አላህ (ሱ.ወ) በአንድ ወቅት ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) የገሰጸበት ክስተት ጉዳዩን የበለጠ ግልጽ ያደርግልናል፡፡ እንዲህ ይላል፡-

‹‹عَبَسَ وَتَوَلَّىٰ [٨٠:١]
أَن جَاءَهُ الْأَعْمَىٰ [٨٠:٢]
وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّىٰ [٨٠:٣]
أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ الذِّكْرَىٰ [٨٠:٤]

‹‹ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡›› 80፡1-4

ክስተቱ የተፈጸመው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እስልምናን ያልተቀበሉ የመካ ሹማምንት ስለ እስልምና እያናገሯቸው በነበረበት ወቅት ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባ የነበረው ኣይነ ስውሩ አብደላህ ኢብኑ ኡሙ ሙክቱም (ረ.ዐ) ጣልቃ በመግባቱ ውይይቱ ያለፍጻሜ ተጠናቀቀ፡፡ በዚህ ጊዜ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የሱን ጣልቃ መግባት አልወደዱትም ነበር፡፡ ምክንያቱም ከእነኝህ ሰዎች መካከል አንዳቸውም እንኳን ወደ ቅኑ መንገድ ይመራሉ የሚል ተስፋ አዝለው ነበር፡፡ ከመካከላቸው(ከመካ ባላባቶች) የአንድኛቸው እንኳን ወደ ኢስላም መምጣት እየተሰቃዩ ለነበሩት እሳቸውና ባልደረቦቻቸው በትንሹም ቢሆን ስቃዩን የሚቀንስና ከለላ የሚሰጥ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከባልደረቦቻቸው መካከል ጥያቄ ያለው ወይንም መማር የፈለገ በሌላ ሰዐት መጠየቅ እንጂ ያንን እንደ ወርቃማ የሚታይ አጋጣሚ ማደፍረስ አይገባም ነበር፡፡ ግን ባልታሰበ መልኩ የዚህ ሰሀባ ጣልቃ መግባት ውይይቱን አደፈረሰው፡፡ በርግጥ ተግባሩ ቅር የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን በስነ ምግባር ልዕልና ለመጠቁት ነብይ ግን ይህንን እንኳ መሰማቱ ለአላህ አስደሳች አልነበረም፡፡ ስለዚህ ተግባራቸውን ነቀፈ የሳቸው ኒያና ፍላጎት ቅን ነበር፡፡ ግን አላህ (ሱ.ወ) ዘንድ እሳቸው (ሰ.ዐ.ወ) ከሚያናገሯቸው አምባገነን መሳፍንት ይልቅ ዓይነስውሩ ተወዳጅና መልካም ነበር፡፡

ይህ ሀጥያት የሚለው ቃል ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሲደርስ ምን ያህል ደረጃው ከፍ ያለ እንደነበር ያሣያናል፡፡ እናም ሀጥያት ማለት ለሳቸው እነኝህ በመልካም ፍላጎት የተጀመሩ ግና በስህተት የተጠናቀቁ ጥቃቅን ተግባራትን ብቻ ነበሩ፡፡ (ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዓለይሂ)

6. እኛ ደግሞ እንጠይቅ እስኪ

የቁርዐኑ አገላለጽ በዚህ ካስቀመጥን እስኪ መጽሀፍ ቅዱስን ፈትሸን ፍጹም ሰው ብቻ ሳይሆን ፍፁም አምላክ ነው ተብሎ የሚታመነው እየሱስ ምን እንደሰራ በጨረፍታ እንመልከት፡፡

እንደ ማቴወስ ገለጻ እየሱስ ሀዋርያትን ሲያስተምር እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል፡-

“እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤”
— ማቴዎስ 6፥12

በጣም የሚገርመው እዚህ አንቀጽ ላይ ‹‹በደላችንን ይቅር በለን›› የሚለው ቃል የአረብኛ መጽሀፍ ቅዱስ ከፍተን ብንመለከት አቻ የአረብኛ ቃል ‹‹ወግፊር ለና ዙኑበና›› የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ረሱል ሀጥያተኛ ናቸው ተብሎ የቀረቡ አንቀጾች በጠቅላላ ማለት ይቻላል የሚጠቀሙት ቃል ደግሞ ይህንኑ እራሱን ቃል በቃል ነው፡፡

በርግጥ የአንቀጹን አውድ ስንመለከተው ደቀመዛሙርቱን ለማስተማር ያዘዛቸው ቃል እንደሆነ እናያለን፡፡ ነገር ግን በሌላ ቦታ እራሱ እየሱስ ከዚህ ጸሎት ውጭ ሌላ ዓይነት አገላለጽን እንደተጠቀመ የሚገልጽ የለም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ

“በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ።”
— ሉቃስ 3፥3-6

በዚህ አንቀጽ በግልጽ እንደተገለጸው የዮሀንስ ጥምቀት የሐጥያት ስርየት ነበር፡፡ በተለያዩ ቦታዎች ደግሞ እየሱስ በዮሀንስ እንደተጠመቀ ይገልጻል፡፡ ይህ ማለት እየሱስ በዮሀንስ የሀጥያት ስርየት ጥምቀት አድርጓል ማለት ነው፡፡ ካልሆነ ግን ጥምቀቱ ለምን አስፈለገ?

ሌላው ነጥብ

“እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።”
— ማቴዎስ 5፥22

በዚህ አንቀጽ እየሱስ እንደሚነግረን ደንቆሮ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ የገሀነብ ፍርድ ይገባዋል፡፡

በሌላ ቦታ ግን እራሱ እየሱስ ይህንን ስድብ ሲጠቀመው እንመለከታለን፡፡

“እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?”
— ማቴዎስ 23፥19

ተጨማሪ

“እናንት ደንቆሮዎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን?”
— ሉቃስ 11፥40

ታዲያ በዚህ ንግግሩ ምክንያት (አሏህ ﷻ ይቅር ይበለንና) ኢየሱስ የገሀነብ ፍርድ የሚገባው ሀጥያተኛ ነው ማለት እንችላለን?

ማጠቃለያ

ታዲያ እየሱስ ክርስቶስ እንደክርስቲያኖች አጠራር አምላክ የሆነውን ምህረትን ይጠይቅና ደቀመዛሙርቱም ምህረት ይለምኑት ዘንድ ያስተምር ከነበረ አምላክ ሳይሆኑ ሰው የነበሩት ታላቁ ነብይ በተግባር ይህንኑ ማስተማራቸው ልዩነቱ ምን ጋር ነው።

ያምሆኖ የሰው ልጅ ለአምላኩ መተናነስና ዝቅ ዝቅ ማለት እንዳለበት እየታወቀ ነገር ግን የእየሱስ ለሀጥያት ስርየት መጠመቅና “ይቅር በለኝ” ማለት በእውነቱ ከአምላክ የሚጠበቅ ነውን?

በተጨማሪም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መዳንን አስመልክቶ የአስተምህሮታቸው መሰረት መልካም በመስራትና ምህረት በመለመን ላይ ሲሆን ይህን ይህን ማድረጋቸው አስተምህሮቱን በተግባር የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ክርስቲያኖች አገላለጽ መዳን የሚገኘው በእየሱስ መስዋዕትነት በሚገኘው ‹‹ምህረት›› ነው፡፡ ታዲያ እንደ ክርስቲያኖች አገላለጽ ምህረት በዚህ ከሆነ የሚገኘው ምህረት ይጠይቁ ዘንድ ማነሳሳቱ ይበልጥ ተገቢነቱ የማን ነበር፡፡ የየትኛውስ አስተምህሮ ከሀይማኖቱ መሰረት አንጻር ስሜት ይሰጣል
ምናልባት ሚሽነሪዎች ይህችን አንቀጽ ረስተዋት ይሆናል፡-

“አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”
— ማቴዎስ 7፥5

ወሏሁ አዕለም!!!!

55 thoughts on “እውን ነብዩ “ﷺ” ሀጥያትን ሰርተዋልን?”

 1. Very good article! We are linking to this particularly great content on our site. Keep up the great writing.

 2. Very good article! We are linking to this particularly great content on our site. Keep up the great writing.

 3. I’ll right away clutch your rss feed as I can not
  to find your e-mail subscription hyperlink or e-newsletter service.
  Do you have any? Kindly allow me recognize in order that I may subscribe.
  Thanks.

 4. Pingback: Google
 5. Pingback: UV LED Nail Gel
 6. Hi, i think that i saw you visited my weblog thus i came to “return the favor”.I am attempting to find things to enhance my site!I suppose its ok to use some of your ideas!!

 7. Pingback: nytimes
 8. Pingback: norwaytoday
 9. Pingback: dutchnews
 10. Pingback: cphpost
 11. Pingback: gayhub
 12. Pingback: 1xbet android
 13. Pingback: helsinkitimes
 14. Pingback: cbd oil
 15. Pingback: icelandreview
 16. Pingback: thesouthafrican
 17. Pingback: 샌즈카지노
 18. Pingback: mature porn
 19. Pingback: 퍼스트카지노
 20. Pingback: Japanese Porn
 21. Pingback: xnxxx

Leave a Reply

Your email address will not be published.