ተምርና መርዝ

ሼር ያድርጉ
905 Views

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)
……
በጹሁፉ የሚዳሰሱ አርዕስቶች

 

🔧 ተምር መመገብ ከመርዝ የሚያድን ከሆነ አሰናንተ ትሞኮሩታላችሁ?

 

🔧 የሀዲሱ ትክክለኛ ትርጓሜ ምንድን ነው?


ከሰሞኑ በአንዳንድ የክርስቲያን ተከራካሪ ወገኖቻችን ለማርቆስ 16:18 ሙግት መከራከሪያ ያገኙ መስሏቸው አንድ ሀዲስን በተደጋጋሚ ሲጠቅሱና በየቦታው ሲያዞሩት ተመልከተናል። የማርቆስ ወንጌል ጭብጥ የሚያወራው አንድ ክርስቲያን በማመኑ ምክንያት መርዝ እንኳን ቢጠጣ እንደማይጎዳው ሲሆን እንደሚከተለው ይነበባል

“፤ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።”
(የማርቆስ ወንጌል 16: 18)

ይህንን አንቀጽ አስመልክቶ መርዝ በመጠጣት ሊያረጋግጥ የሚችል ክርስቲያን ለዘመናት ቢፈለግም አልተገኘም። በተለያዩ ጊዜያትም አንድ ጊዜ “ጌታ አምላክን መፈታተን ነው” ብለው ድክመታቸውን ወደ እግዚአብሄር ሲያስጠጉ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጭራሽ አንቀጹ የፈጠራ ቃል/Forged/ ነው በሚል ከመፅሀፍ ቅዱስ ሲያወጡት ተመልክተናል። የአማርኛ መፅሀፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ቃሉን ከማውጣት ይልቅ እዛው አስቀምጠውት ከታች ግን ይህ አንቀፅ ኦርጂናሉ ላይ እንደማይገኝ መጥቀሱን መርጠዋል 🙂 (የ2000 እትምን ማየት ይቻላል)። ነገር ግን እውቅ የአለም አቀፍ የእንግሊዝኛ የመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉሞች ቃሉ ከነ አካቴው የለም በሚል መፅሀፉ ውስጥ አለማካተትን መርጠዋል።

ይህ እንግዲህ ምናልባት መርዙን ላለመጠጣት ከሚደረገው ጥረት አንዱ ክፍል ሊሆን ይችላል። ተያይዞ ያሉ እባብ መያዝ፣ አዲስ ቋንቋ መናገርም ቀላል የሚባሉ ፈተናዎች አይደሉምና መላ መፈለጋቸው ትክክለኛ አካሄድ ሊሆን ይችላል።

ለመግቢያ ይህንን ካልን ወደተነሳንበትና ምላሽ ወደምንሰጥበት ርዕስ እንመለስ። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ሀዲስ ከዚህ በታች አስቀምጨ ለማብራራት እሞክራለሁ።

ሰዓድ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል “አንድኛችሁ ጥቂት የ”አጅዋ” ተምርን በየጧቱ ከተመገበ በዛው ቀን ከመርዝ ወይንም ከድግምት እስከ ምሸት ድረስ ይጠበቃል”

ይህንን ሀዲስ ካስቀመጡ በኃላ በኩራት መንፈስ “ሰባት አጅዋ ተምር ከበላችሁ በኃላ መርዝ ትጠጣላችሁ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።

⛅ እነሆ ምላሹ

በአሁኑ ሰአት ካሉ የአብዛኛው ሰው የተሳሳተ አመለካከት ውስጥ አንዱ የሀዲስ ትርጉምን በማንበብ ብቻ ሀዲስ ያወቁ የሚመስላቸው ጉዳይ ነው። የሆነች የሀዲስ ትርጉም ካዩ ከነሱ የበለጠ ተንታኝና አዋቂ ያለ አይመስላቸውም። ይህ ፈጽሞ የተሳሳተና ሎጂኩን የሳተ አካሄድ ነው። የትኛውም የታሪክ ሁነትን ለማወቅ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ቀዳሚው መርህ የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታና ታሪካዊ አውዱን ቀድሞ መረዳት ነው።

ሀዲሶቹ ከላይ ከገለጽኩት በተጨማሪ የሚከተሉት ናቸው።

🍒 Sa’d told of hearing Allah’s Messenger say, “He who has a morning meal of seven ‘ajwa dates will not suffer harm that day through toxins or magic.” (Bukhari, Hadith 5327 and Muslim, Hadith 3814)

🍒 ‘Aisha reported Allah’s Messenger as saying, “The ‘ajwah dates of al-‘Aliya contain healing, and they are an antidote (when taken as) first thing in the morning.” (Muslim, Hadith 3815)

🍒 ‘Aisha reported Allah’s Messenger as saying, “The ‘ajwah dates of al-‘Aliya taken as the first thing in the morning, in the state of fasting; contain healing for all (kinds of) magic or toxins.” (Musnad Ahmad, Hadith 23592)

እዚህ ሀዲስ ላይ እንደተቀመጠው የ”አል ዓሊያ” አጅዋ ተምር ተብሎ የተገለጸው በምስራቃዊ መዲና ጥቂት ማይሎች ርቀት የምትገኘዋ የዓሊያ መንደር ውስጥ የሚበቅለው የተምር አይነት ነው።

🍒Narrated ‘Urwah: ‘Aisha used to order to make a habit of or taking in regular intervals seven ‘ajwah dates, in the state of fasting for seven mornings. (Musannaf Ibn Abi Shayba, Hadith 23945)

እነዚህን ክስተቶች ከግምት አስገብተን ሀዲሶቹን ስንመለከታቸው የተምሮቹ ጠቃሚነት በሚከተሉት ነጥቦች ውስጥ የተጠቃለሉ ናቸው።

1- ሀዲሶቹ የሚያወሩት በተናጠል ስለ አጅዋ ተምር ሲሆን የሚገኘውም በመዲና አቅራቢያ በምትገኘው ዓሊያ ከተማ የሚበቅለውን ነው።

2- ጠቃሚነቱም በጠዋት ለሚመገበው ሰው እና ፆሙን ለሚፈታበት ሰው ነው።

3- ጠቃሚነቱ በቋሚነት ለሚመገበው ሰው ነው። (ልክ ዓዒሻ እንዳዘዘችው)

⛅ እነዚህን ነጥቦች ከግምት ካስገባን በኃላ ዘለቅ ብለን ጥቂት ነገሮችን ላብራራ

♨ መርዝ ወይንም ጎጂ ነገር የሚለው ቃል የአረብኛ አቻ ትርጉሙ “ሱም” የሚል ነው። የአንዳንድ ሰዎች ትልቁ ያለመረዳት ችግር ታዲያ እዚህ ጋ ነው። ቃሉን ወዲያውኑ በትርጉም ጥራዞች ውስጥ ሲሰሙ ገዳይ ንጥረ ነገሮች ወደ አእምሯቸው ይመጣሉ። ሀዲሱ ግን “ሱም” ብሎ የሚገልጸው ለሰውነታችን ጎጂ የሆኑና ውስጣችን ውስጥ በመቆየት ለህመም የሚዳርጉንን አካላት አስመልክቶ ነው። ከዚህ በታች ያለውን የአረብኛ እንግሊዝኛ ፍች ለማስረጃነት ይመልከቱ

Al-Mawarid Arabic-English Dictionary Dar el-Elm Lilmalayin, Beirut 1995 p.642

ኢማም ኢብኑል ቀይም በ”ጢበ ነበዊ” ድርሳናቸው እንደገሚገልጹት

“ለሌላ አካባቢ ሰዎች ስንዴ ቋሚ የቀለብ ምግባቸው እንደሆነው ሁሉ ለመዲና ሰዎች ደግሞ ተምር ቋሚ ምግባቸው ነው። በተጨማሪም በዓሊያህ አካባቢ የሚገኘው ደረቅ ተምር ደግሞ ተመራጭ ነበር። ይህ ተምር ለሀገሬው ሰው ከምግብነት በተጨማሪ የመድሀኒትነት ግልጋሎትም ነበረው። ለሰውነት ምቹ ከመሆኑ በተጨማሪ ሙቀትና ሀይል ሰጭ ይዘትም አለው። ከዚህም በተጨማሪ ተምሮች እንደሌላ ፍሬዎች ተያያዥ መርዛማ ንጥረ ነገሮች የሏቸውም። ከዚያ ይልቅ በሰውነታችን ሊወገዱ የሚገባቸው ጽዳጆች መርዛማ ሆነው እንዳይጎዱን የመከላከል ጥቅም ይሰጣል። (Healing with the Medicine of the Prophet, Translated by Abd el-Qader bin Abd el-Azeez, Dar al-Ghadd al-Gadeed, al-Mansoura (Egypt), 2003 p.121)

ከዚህ በታች ሀሳቡን የሚያብራሩ ጥቂት ተጨማሪ ዘገባዎች ላስቀምጥ

ሰዓድ ባስተላለፉት ሀዲስ ፦ በአንድ ወቅት በበሽታ ተጠቃሁ፤ የአላህ መልዕክተኛም (ሰዐወ) ሊጠይቁኝ መጡ። እጃቸውን ደረቴ ላይ አስቀመጡት በዚህም ልቤ ላይ ቅዝቃዜ ተሰማኝ። ከዚያም እንዲህ አሉ “አንተ በልብ ህመም የተጠቃህ ሰው ነህ፤ የሰቂፍ ወንድም ወደሆነው ወደ ኻሪስ ኢብን ካላዳህ ሂድ። እሱ ህክምናውን ይሰጣል። ሰባት አጅዋ ተምሮችን ይውሰድና ከነፍሬው ይፍጫቸው ከዚያም እነሱን ተመገባቸው። (ሱነን አቡ ዳውድ 3875

በተመሳሳይ ሰንሰለቱ ደካማ በሆነ ሀዲስ እንደተላለፈው

“አሊይ (ረ.ዐ) ሲናገር፦ በየቀኑ ሰባት አጅዋ ተምሮችን የተመገበ በሆዱ ውስጥ ያለን በሽታ ይገልለታል።” (ከንዙል ኡማ ሀዲስ ቁጥር 28472)

ይህ እንደሚጠቁመን ለልብ በሽታና ለሆድ ውስጥ በሽታዎች ፈዋሽነት እንዳለው ነው። ይህ ደግሞ ሳይንሳዊ እውነታ ነው። የቅርብ ጊዜ ሳይንሳዊ እውነታዎች እንደሚነግሩን ደግሞ ተምር የልብ አርተሪዎችን ይጠብቃሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ የልብ ድካም አደጋን የመቀነስ ጉልህ አስተዋፅኦም አላቸው። አብዛኛው የልብ በሽታዎች አምጭ የሆነው ኮሎስትሮል በራሱ ጎጂ ንጥረ ነገር ነው። ከዚህም በተጨማሪ የተምር ተዋፅኦዎች የምግብ ስርአተ ሽርሽር ሂደትን/Digestive system/ ሊያደናቅፉ ለሚችሉ ችግሮች መፍትሄ በመሆን ፈውስነታቸው የተረጋገጠ ነው።

⛅ አስማት

አስማትን አስመልክቶ በሁለት መልኩ ማብራራት የሚቻል ሲሆን የመጀመሪያው የቃል በቃል ትርጉምን መሠረት አድርገን የምናወራ ከሆነ አስማትን አስመልክቶ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ጥናትና ግኝት ባለመኖሩ በመርህ ደረጃ ተቃውመን ሀሳብ ማቅረብ አንችልም። በሁለተኛ መልኩ የምናብራራው የአስማትን ምንነት በመተንተን ነው። ይኸውም “ሲኽር” ወይንም አስማት የአረብኛ ገለጻው የጤና ሁኔታን ለሚቀይሩ በሽታዎችም አገልግሎት ላይ ይውላል E.W. Lane’s Lexicon Book I p.1316 መመልከት ይቻላል። ይህ ማለት ደግሞ ከላይ የገለጽናቸውን በሽታዎች ጭምር ለመጠቆም አገልግሎት ላይ ይውላል ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሁለቱን ለመለየት ሀዲሱ የሚጠቀመው መለያ “ወይንም” “Or” የሚለውን ቃል ነው። ይህም በተዘዋዋሪ ማስረጃውን አጠናካሪ ነው። ከዛም በተጨማሪ ለተለያዩ ጨረሮች ተከላካይ የሆኑ ካሌሺየም፣ ማግኒዥየም፣ ሴሌኒየም፣ ዚንክና ቪታሚን ሲ የመሳሰሉ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ አቅፎ ይዟል።

🍒 ማጠቃለያ

⛅ ሁለቱ ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች በዋናነት ትኩረት አድርገው የሚገልጹት በአል ዓሊያህ አካባቢ የሚበቅለውን ተምር አስመልክቶ ሲሆን ጠቃሚነቱም ከአካባቢው ውስን የከባቢ አየር ጠቀሜታ አንፃር የተገለጸ ነው።

⛅ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን አስመልክቶ ተምር ፈዋሽነቱ ጥርጥር የለውም።

⛅ የሀዲሱ ዘገባ የሚገልጸው የዓሊያ ተምር በመደበኛ ሁኔታ ጧትና ማታ በተከታታይ ሰሰለሚመገቡ ሰዎች ሲሆን እነዚህ ሰዎች ይህን በማድረጋቸው ከሆድ ውስጥ በሽታዎች እንዲሁም ከልብ ችግሮች እንደሚከላከል የሚገልጹ ናቸው።

ወሏሁ አዕለም.! .

Shortlink http://q.gs/Ewics