ማስገንዘቢያ ለክርስቲያኖች

ሼር ያድርጉ
356 Views
ኢሊያህ ማሕሙድ በመጽሐፋችሁ ያሉ ወጣ ያሉና “ስድ” የሚመስሉ ንግግሮችን ስታነቡ “እግዚኣብሔር በፈለገው መልኩ ይናገራል፤ሰው አይደልምና እንደሰው እንዲናገር መጠበቅ የለብንም፤በፈለገው መልኩ ምሳሌ ማድረግ ይችላል…”ወዘተና አከተ መልሶቻችሁና አምክንዮዎቻችሁ፤የኛንም የሙስሊሙን መለኮታዊ መጽሐፍ ስታነቡ ብትጠቀሙበት ፍታሐዊ ያደርጋችኋል፡፡ ለምሳሌ ፡- ትንቢተ ሕዝቅኤል 23/1-8 የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ።በግብጽም ≠አመነዘሩ፥≠ በኰረዳነታቸው አመነዘሩ፤≠ በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ≠ በዚያም የድንግልናቸውን ጡቶች ዳበሱ።≠ በግብጽም የነበረውን ≠ግልሙትናዋን ≠አልተወችም፤ በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ≠ተኝተው≠ ነበር፥ ≠የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥≠ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ≠ ነበር። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4/5
≠ሁለቱ ጡቶችሽ≠ መንታ እንደ ተወለዱ፥ በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ እንደ ≠ሚዳቋ ግልገሎች≠ ናቸው። የማቴዎስ ወንጌል 12/39 ክፉና ≠አመንዝራ≠ ትውልድ ምልክት ይሻል ኦሪት ዘዳግም 23/1 …ላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ (ወዳጄ ገብተው ያንብቡት ሙሉውን) መጽሐፈ መሣፍንት 5/30
ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ≠ሁለት ቈነጃጅት፤≠ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጕርጕር ልብስ።
ወዳጄ “ቆነጃጅት” ለሚለው ቃል ትክክለኛው የሒብሩ ቃል ይህ ነው רַחַם (racham)ራቻም ማለት ደግሞ-
But רַחַם (racham ) doesn’t mean “girl” (or “damsel” as in other translations). Though it has a variety of meanings, in this context at best it means “womb” and at worst “vagina.” (https://www.agameforgoodchristians.com)
ስንገረድፈው፡-
“ራቻም ማለት “ልጃገረድ” (ቆነጃጅት) ማለት አይደለም፡፡በርካታ ትርጋሜዎች ቢኖሩትም ፤በዚህ ዐውድ ውስጥ ግን በጥሩ ቃል ሲገለጽ “ማሕጸን” በመጥፎ ቃል ሲገለጽ ደግሞ “ vagina”ማለት ነው፡፡ ወዳጄ አሁን ይህንን ቃል ሰክተን ጥቅሱን ስናነበው ያለውን መልእክት ልብ ብለው ያስቡት፡፡ “ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ≠ሁለት vagina ፤≠
ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጕርጕር ልብስ። ” የሚል ይኾናል፡፡ ምን ያህል የትረጉም ልዩነት እንዳለው ልብ ይበሉ፡፡ ተረጓሚዎችም በሌላ ቃል የተጠቀሙት ያለውን ጎርባጣ መልእክት ፈርተው ሊኾን ይችላል፡፡ ወዳጄ በአማርኛችን ነውር የሚባሉ መሰል በርካታ ቃላትን ከመጽሐፉ መዘርዘር ይቻላል፡፡ አሁንም ግን ዓላማው ወገኖቻችን መሰፍሪያችሁ ይሰተካከል ለማለት ብቻ ነው፡፡ በኣማርኛ ነውር የሚባሉ በሌሎች ቋንቋዎች በተለይም ሴማቲክ በኾኑ እነ ዐረብኛ፣ሒብሩና አርማይክ ቋንቋዎች ነውር ያልኾኑ ቃላት አሉ፡፡ ኣማርኛ ላይ ቆመን መጽሐፎቹ እንዴት አንዲህ አሉ፤ለምንስ በዚህ መልኩ ምሳሌ አደረጉ ብሎ መተቸት፤ወርቅን በእህል መስፈሪያ እንደመስፈር ስለኾነ ወገኖቻችን አስቡበት ፡፡