አሁን ከሰላት በኋላ የተገለጠችልኝ ቅኔ ናት

ሼር ያድርጉ
377 Views
ኢሊያህ ማህሙድ አሁን ከሰላት በኋላ የተገለጠችልኝ ቅኔ ናት እስኪ ፈታ…ፈታ አድርጓታ!!! ሰሞኑን ጨረቃ ላይ “ሰዎች” ማንጋጠጣቸውን በወፍ በረር ማንበቤ ነው መሰል “ግልጠቱን” ያመጣው ii ሕዝበ ክርስቲያኑ አቅሉን ምን ሰለበው!!!(በተልባ የታጨቀ ወና ባዶ አረገው
ይገርማል፣ ይደንቃል ኣንጋጦ ማደሩ
ኹሉም በየፊናው (ኹሉም ከመንደሩ
ደቂቅ ከአዋቂ ኣንዲት እንኳ ሳይቀር
ሲያፈጥ…ሲቃርም ከሰማይ ቀበሌ ከከዋክብት መንደር
“ታምር” ሊያስወራ ድርቅ ብሎ ክርርር….
መረጃ ቢጠፋ ደርሶ ሚያሸንፍ ( ልብን ሚሰባብር
እያለ አወጀ…
“በጨርቃም ተሳለ ክርስቶስ ሲነከር”