በሰዎች ስርዓት የሚመለክ ክርስቲያናዊው አምላክ

ሼር ያድርጉ
544 Views
ኢሊያሕ ማሕሙድ የአላህ ሰለም ቀጥተኛ መንገዱን በተከተሉ ላይ ይሁን! አሜን፡፡ ወዳጄ! ዛሬ የኢትዮጵያ ክርስቲያን አምላክ ከሞተበት ተነሳ በሚል እያከበረ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ወዳጄ ይህ የአምላክ መሞት፣ ሶስት ቀን በምድር ልብ መቆየት ከዚያም ሞትን ድል አድርጎ መነሳትን ማረግ ክርስትና ከሌሎች ቀደምት እምነቶች የወሰዳቸው ጽንሰ ሀሳቦች እንጂ የራሱ እንዳልሆኑ ትናንትና በለጠፍኩት ጽሁፍ ፍንጭ ያገኙ ይመሰልኛል፡፡ለምሳሌ የጥንታዊ ግብጽ አምላክ ተብሎ የሚታሰበው ሆረስ ከመወለዱ በፊት መላእክት ለእናቱ አይሲስ መቶ አበስሯታል፡፡ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ኢሪዳኑስ ወንዝ ውስጥ በሰላሳ ዓመቱ አናፕ በሚባል ሰው እንደተጠመቀና በአጠቃላይ አስራ ሁለት ደቀ-መዛሙርት እንደነበሩት፤ ታላላቅ ታምራትን ለምሳሌ በውሃ ላይ መራመድ፣ አይነ-ስውርን ማብራት፣ የሞተን መቀስቀስ ወዘተ እንዳደረገና በስተመጨረሻ በስቅላት እንደተቀጣ፣ ከሶስት ቀን ሞት በኋላ ወደ አባቱ ኦሲስ እንዳረገ ወዘተ አይተናል፡፡ ወዳጄ አይገረሙ! ይህ ለእየሱስ የተሰጠው ታሪክ ከሆረስ ጋር ብቻ ሳይሆን ከነ ክሪሽና፣ ሚዝራ፣ በድሩ ወዘተ አረማውያን ያምኑባቸው ከነበሩ አማልክት ታሪክ ጋር ይዛመዳል፡፡ እነዚህ እምነቶች ሁሉም ከክርስትና በመቶዎችና በሺ ዘመናት የቀደሙ ናቸው፡፡ ከዚህ አኳያ አብዛኛው የክርስትናው ታሪክ ከየት እንደመጣ ግልጽ ይሆናል፡፡ አላህ በቃሉ እንዲህ ይላል፡- አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አለች፡፡ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡ ይህ በአፎቻቸው (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡ አላህ ያጥፋቸው፡፡ (ከእውነት) እንዴት ይመለሳሉ! 9/30ይህ የቁርአን ጥቅስ የሚነገርን አይዶችን ክርስቲያኖች በራካት ከቀደምት እምነቶች ጽነሰ-ሃሳቦችንና አመለካከቶችን እንደወሰዱ ነው፡፡ በተለይ የክርስትናው ዓለም ከቀደምት አረማውያን በርካታ ነገር ወስዶ የራሱን ጨምሮ “እምነት” ሚመስል ነገር ፈጥሮ ይኖራል፡፡ በቀላሉ ለማየት ሰሞኑን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ሲጾሙት የነበረው ጾም መረጃ ከመጽሀፋችሁ እንፈልጋለን ስንል “ ሲኖዶስ… ወዘተ ተስማምቶ” የሚሉ መልሶችን እናገኛለን፡፡ የኛ ጥያቄ እምነቱ ሙሉ ስላልሆነ ነው ሰዎች ተስማምተው አምልኮ የሚፈጥሩለት? ስንል “እየሱስ አርባ ቀንና ሌሊት ተራበ ስለዚህ እኛም…” የሚሉ መልሶችን እናነባለን፡፡ አስከትለንም እንዲህም ብለን ጠየቅን እየሱስ አርባ ቀንና ሌሊት ጾመ ማለት ሃምሳ አምስት ቀን ማለት ነው? ለሊቶቹ የት ገቡ? “አይ እሱ በስጋ አይደለም የጾመው” የሚል መልስ ሰማን፡፡ እኛም ታዲያ በስጋ ካልሆነ በመንፈስ መጾም ምን ማለት ነው? ብለን ጠየቅን፡፡ ደግመንም እንተይቃለን፡፡ አስከትለንም ለመሆኑ እየሱስ በየትኛው ወር ነበር የጾመው? ብለን ጥያቄአችንን እናጠናክራለን፡፡ ወዳጄ የኦርተዶክሱ ሀይማኖት ከዚህ ውጭ ሌሎች በርካታ አጻማት አለው፡፡ ጥያቄው ግን አሁንም እነዚህ አጻማት ከየት መጡ፤ መረጃቸው ምንድን ነው? የሚል ነው፡፡ ትንቢተ ኢሳያስን ገርመም ስናደርግ “ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈርቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና” 29/13 የጥቅሱን የመጨረሻ ዓ/ነገር ስናነብ “በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና” የሚለው ሰዎች በሰዎች ስርዓት ወደ ፈጣሪ እንቃረባለን ብለው እንደሚያስቡ ነገር ግን ያ ከንቱ ልፋት እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ታዲያ ክርስቲያን ወገኖች እስኪ ቆም ብላችሁ አስቡ፤ ሰዎች ምን ያህል ሰዎችን አውቀው ነው ህግ ሚያስቀምጡላቸው? ስትጾም ይህንን ብላ ይህንን አትብላ ወዘተ መጽሀፉ ራሱ ካላዘዘ ሰዎች ምን ቆርጧቸው ነው ይህንን ህግ የሚያወጡት? ተመልከቱ ወዳጄ ይህ የክርስትና እምነት ፈጣሪ ለዓለም ሀዝብ የመረጠው ነው ብለው ይነግሩናል፤ እንደዚያ ከሆነ ለምሳሌ በሰሜንና ደቡብ ዋልታ የሚገኙ የበረዶ ሰዎች ምግባቸው ስጋ ብቻ ነው፡፡ አድነው የሚያገኙትን ስጋ በረዶ ውስጥ በማቀዝቀዝ ይመገባሉ፡፡ የአፋርና የሱማሌ ዘላኖች ምግባቸው ወተትና አልፎ አልፎ ስጋ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቢሆኑ ምን በልተው ሊጾሙ ነበር? ወይስ ለነሱ ህጉ እንደ አሳው ህግ ይሻሻላል? ቸር እንሰንብት