በመላእክት ማመን ክፍል አስራ አራት በአቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
349 Views

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
5/ የመላእክት የስራ ድርሻቸው፡-
ረ/ በሰው ላይ ኃላፊነት የተሰጣቸው፡-
7/ የቀብር ጥያቄና መልስ፡-
ሰው ከሞተ በኋላ የውሙል ቂያም እስከሚቀሰቀስ ድረስ ያለው ጊዜ “ዓለሙል በርዘኽ” ‹የግርዶው ዓለም› በመባል ይጠራል፡፡ ተመልሶ ወደ ዱንያ መምጣት አይችልም፡፡ በቀንዱ ተነፍቶ እስከሚቀሰቀስበት ቀን ከመቃብር ዓለም ወደየትም መሄድ አይችልምና፡፡
” حَتَّى إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ * لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ كَلَّا إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا وَمِنْ وَرَائِهِمْ بَرْزَخٌ إِلَى يَوْمِ يُبْعَثُونَ ” سورة المؤمنون 100-99
“አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡ በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ (ጌታዬ ሆይ! መልሱኝ ማለቱ) እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ #ግርዶ አልለ፡፡” (ሱረቱል ሙእሚኑን 23፡99-100)፡፡
በቀብር ውስጥ የመላእክት ጥያቄና የኛ መልስም ይኖራል፡፡ ደግሞም ቅጣትና ጸጋ (ኒዕማ) መኖሩንም አምነን እንቀበላለን፡፡ ሟች በቀብር ውስጥ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፡፡ እነሱም፡- ጌታህ ማነው?፣ ወዳንተ የተላከልህ መልክተኛ ማነው?፣ ሃይማኖትህስ ምንድነው? የሚሉት ናቸው፡፡ ቀጣዩ ነቢያዊ ሐዲሥ ይህንን ያስረዳል፡-
أخرج البخاري في صحيحه: عن أنسِ بنِ مالكٍ رضيَ اللهُ عنه أنّهُ حدَّثَهم أنّ رسولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قال «إنَّ العبدَ إذا وُضِعَ في قبرهِ وتولَّى عنه أصحابُه ـ وإنّه ليَسمَعُ قرعَ نِعالهِم ـ أَتاهُ مَلَكانِ فيُقعدانِه فيقولانِ: ماكنتَ تَقولُ في هذا الرجُلِ؟ لمحمدٍ صلى الله عليه وسلم. فأمّا المؤمِنُ فيقولُ أشهدُ أنهُ عبدُ اللهِ ورسولهُ. فيقال له: انظُرْ إلى مَقْعَدِك مِنَ النّارِ، قد أبدَلَكَ اللهُ بهِ مَقعداً منَ الجنةِ، فيراهُما جميعاً» قال قَتادةُ: وذُكِرَ لنا أَنَّهُ يُفسَحُ لهُ في قبرِهِ. ثم رَجَعَ إلى حديثِ أنس قال «وأمّا المنافِقُ فيقالُ لهُ: ماكنتَ تقولُ في هذا الرجُلِ؟ فيقول: لاأدري، كنتُ أقولُ مايقولُ الناسُ. فيقال: لادَرَيتَ ولاتَلَيَتَ. ويُضرَبُ بمطَارِقَ من حديدٍ ضَربةً، فيَصيحُ صيحةً يَسمعُها مَن يَليهِ غيرَ الثَقلَينِ» .
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አንድ የአላህ ባሪያ ቀብር ገብቶ፡ ቀባሪዎቹም ከቀብር ሲመለሱ የጫማቸውን ኮቴ ይሰማል፡፡ ሁለት መልአኮችም ወደሱ ዘንድ ይመጡና ያስቀምጡታል፡፡ ስለ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምን ትላለህ? በማለት ይጠይቁታል፡፡ ሙእሚን ከሆነ፡ ‹‹እሳቸው የአላህ መልክተኛና ባሪያው መሆናቸውን እመሰክራለሁ!›› በማለት ይመልሳል፡፡ ከዛም፡- ከእሳት ወደነበረው መቀመጫህ ተመልከት! አላህ ከጀነት በሆነ መቀመጫን ቀየረልህ እንጂ! ይሉታል፡፡ እሱም ሁለቱንም መቀመጫዎች ያያቸዋል፡፡ ቀብሩም ሰፊ ይደረግለታል፡፡ ሙናፊቅ የነበረው ሰው ደግሞ፡- ስለ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምን ትላለህ? በማለት ሲጠይቁት፡ ‹‹አላውቅም! ሰዎች ይሉ የነበረውን ብቻ እል ነበር›› በማለት ይመልሳል፡፤ አላወቅህም? አላነበብክም (ያወቁትንም አልተከተልህም?) ይሉትና በመዶሻ አናቱን አንዴ ይመቱታል፡፡ እሱም አንዴ ጩኸትን ይጮኻል፡፤ ከሰውና ከጂንኒ ውጭ ያለው ሁሉ ይህን ጩኸት ይሰማዋል” (ቡኻሪይ 1273)፡፡
عَنِ ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ: «إِنَّ أَحَدَكُمْ إِذَا مَاتَ عُرِضَ عَلَيْهِ مَقْعَدُهُ بِالْغَدَاةِ وَالْعَشِىِّ: إِنْ كَانَ مِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ؛ فَمِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ، وَإِنْ كَانَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ؛ فَمِنْ أَهْلِ النَّارِ، يُقَالُ: هَذَا مَقْعَدُكَ حَتَّى يَبْعَثَكَ اللَّهُ إِلَيْهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ. متفق عليه: البخاري 1379 ، و مسلم 286 ]
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ከናንተ አንዳችሁ በሞተ ጊዜ፡ ሁሌም በጠዋቱና በምሽቱ መቀመጫው ይቀርብለታል፡፡ የጀነት ነዋሪ ከሆነ፡ ከጀነት ነዋሪዎች የሆነ ማረፊያውን፣ ከጀሀነም ሰዎች ከሆነ ደግሞ፡ ከጀሀነም ሰዎች የሆነ ማረፊያውን ያያል፡፡ ‹‹አላህ እስኪቀሰቅስህ ድረስ፡ ይህ የወደፊቱ ማረፊያህ ነው›› ይባላል” (ቡኻሪይ 1379፣ ሙስሊም 1286)፡፡
ይህንን ኃላፊነት ወስደው በቀብር ውስጥ ሟችን የሚጠይቁት መልአኮች ‹‹ነኪር›› እና ‹‹ሙንከር›› (ዐለይሂማ-ሰላም) በመባል ይታወቃሉ፡፡
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( إِذَا قُبِرَ الْمَيِّتُ أَوْ قَالَ أَحَدُكُمْ أَتَاهُ مَلَكَانِ أَسْوَدَانِ أَزْرَقَانِ يُقَالُ لأَحَدِهِمَا الْمُنْكَرُ وَالآخَرُ النَّكِيرُ ، فَيَقُولَانِ : مَا كُنْتَ تَقُولُ فِي هَذَا الرَّجُلِ ؟ فَيَقُولُ مَا كَانَ يَقُولُ : هُوَ عَبْدُ اللَّهِ وَرَسُولُهُ ، أَشْهَدُ أَنْ لا إِلَهَ إِلا اللَّهُ ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ . فَيَقُولانِ : قَدْ كُنَّا نَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُولُ هَذَا ، ثُمَّ يُفْسَحُ لَهُ فِي قَبْرِهِ سَبْعُونَ ذِرَاعًا فِي سَبْعِينَ ، ثُمَّ يُنَوَّرُ لَهُ فِيهِ ، ثُمَّ يُقَالُ لَهُ : نَمْ ، فَيَقُولُ : أَرْجِعُ إِلَى أَهْلِي فَأُخْبِرُهُمْ ، فَيَقُولَانِ : نَمْ كَنَوْمَةِ الْعَرُوسِ الَّذِي لا يُوقِظُهُ إِلا أَحَبُّ أَهْلِهِ إِلَيْهِ حَتَّى يَبْعَثَهُ اللَّهُ مِنْ مَضْجَعِهِ ذَلِكَ .
وَإِنْ كَانَ مُنَافِقًا قَالَ : سَمِعْتُ النَّاسَ يَقُولُونَ فَقُلْتُ مِثْلَهُ لا أَدْرِي . فَيَقُولَانِ : قَدْ كُنَّا نَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُولُ ذَلِكَ ، فَيُقَالُ لِلأَرْضِ : الْتَئِمِي عَلَيْهِ ، فَتَلْتَئِمُ عَلَيْهِ ، فَتَخْتَلِفُ فِيهَا أَضْلاعُهُ ، فَلا يَزَالُ فِيهَا مُعَذَّبًا حَتَّى يَبْعَثَهُ اللَّهُ مِنْ مَضْجَعِهِ ذَلِكَ ) والحديث حسنه الألباني في صحيح الترمذي .
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ሟች (ከናንተ አንዳችሁ) በተቀበረ ጊዜ፡ አይናቸው ሰማያዊ መልካቸው በጣም የጠቆረ የሆነ ሁለት መልአኮች ይመጡታል፡፡ አንደኛው ‹‹ነኪር›› ሲባል፡ ሌላኛው ደግሞ ‹‹ሙንከር›› ይባላል፡፡ ስለዚህ ሰው (ስለ ሙሐመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምን ትል ነበር? በማለትም ይጠይቁታል፡፡ እሱም (በዱንያ) ይል የነበረውን እንዲህ ይላል፡- ‹‹እሳቸው የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው፡፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩንና፡ ነቢዩ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛና ባሪያው መሆናቸውን እመሰክራለሁ››፡፡ መልአኮቹም፡- አንተ ይህን እንደምትመልስ በርግጥ እናውቅ ነበር!! ይሉታል፡፡ ከዛም ቀብሩ ከፊትም ከጎንም ሰባ ክንድ ያህል ይሰፋለታል፡፡ ብርሀንም ይደረግለታል፡፡ ከዛም ‹‹አረፍ በል! ተኛ›› ሲሉት፡ ‹‹ወደቤተሰቦቼ ልመለስና ልንገራቸው!›› ይላል፡፡ እነሱም ‹‹ከቤተሰቡ እሱ ዘንድ በጣም የተወደደው ሰው እንጂ ከእንቅልፉ ማንም እንደማይቀሰቅሰው ሙሽራ ተኛ!፡፡ አላህ ከዚህ ማረፊያህ እስኪቀሰቅስህ ድረስ›› ይሉታል፡፡ ሙናፊቅ ከሆነ ደግሞ የተጠየቀውን ሲመልስ፡- ‹‹ሰዎች የሚሉትን ሰምቼ አልኩ እንጂ አላውቅም!›› ይላል፡፡ እነሱም ‹‹ይህን እንደምትል በርግጥ እናውቅ ነበር!›› ይሉታል፡፡ ምድርንም ‹‹አጣብቂው!›› ትባላለች፡፡ ሰውነቱን ስታጣብቀው አጥንቶቹ በመላ ቦታቸውን ለቀው ይቀያየራሉ፡፡ አላህ እስኪቀሰቅሰው ድረስ በዚህ መልኩ ከመቅቀጣት አይወገድም” (ቲርሚዚይ 1071)፡፡
አላህ ከቀብር ፈተናና ቅጣት ይጠብቀን፡፡
ይቀጥላል