ቁርኣን ስለ ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት መበረዝ ክፍል -2

ሼር ያድርጉ
429 Views

ኢሊያህ ማህሙድ

{ክፍል ኹለት }

በኣላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ዘመን በተላኩ ነቢይ ሙሓመድ (ሠ) ላይ የኣላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ ብለን እንቀጥላለን፡፡ ወዳጄ እንደምን ከረሙ?! ከሰሞኑ የሂጃብና የዴቪድ ውይይት በኋላ ወገኖቻችን ከውይይቱ የቃረሙትን እንደ አዲስ ነገር ለመጠየቅ (በነሱ ህሳቦ ለመገዳደር) ሲሞክሩ እያየን፤ እያዘንም፤ እየታዘብንም እንደኾነ ይሰማኛል፡፡ ኣንዳንዴ ግን ለነሱ መልሱ መስጠቱ ላያስፈልግ ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በተለይ ጥያቄው ኣራሙቻ ሲኾን የዝመታ እሳት መልቀቁ በቂ ነው፡፡ ወይም ደግሞ በጥያቄያቸው ውስጥ ምን እያመኑ እንደኾነ ራሳቸውን እንዲጠይቁ ማድረግ እጅግ ትርፋማ ነው፡፡ቃላት አያባክንምና!!!

በቀደመው ጽሁፋችን ርዕሱን ይዘን ከቀደምት መጽሐፍት አኳያ ቁርኣን ምን ዓይነት አቋም እንዳለው አይተናል፡፡ እነሆ ዛሬ ክፍል ኹለትን እንቀጥላለን፡፡ በክፍል ኣንድ ከዘረዘርናቸው አራት ነጥቦች ተነስተን ዛሬ ወገኖቻችን እጅ ስላሉት መጽሐፍት እንዲህ እንላለን፡-

1ኛ) ዛሬ ላይ ያለው መጽሐፍ ከኣላህ የኾኑ ህግጋት ሊኖሩት ይችላል፡፡ እነዚህ ህግጋት ከቁርኣን ጋር ተስማምተው ሲገኝ ከኣላህ መኾናቸውን እንቀበላለን፡፡ምክንያቱም ቁርኣን በቀደምት መጽሐፍት ላይ “አረጋጋጭና ማመሳከሪያ” ኾኖ ስለወረደ፤ በቁርኣን መስፈርት እስካላለፍ ድረስ ግን የትኛውም ክርስትያናዊም አይሁዳዊም ሕግ ቅቡልነት የለውም፡፡ኣላህም “እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጂልን ‡ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን‡ እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም” ሲል በመጀመሪያ ከራሳቸው መጽሐፍ ውስጥ ባሉት ባልተበረዙና ከቁርኣን ጋር ስምሙ በኾኑት እንዲፈርዱ ሲያዝ፤ ሲቀጥል “‡ ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን‡” በሚለው ሐረግ ደግሞ በቁርኣን እንዲያምኑ ያሳስባል፡፡ ኣላህ በቃሉ ሲናገር ፡-

“እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ‡ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡‡ ከነሱም የተለዩ ክፍሎች
እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ፡፡” አልበቀራህ/146

እዚህ የቁርኣን ጥቅስ ላይ ኢማሙ ቁርጡቢ በተፍሲር መጽሀፋቸው ሲናገሩ “ዑመር (ረ) ለዓብደላህ ቢን ሰላም (ረ) “ልጅህን እንደምታውቅ ሙሐመድን (ሠ) ታውቀው ነበርን?” ብሎ ጠየቀው፤ እሱም “አዎ ከዚያም በበለጠ…!!!” በማለት መለሰለት”ይላሉ፡፡ ወዳጄ ሀሳቡን ከተረዱ፤ አይሁዳዊው ዓብደላህ ቢን ሰላም (ረ) ከልጆቻችን በላይ መልክተኛውን (ሠ) እናውቀው ነበር ሲል በጊዜው በነበረው መጽሐፋቸው የመልክተኛው ሙሐመድ (ሠ) ዝርዝር መገለጫዎች ስለሰፈሩ ነው፡፡ ልጆቻቸው ከሌሎች የተወለዱ ሊኾኑ ይችላል፡፡ በጊዜው በነበረው እደ-ጥበብ (ቴክኖሎጂ) የዘረ-መል ፍተሻ (DNA Test) ማድረግ ስለማይቻል ሴቲቷ ካበለች ከባሏ ያልኾነውን ልጅ የባሌ ነው ብትል በትክክል መለየት አይቻልም ነበር፡፡ ስለኾነም የመጽሐፍቱ ባለቤቶች ከልጆቻቸው በላይ ስለ ሙሐመድ (ሠ) ነብይነት እርግጠኞች ነበሩ፡፡

ዛሬ ወገኖቻችን እጅ ላይ ያለው መጽሐፍ በትክክል ከኣላህ ከኾነ ስለ ነብዩ ሙሐመድ (ሠ) በሰፊው ዝርዝር ሃሳቦች መኖር ይኖርበታል፡፡ ቁርኣን ስለኛ መጽሐፍ መስክሯል የሚሉ ወገኖች በሙሉ ይህንን የመልክተኛውን ዝርዝር መገለጫዎች ከመጽሓፋቸው ነቅሰው ሊያሳዩን ይገባል፡፡ማሳየት ብቻም አይደለም በርሳቸውም ሊያምኑ የግድ ይላል፡፡ ምክንያቱም ቁርኣን ሙሐመድን ከልጆቻቸው በላይ ያውቁታል ብሎ ከተናገረ በኋላ በቁርኣንም እመኑ እያለ ያሳስባልና፡፡ ጥቅሶቹን ማቅረብ ካልቻሉ ግን፤ቁርኣን ዛሬ እነሱ እጅ ስላለው መጽሐፍ ሳይኾን ስለሌላ ስለጠፋ መጽሐፍ ነው ሚያወራው ማለት ነው፡፡

2ኛ) ዛሬ ባለው የወገኖቻችን መጽሐፍት ውስጥ ሰብኣዊ ንግግሮች ተካተዋል፡፡ ኣንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ በግልጽ ሰብኣዊ እንደኾኑ ኹላችንም እንስማማለን፡፡ ለምሳሌ በአዲስ ኪዳን ያሉ ኹሉም መልዕክቶች፡፡ ወንጌል በሚባሉ አራት መጽሐፍትም ውስጥ ቢኾን የእየሱስ የኾኑ አንድም ንግግሮች በርገጠኛነት ስለ መኖራቸው መናገር አይቻልም፡፡

ጂሰስ ሴሚናሪ በ 150 የዘርፉ ልሂቃን በ 1985 ተቋቋመ፡፡ የስብስቡ ዓላማ የቶማስን ጨምሮ በአምስቱ “ወንጌሎች” ውስጥ የእየሱስ (ዐ) ንግግሮችና ተግባራት ናቸው የተባሉት በትክክል ታሪክን ባማከለ መልኩ የርሱ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ለማረጋገጥ ነበር፡፡ በስተመጨረሻም ቡድኑ ጥናቱን ሲጨርስ በአምስቱ “ወንጌሎች” ውስጥ እየሱስ ተናግሮኣቸዋል የተባሉትን ቃላት በኣራት ቀለማት ከፋፍሎ አስቀመጠ፡፡ እንደሚከተለው፡-
‡ቀይ ቀለም‡፡- እየሱስ በአምስቱም “ወንጌላት” ምንባቦች ውስጥ ከተቀመጡ ቃላት ጋር በጣም የሚመሳሉ ንግግሮችን ተናግሯል ተብሎ ሲታመን (3 ነጥቦች ይይዛል)~ likely authentic
} በዚህ ቀለም የተቀለሙ ጥቅሶች የሚከተሉት ብቻ ናቸው፡-
{ከማርቆስ}
12/17
{ከማቴዎስ}
5/39፣ 5/40፣ 5/3፣ 5/6፣ 5/41፣ 5/44፣ 13/33፣ 22/21፣ 5/42
{ከሉቃስ}
6/29፣6/30፣ 6/21፣ 6/20፣ 6/27፣ 6/32-35፣ 10/30-35፣ 13/20-21፣ 20/25፣
{ከቶማስ}
96/1-2፣54/1-መጨረሻው፣69/2፣100/2

ወዳጄ ከዩሃንስ ወንጌል ምንም በዚህ ጎራ የተመደበ ጥቅስ እንደሌለ ያስምሩበት!!!

ፒንክ ቀለም ፡- እየሱስ ምናልባት ከምንባቡ ጋር ሊመሳሰል የሚችል ንግግር ተናግሯል ተብሎ ሲገመት (2 ነጥቦችን ይይዛል)~ somewhat likely

ግራጫ ቀለም፡- ምንባቡ የእየሱስን ሃሳብ እንጂ ምንም የርሱን ቃላት ካልያዘ (1 ነጥብ ይይዛል)~ somewhat unlikely

ጥቁር ቀለም፡- በምንባቡ ያሉትንም ቃላት ኾነ ሃሳቡንም ጨምሮ እየሱስ ምንም የተናገረው ነገር ከሌለና ከሌሎች ታሪኮች የተቀዳ ከኾነ (0 ነጥብ ይይዛል) ~unlikely

ወዳጄ ልሂቃኑ በርግጠኝነት እየሱስ ብሎታል የሚሉት ምንም ቃል በአራቱም “ወንጌሎች” ውስጥ እንደሌለ ልብ ይሏል፡፡አስቀድመን እንዳየነው በጣም የሚመሳሰሉ ቃላትን ተናግሯል ለሚለው ሃሳብ ቀይ ቀለም የተጠቀሙ ሲኾን ከጥናቱ በስተመጨረሻ ቀይ ቀለም የተሰጣቸው ቃላት ኣንድ ዓምድ (ኮለም) የማይሞሉ እንደኾነም ከላይ ከተደረደሩት ጥቅሶች መረዳት ይቻላል፡፡

3ኛ) ኣላህ ካወረደው ተውራት በባህታውያን የተደበቁ/የተሰወሩ ሃሳቦች አሉ፡፡ ኣላህ በቃሉ ሲናገር፡-

“‡(የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ‡ብዙውንም ትደብቃላችሁ‡፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ፤» ኣንዓም/91

4ኛ) የኣላህን ቃል መለወጥ የሚለው በኹለት መልኩ ኾኗል፡፡ አንደኛው “ቃላዊ ልወጣ” ሲኾን ይኸውም በነበረው ላይ መጨመር ወይም መቀነስን ያመላክታል፡፡ ኹለተኛው “ትርጉማዊ ልወጣ” ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኣንድን ቃል ሌላ ትርጉም እንዳለው አድርጎ ማቅረብ ነው፡፡ ይህ ዛሬም ድረስ በተለይ በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን “አንደምታ” እየተባለ የሚሰራበት ነው፡፡ ዲያቆን አግዛቸው “የተቀበረ መክሊት” በሚለው መጽሐፉ ገጽ 94 ላይ እንዲህ ይላል፡-
“አንደምታ የተሰኘው የትርጓሜ ስልት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርስ በርስ ተቃራኒ የሚመስሉ ምንባቦችን በማስታረቅና በመሳሰለው አስተዋጽኦ ቢኖረውም፤‡እውነትን ለማፈንና ስህተትን ለማራመድም ረድቷል‡”

ኢብኑ ሃዝም ሲናገር ደግሞ “ ኢስራኤላዊ ከሃድያን ተውራትንና ዘቡርን ለወጡ… ክርስትያኖች ደግሞ ኢንጂልን ለወጡ…” አልፈስል ፊል ሚለል 1/157

————————————————-ይቀጥላል————————

Shortlink http://q.gs/Eye01