ማነው እውነተኛው እግዚአብሄር ወይስ እባቡ

ሼር ያድርጉ
478 Views
ኢሊያህ ማሕሙድ በአላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነው ጀምረን እንቀጥላለን፡፡ ወዳጄ እንደምን ከረሙ? የምርጫው ሙቀትስ ከዝናቡ ጋር እንዴት ይዞታል? እኔ ከምኖርበት አገር ወቅቱ ከፍተኛ ሙቀት ያለበት ስለሆነ ዝናብ በዲሽ ማየት ሁሉ ይናፍቃል፡፡ በተለይ ዘንቦ ጭቃ ማየትማ አቤት!!!… በህልም ሁሉ ሳይነፍቅ አይቀርም፡፡ ወደ ቁም ነገሩ ስንዘል፣ ወዳጄ ዛሬ የምናወራው በኦሪት ዘፍጥረት ስላለው የእባቡና የእነ ሄዋንን አስደማሚ ታሪክ ይሆናል፡፡
{ኦሪት ዘፍጥረት}
ዘፍትረት 3/1 “እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ።” ወዳጄ እስኪ ሩቅ ሳንሄድ ከዚሁ ጥቅስ ተነስተን እንጠይቅ (ጥ.1.) አምላክ ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ እባብ ተንኮለኛ ስለመሆኑ ምን ሳይንሳዊ/ታሪካዊ መረጃ አለን? ወዳጄ “ ይኸው መጽሀፉ ይል አይደለም እንዴ?” እንዳይሉ፡፡ ለምን መሰሎት ሲጀምር አምስቱ የኦሪት መጽሀፎች መለኮታዊ ራእይ ይሁኑ አይሁኑ፤ ሙሴ ይጻፋቸው አይጻፋቸው ምንም ግልጽ የሆነ መረጃ የለም፡፡ እስኪ ይህንን ድረ-ገጽ ጣቅ እናርግና አበረን እናንብበው፡-http://biblehub.com
The facts are, that Jesus nowhere testifies that Moses wrote the whole of the Pentateuch; and that he nowhere guarantees the infallibility either of Moses or of the book. On the contrary, he sets aside as inadequate or morally defective certain laws which in this book are ascribed to Moses.
ስንገረድፈው ፡- “እውነታው እየሱስ የትም ቦታ ላይ ኦሪቶቹን ሙሴ ስለመጻፉ ምስክርነት አልሰጠም፡፡ በተጨማሪም የትም ቦታ ላይ ስለ ሙሴም ሆነ ስለ ኦሪት ፍጹምነት ዋስትና አልሰጠም፡፡ በተቃራኒው ግን በዚህ የሙሴ በተባለው መጽኀፍ ውስጥ በቂ እንዳልሆኑ ወይም ከስብእና አኳያ ችግር እንዳለባቸው ሁሉ አንዳንድ ህግጋትን ሽሯል፡፡”
They (Christ and the apostles) nowhere pronounce any of these writings free from error; there is not a hint or suggestion anywhere in the New Testament that any of the writings of the Old Testament are infallible.
“እነዚህ የኦሪት ጽኁፎች ከስህተት የጠሩ ስለመሆናቸው እየሱስና ደቀ-መዛሙርቱ ጮኸው (በግልጽ) የተናገሩበት አጋጣሚ የለም፤ በአዲስ-ኪዳን ውስጥ የትኞቹም የብሉይ-ኪዳን ጽሁፎች ፍጹም ናቸው የሚል ፍንጭም ወይም ሀሳብም የለም፡፡”
ወዳጄ እስኪ ደግሞ ኦሪትን እናንብብ፡- ዘዳግም 34/5 “የእግዚአብሔር ባሪያም ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ።”
ቀጠለና እባቡ “ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ሴቲቱም ለእባቡ አለችው። በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፤ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ፦ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም።” ወዳጄ ልብ ይበሉ እግዚአብሄር “እዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ” ሲል እባቡ ደግሞ “ሞትን አትሞቱም፤ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።” አላቸው ከዚያ በኋላም “ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች ከፍሬውም ወሰደችና በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥”
ልብ ይበሉ ወዳጄ! ፍሬውን ከበሉ በኋላ መሞት ይቅርና የሁለቱም አይኖች ተከፈቱ፤ መከፈት ብቻም አይደለም “እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።” ታዲያ ወዳጄ ስህተተኛው ማነው? እባቡ የነገራቸው ሁሉ ሆነ፡፡ እግዚአብሄር ግን ከነገራቸው አንድም እንኳን አልሆነም፡፡ አይገርምም!!!!!!
ሌላው መጽኀፍ ቅዱስ ላይ ትልቅ ጥያቄ የሚያስነሳው አሳሳቹ እባብ ነው ወይስ ሰይጣን? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ ምናልባት ክርስቲያኖቹ አይ ሰይጣን እባብ መስሎ ተከስቶ ነው ሊሉ ይችላል፡፡ እኔ ግን መጀመሪያ እነዚህ ጥቅሶች ጀባ ልበልና እንደተለመደው ጥያቄዬን ላስከትል፡፡ የዩሃንስ ራእይ 12/9 “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።” የዩሀንስ ራእይ 20/2 ላይ በተጨማሪ ያ እባብ ሰይጣን እንደነበር ይነግረናል “የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ።የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥”
ዘፍጥረት 3/14 ላይ ደግሞ የተባለውን እስኪ እናንብብና እንጠይቅ “እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።”
ታዲያ ወዳጄ አሳሳቹ ሰይጣን ከሆነ እግዚአብሄር “ከምድር አራዊት” የሚለውን ሀረግ ለምን ተጠቀመ? “በሆድህም ትሄዳለህ” ማለትስ ማንን ነው የሚያመላክተው? “አፈርንም በህወይትህ ዘምን ሁሉ ትበላለህስ” የሚለው? እግዚአብሄር የሚያናግረውን አያውቅም ነበርን?
ወዳጄ ሳይንሱ እንደሚነግረን በዓለም ከ3000 ሺህ በላይ የእባብ ዝርያዎች ይገኛሉ ግና አንዱም ዝርያ አፈር አይመገብም፡፡ ታዲያ አፈር የሚመገበው ሰይጣን ይሆን? ነው ከተባለ ማስረጃ እንፈልጋለን፡፡ እዚህ ቦታ ላይ የተገለጸው ታሪክ ሌላ ፍካሬአዊ (ሲምቦሊክ) ትርጉም አለው ከተባለ የሁሉም ቃላት ሰምና ወርቅ ይፈታና እንስማው፡፡ ለምሳሌ እዚህ ቦታ ላይ “አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ” የሚለው ሃረግ እንደዚሁም “ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።” የእነዚህን ቃላት ሁላ ሰምና ወርቅ ማወቅ እንፈልጋለን፡፡ ቸር እንሰንብት!!!