እውነት የሙሴ ጽላት ሀገራችን ነው ያለው?

የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሙሴ ጽላት እኔ ጋር አለ ወደ ኢትዮጵያም የገባው በንጉሱ ሰለሞን ጊዜ ነው ብላ ታስተምራለች

መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ ከሰለሞን በኋላ 16ኛ ንጉስ በሆነው በኢዮስያስ ዘመነ-መንግስት ታቦቱ እዛው እስራኤል ውስጥ መኖሩን በመፅሐፈ ዜና መዋዕል ላይ ተዘግቧል፦

ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ #አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤

ከእዮሲያስ በፊት ደግሞ ምናሴ በነገሰበት ዘመን ቤተ መቅደሱ ያሉትን እቃወች በሙሉ አውጥቶ ጣኦት አስቀመጠበት

“በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሠራውን የጣዖት የተቀረጸውን ምስል አቆመ።”
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 33:7-8)

ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው በቤቶቻቸው ይዞሩ ነበር በዚህ ምክኒያት ነው በትክሻችሁ ሸክም አይሁንባችሁ ያለው (መፅሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 35:3)

እንግዲህ ኢዮሲያስ የነገሰው ከሰለሞን ሞት ወደ 300 አመት በኃላ ማለት ነው ታቦቱ በዚህ ዘመን እስራኤል ውስጥ ከነበረ ወደ ኢትዮጵያ በሰለሞን ጊዜ ገባ እያለች ምትሰብከን የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ እንዴት ነው ልታስረዳን ምትችለው?

(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ምዕ.36)
———-
17፤ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።

18፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የአለቆቹን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።

19፤ የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠሉ፥ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ።

20፤ ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ፤

መፅሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ 1:54

እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበት ንዋየ ቅዱሳቱን ጥቃቅኑንም ታላለቁንም ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግስት ቤትም ያለውን ሳጥኑን ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ

የእግዚአብሔርን ማደሪያ ቤተ መቅደስም አቃጠሉ የኢየሰሩሳሌምን ቅጥር አፈረሱ ግምባን አቃጠሉ

2 በሀገራችን የኦርቶዶክስ አማኞች ብቻ ተቀባይነት ያለው የብሉይ ኪዳን ተጨማሪ መፅሐፍ በሆነው በመፅሐፈ ዕዝራ ላይ ደግሞ ታቦቱ ከዛ በኃላ እስራኤል በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደጠፍ ይናገራል

መፅሐፈ እዝራ ሱቱኤል ምዕራፍ 9
ቁጥር 21 23

21 ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይም 22 ግናይቱ እንደጠፍ ምስጋናችን እንደቀረ ዘመራ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፍ የህጋች ማደሪያ ታቦተ ፅዮን እንደተማረከች ንዋየ ቅዱሳት አንዳደፉ ምልኮታችን እንደቀረ

23 ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ፅዮን እንደጠፍች ቀረች ከሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን

ታዲያ ታቦቱ በምርኮው ጊዜ ተወስዶ ከጠፍ ዛሬም ከኔ ጋር ነው ብላ ቤተክርስቲያኗ ምዕመኑን ምታታልለው ለምንድን ነው? ካልሆነ ደግሞ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጠው ታሪክ ተረት ብቻ ነው ማለት ነው

ስለዚህ አክሱም ላይ የሙሴ ታቦት የለም በዚህ አይነት የውሸት ተረት ህዝቡን በማታለል የነሱን እምነት ብቻ ቅዱስ አስመስለው ሙስሊሙ እንደዜጋ የሚገባውን መብት የነፈጉ አካላት ለህግ መቅረብ አለባቸው ካልሆነም እስከዛሬ ድረስ ያጭበረበሩትን ህዝብ እውነቱን ተናግረው ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው!

እውነት እነሱ እንደሚሉን ታቦተ ጺዮን አክሱም ላይ ስላለ መስጅድ በመሰራቱ የከተማዋ ቅድስና የሚያረክስ ከሆነ የዳንኪራና የዝሙት ቤቶች ለምን አልተከለከሉም?

(ቢላል ሀበሽ)

ሼር ያድርጉ