ብላኤ ሰብእ ትዕዛዛት- ዘክርስቲያን

ሼር ያድርጉ
478 Views

ኢሊያህ ማሕሙድ{አንድ}
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነው ጀምረን እንቀጥላለን፡፡

ወዳጄ እንደምን ከረሙ? ሀገራችን ኢትዮጲያ ዛሬም እንደወትሮው በአረንቋ እየተገረፈች ነው፡፡ ሁላችንም በያለንበት ኢትዮጵያን በጸሎት እናስብ፤ አላህ ለተጠበበ ደራሽ ነውና ይሰማን ይሆናል፡፡ ወዳጄ ዛሬና በሚቀጥሉት ጽሁፎቼም እማወጋዎ “ብላኤ ሰብእ ትዕዛዛት” በሚል ርእስ ሲሆን ትርጓሜውም “ሰው በሊታ ትዕዛዞች” እንደ ማለት ነው፡፡ ክርስቲያን ወገኖች ኢስላምን በዳይ ለማስመሰል ምስሎችን ሲለጥፉና ጥቅሶችንም በራሳቸው የማጠጋጋት ግንዛቤ ሊያብራሩ ሲሞክሩ አነበብኩ፡፡ እውይ! እውይ!… አልኩና ይህችን ጽሁፍ ላካፍሎት መልካም መስሎ ታየኝ፡፡ ጉልበቴም በረታ፡፡

ዘፍ 16/6-9 አብራምም ሦራን፦ እነሆ ባሪያሽ በእጅሽ ናት፤ እንደ ወደድሽ አድርጊባት አላት። ሦራም ባሠቀየቻት ጊዜ አጋር ከፊትዋ ኮበለለች።… የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፤… የእግዚአብሔር መልአክም፦ ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ አላት።ወዳጄ ልብ ይበሉ! የአምላክ ነቢይ የሆነው አብራሃም (ዐ.ሰ) ኢፍትሃዊ በሆነ መልኩ ያረገዘችለትን ሚስቱን ለሌላኛይቱ ሚስቱ እደፈለግሽ አርጊባት ብሎ አሳልፎ እንደሰጠ መጽሃፉ እየነገረን ነው፡፡ በትክክል የአምላክ ነቢይ እና ጻዲቅ አይደለም በሚስቶቹ መካከል በህዝቦች መካከል እንኳ ፍትህን ለማስፈን ይጥራል! ጥረቱ እስከ ደም መፍሰስ ሊደርስ ይችላል፡፡ እዚህ ጋር መጽሀፉ የሚያስነብበን ግን በሚስቶቹ መካከል እንኳ ፍትህን ማስፈንና የቅናቻን መንፈስ ማስቀረት አልቻለም፡፡ ይልቁንም በቅናት መንፈስ ለተንቀለቀለው የሶራ አመለካከት የአብራሃም ቸልተኝነትና ኢፍትሃዊ “አባወራነት” ማገዶ ሲሆን እናያለን፡፡

ወዳጄ ምናልባት አብራሃም ስጋ የለበሰ ሰብኣዊ ነው የሚል አስተሳሰብ ውል ሊልቦ ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ዘፍ 20/6 ላይ እንደምናነበው አብራሃም የአምላክ ነቢይ ሆኖ በመለኮታዊ ኀይል የሚመራ ነበር፡፡ ታዲያ በመለኮታዊ ኀይል የሚመራ ነቢይ የዚህ አይነት ኢፍትሃዊ አመለካከት እንዴት ሊያድርበት ቻለ የሚል ሌላም ጥያቄ አእምሮ ውስጥ ሊመላለስ ይችላል፡፡ እውነት እውነት እሎታለሁ ጥያቄዎ የኔም ጥያቄ ነው፡፡ አብራሃም ያስተላለፈውን ኢፍትሃዊ ትዕዛዝ ከአምላክ “የተላከውም” መልአክ እንዲህ ሲል ይደገፈዋል “ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ” እኔ ገና ይህንን ታሪክ ዘፍጥረት ላይ ማንበብ ስጀምር እጠብቅ የነበረው የአምላክ መልአክ መጥቶ አጋርን ያበረታታል፤ ሳራንም ለፈጸመችው የቅናት በደል ይገስጻታል፤ አብራሃምንም ከስህተቱ እንዲታረም ይመክራል፤ የሚል ወዘተና አከተ ተመጣጣኝ ፍርድ ነበር፡፡ ይሁንና ከአምላክ የተላከውም መልአክ ተመለሺና እንደገና የባርነት ቀንበርሽን ተሸከሚ የሚል ሆነ፡፡

እንቀጥላለን ቸር እንሰንብት!!

Shortlink http://q.gs/Eye4e