ቁርኣን ስለ ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት መበረዝ ክፍል-3

ሼር ያድርጉ
333 Views

ኢሊያህ ማህሙድ

በኣላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ዘመን በተላኩ ነቢይ ሙሓመድ (ሠ) ላይ የኣላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ ብለን እንቀጥላለን፡፡ ወዳጄ ከሰሞንኛ ወጋችን ቁርኣን ስለ ቀደምት መጽሐፍት መበረዝ ያነሳቸውን ነጥቦች የዘርፉ ልሂቃን የደረሱበትንም ማሳረጊያ ሃሳቦች አውርተናል፡፡ እነሆ ዛሬ የክርስትያኑ መጽሐፍ ራሱ የሰጣቸውን ምስክርነቶችን ከልሂቃኑ መጽሐፍት ጋር ኣዋዝተን እናያለን፡፡
ትንቢተ አሞጽ 8/11-12

“እነሆ፥በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እርሱም‡ የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም‡። ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይሯሯጣሉ፥ ‡አያገኙትምም‡።”

ወዳጄ በዚህ ጥቅስ መሰረት እግዚኣብሄር ኣንድ ወቅት በሰዎች መካከል “ቃሉን” እንደሚያነሳና ሰዎችም ቃሉን ፈልገው ሙሉ በሙሉ እንደሚያጡት እንረዳለን፡፡ ዛሬ ላይ የዘርፉ ልሂቃን በርካታ ፍተሻና ምርምር ካደረጉ በኋላ “የመጀመሪያዎቹ” የሚባሉትን እደ-ክታባት ማግኘት እንዳማይቻል ደምድመዋል፡፡ ዛሬ ላይ ያሉ እደ-ክታባት የቅጅ ቅጂ…ቅጂ እንጂ የመጀመሪያዎቹ የሂብሩና አርማይክ ጽሁፎች አይደሉም፡፡ ጥቅሱ እንሚያስረዳን የኣምላክን ቃል ሰዎች ለማግኘት ብዙ ይኳትናሉ ኾኖም ግን ኣያገኙትም፡፡ ፕሮፌሰር ባርት ኢህርማን ይህንን እውነታ እንዲህ በማለት ያረጋግጣል፡-

“ The vast majority of Christians for the entire history of the church have not had access to the originals, making their inspiration something of a moot point.Not only do we not have the originals, we don’t have the first copies of the originals. We don’t even have copies of the copies of the originals, or copies of the copies of the copies of the originals. What we have are copies made later much later. In most instances, they are copies made many centuries later.And these copies all differ from one another,in many thousands of places…these copies differ from one another in so many places that we don’t even know how many differences there are. Possibly it is easiest to put it in comparative terms:
There are more differences among our manuscripts than there are words in the New Testament.”

“ …ሁሉንም የቤተክርስቲያን ታሪክ ስንመለከት አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የመጀመሪያዎቹን መጽሐፍት የማግኘት እድል አልነበራቸውም፤ስለሆነም የመጀሪያዎቹ መጽሐፍት በመለኮታዊ ሀይል ተጻፉ ማለቱ በራሱ ውይይት የሚፈልግ ነጥብ ነው፡፡ ዋናዎቹ ሳይሆን ዛሬ የዋናዎቹ ቅጂዎች እንኳ የሉንም፡፡ የዋናዎቹ የቅጂ ቅጂዎችም ቢሆኑ የሉንም፡፡ ወይም ደግም የዋናዎቹ የቅጂ ቅጂ ቅጂዎች የሉንም፡፡ አሁን ያሉን የኋላ ኋላ የተጻፉና ከክፍለ ዘመናት በኋላ የተዘጋጁ ቅጂዎች ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም ቅጂዎች ታዲያ ሺህ ቦታዎች ላይ እርስ በርስ ይጣረሳሉ፡፡ …እነዚህ ቅጂዎች ያን ያህል ከመጣረሳቸው ባሻገር ምን ያህል መጣረሶች እንኳ እንዳሉ መገመት ያዳግታል፡፡ ምናልባት በማነጻጸር ማስቀመጡ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም እንዲህ ብለን፡- በእደ-ክታባቱ መካከል አዲስ-ኪዳን ውስጥ ‡ካሉት ቃላት በላይ‡ መጣረሶች አሉ፡፡” Misquating Jesus/ 10
ትንቢተ ኤርምያስ 8/8-9

“ እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? ‡እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል‡። ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፤ እነሆ፥ ‡የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል‡፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?”

ለአይሁዶች የእግዚኣብሄር ቃል ተስጥቶ ነበር (ወደ ሮሜ 3/2) ኾኖም ግን ጸሃፍት ይህንን የመጀመሪያውን ቃል እንዳሻቸው ጥለው ሌላ ሐሰተኛ ቃል ከትበዋል፡፡ ስለኾነም ከእንግዲህ ወዲህ ጥበበኞች አይባሉም፡፡ ዛሬ በክርስትያኑና አይሁዱ እጅ ያሉ መጽሐፍት በዓይነትም በቁጥርም እየቅል መኾናቸው ኣንደኛው ምክንያት ራሱ መጽሐፍ-ቅዱስ እንደሚመሰክረው ቀደምት በርካታ ጸሐፍት ብዙ ኾን ተብሎም በስህተትም ልወጣዎችን በማድረጋቸው ነው፡፡

ዛሬ በሃያ ኣንደኛ ክ.ዘ. በወንጌል ስም የሚታወቁ በርካታ መጽሐፍት አሉ፡፡ በጭብጥ ደረጃ ፈጽሞ ተጻራሪ ሃሳቦችም አሏቸው፡፡ ለምሳሌ የይሁዳ ወንጌል ስለስቅለት ከሚያወሩት ሌሎች ወንጌሎች የተለየ ሃሳብ አለው፡፡ ፕ/ሮ ባርት እንዲህ ይላል፡-

“ለምንድር ነው ይሁዳ እየሱስን ኣሳልፎ የሰጠው? ለዚህ ጥያቄ ወንጌላት በርግጥ የተለያየ መልስ አላቸው፡፡ በይሁዳ ወንጌል ግን ይሁዳን ‡እየሱስ ራሱ ኣሳልፎ እንዲሰጠው አግባብቶታል‡፡፡ በጥንት መረጃዎቻችን ውስጥ የተለያዩ ምክንያቶች ተስጥተዋል፡፡ ዩሃንስ ይሁዳን ፍጹም ሰይጣን አድርጎ ይስለዋል፡፡ እየሱስን አሳልፎ መስጠቱም ውስጣዊ ዝንባሌው እንደነበር ያምናል፡፡ ሉቃስ ሰይጣን ኣሳስቶት ነው የሚል ሃሳብ ያቀርባል፡፡ ማቲዎስ ደግሞ ስለ ገዘንብ ብሎ እንዳደረገው ይተርካል፡፡” (The lost Gospel of Judas Iscariot/177 )

 

Shortlink http://q.gs/Eye3O