በመላእክት ማመን ክፍል ስድስት በአቡ ሀይደር

ሼር ያድርጉ
511 Views

ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
5/ የመላእክት ግላዊ ስሞች እና የስራ ድርሻቸው፡-
መላእክት አላህ ለሚፈልገው ዓላማ የፈጠራቸው ባሮቹ ናቸው፡፡ ሁሌም እሱን በመገዛትና በማምለክ ተግባር ላይ የተጠመዱ ናቸው፡፡ በዚህ ፍጥረተ ዓለም ጉዳይ ላይም ኃላፊነትን በማሸከም ትእዛዝ ሰጥቷቸዋል፡፡ በሱ መሪነትና ተቆጣጣሪነት የፈለገውን ነገር እንዳዘዛቸው ይፈጽማሉ፡፡ ከትእዛዙ ለአፍታ እንኳ ፍንክች አይሉም፡፡ በራሳቸው ግላዊ ፈቃድም አንዳች ነገር ማድረግ አይችሉም፡፡ ከነዚህ የስራ ድርሻ ከተሰጣቸው መላእክት መካከል የተወሰኑትን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
ሀ/ ወሕይ (መለኮታዊ ራእይን ማውረድ)፡-
በጌታ አላህና በመረጣቸው ነቢያት/መልክተኞች መካከል ተላላኪ በመሆን ይህን ግዳጅ የሚወጣው መልአክ ጂብሪል/ጂብራኢል (ዐለይሂ-ሰላም) ነው፡፡ መለኮታዊ ራእይን (ወሕይን) ከአላህ በመቀበል አድርስ ወደተባለው ነቢይ/ረሱል በታማኝነት ያደርሳል፡፡ በዚህ ተግባሩም ‹‹አል-አሚን›› (ታማኙ) የሚልን የክብር ማእረግ ከጌታው አላህ ዘንድ ተቀብሏል (ሱረቱ-ተክዊር 81፡21፣ ሱረቱ-ሹዐራእ 26፡193)፡፡
ቅዱስ ቁርኣንንም ከአላህ ዘንድ ኃላፊነትን ወስዶ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ እንዲያደርስ የተመረጠው ይኸው መልአክ ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
” قُلْ مَنْ كَانَ عَدُوًّا لِجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَى قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَى لِلْمُؤْمِنِينَ ” سورة البقرة 97
“ለጂብሪል (ለገብርኤል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፡፡ እርሱ (ቁርኣኑን) ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 2፡97)፡፡
– መጠሪያ ስሞቹ፡- ይህ መልአክ የሚጠራባቸው ብዙ ስሞች አሉት፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
1/ ጂብሪል/ጂብራኢል፡- አንዱና ዋነኛ ስሙ ነው፡፡ ይህ ጂብሪል የሚለው ስም በቁርኣን ውስጥ ሶስት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ በሐዲሥ ላይ ደግሞ ለብዙ ጊዜ ተወስቷል፡፡ በቁርኣን ላይ የተጠቀሰበት ስፍራም፡-
” قُلْ مَنْ كَانَ عَدُوًّا لِجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَى قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَى لِلْمُؤْمِنِينَ * مَنْ كَانَ عَدُوًّا لِلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِلْكَافِرِينَ ” سورة البقرة 98-97
“#ለጂብሪል (ለገብርኤል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፡፡ እርሱ (ቁርኣኑን) ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡ ለአላህና ለመላእክቱ ለመልክተኞቹም #ለጂብሪልም ለሚካልም (ሚካኢል) ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለ(እነዚህ) ከሓዲዎች ጠላት ነው፡” (ሱረቱል በቀራህ 2፡97-98)፡፡
” إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا وَإِنْ تَظَاهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ مَوْلَاهُ وَجِبْرِيلُ وَصَالِحُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمَلَائِكَةُ بَعْدَ ذَلِكَ ظَهِيرٌ ” سورة التحريم 4
“ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስሰማላችሁ)፤ በርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እረዳቱ ነው፤ #ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቱ ናቸው።” (ሱረቱ-ተሕሪም 66፡4)፡፡
عن أَبي سَلَمَةَ بْنِ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ عَوْفٍ قَالَ سَأَلْتُ عَائِشَةَ أُمَّ الْمُؤْمِنِينَ بِأَىِّ شَىْءٍ كَانَ نَبِىُّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَفْتَتِحُ صَلاَتَهُ إِذَا قَامَ مِنَ اللَّيْلِ? قَالَتْ:- كَانَ إِذَا قَامَ مِنَ اللَّيْلِ افْتَتَحَ صَلاَتَهُ « اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ وَمِيكَائِيلَ وَإِسْرَافِيلَ…» رواه مسلم.
አቢ ሰለመህ ዐብዲ-ራሕሕማን ኢብኒ-ዐውፍ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- “የምእመናን እናት የሆነችዋን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የለይል ሶላታቸውን በምን አይነት ዱዓ እንደሚጀምሩ ጠየቅኋት፡፡ እሷም፡- ‹‹የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የለይል ሶላታቸውን፡- የጂብራኢል፣ የሚካኢልና የኢስራፊል ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ…በማለት ይጀምሩ ነበር›› አለችኝ” (ሙስሊም 1847)፡፡
በዚህ ሐዲሥ መሰረት መልአኩ ጂብሪል (ዐለይሂ-ሰላም) ጂብራኢል ተብሎ እንደሚጠራም መረዳት እንችላለን፡፡ ጂብሪል/ጂብራኢል የሚለው ስም ትርጉሙ፡- ዐብዱላህ/የአላህ ባሪያ ማለት ነው፡፡
2/ ሩሕ/ መንፈስ፡-
ሌላኛው ሁለተኛው መጠሪያ ስሙ ነው፡፡ መልአኩ ጂብሪል በጌታው አላህ ዘንድ ‹‹ሩሕ›› (መንፈስ) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ለዚህም ማስረጃችን ቀጣዮቹ አንቀጾች ናቸው፡-
” وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ مَرْيَمَ إِذِ انْتَبَذَتْ مِنْ أَهْلِهَا مَكَانًا شَرْقِيًّا * فَاتَّخَذَتْ مِنْ دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا ” سورة مريم 17-16
“በመጽሐፉ ዉስጥ መርየምንም ከቤተ ሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለየች ጊዜ (የኾነዉን ታሪኳን) አዉሳ። ከነሱም መጋረጃን አደረገች፣ #መንፈሳችንንም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፤ ለርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት።” (ሱረቱ መርየም 19፡16-17)፡፡
3/ ሩሑል ቁዱስ/ ቅዱሱ መንፈስ፡-
” وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَقَفَّيْنَا مِنْ بَعْدِهِ بِالرُّسُلِ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ…” ” سورة البقرة 87
“ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክትኞችን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው…” (ሱረቱል በቀራህ 2፡87)፡፡
” تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَى بَعْضٍ مِنْهُمْ مَنْ كَلَّمَ اللَّهُ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ…” سورة البقرة 253
“እነዚህን መልክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው…” (ሱረቱል በቀራህ 2፡253)፡፡
” وَإِذَا بَدَّلْنَا آيَةً مَكَانَ آيَةٍ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوا إِنَّمَا أَنْتَ مُفْتَرٍ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ * قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِنْ رَبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَى لِلْمُسْلِمِينَ ” سورة النحل 102-101
“በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለውጥን ጊዜ፣ አላህም የሚያወርደውን ነገር ዐዋቂ ነው፤ አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም ይላሉ፤ በውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም። እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር (ቁርአንን)፣ ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው በላቸው።” (ሱረቱ-ነሕል 16፡102)፡፡
4/ ሩሑል አሚን/ ታማኙ መንፈስ፡-
” وَإِنَّهُ لَتَنْزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِينَ * نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ * عَلَى قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنْذِرِينَ * بِلِسَانٍ عَرَبِيٍّ مُبِينٍ ” ” سورة الشعراء 195-192
“እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ እርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው፤ ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትኾን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረደው)፡፡ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ፡፡” (ሱረቱ-ሹዐራእ 192-195)፡፡
ይቀጥላል