“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” 7

ሼር ያድርጉ
402 Views

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

2. ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ

ቀ/ ትንሽ ውሃ እጅግ መብዛቱ

ሙስሊሞች (ሶሀባዎች) መዲና ውስጥ እያሉ ለውዱእ ውሃ እጅግ በጣም ይቸግራቸው ነበር፡፡ ታዲያ ምን ተከሰተ?፡-
عَنْ أَنَسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ: أُتِيَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِإِنَاءٍ، وَهُوَ بِالزَّوْرَاءِ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي الإِنَاءِ، «فَجَعَلَ المَاءُ يَنْبُعُ مِنْ بَيْنِ أَصَابِعِهِ، فَتَوَضَّأَ القَوْمُ» قَالَ قَتَادَةُ: قُلْتُ لِأَنَسٍ: كَمْ كُنْتُمْ؟ قَالَ: ثَلاَثَ مِائَةٍ، أَوْ زُهَاءَ ثَلاَثِ مِائَةٍ.
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘውራዕ በተባለው ስፍራ ከባልደረቦቻቸው ጋር እያሉ ውሃ መያዣ እቃ መጣላቸው እጃቸውንም በእቃው ላይ አስቀመጡና አነሱት ከዚያም ከጣታቸው መካከል ውሃ መፍለቅ ጀመረ፡፡ ህዝቦቹም ውዱእ አደረጉ” ቀታደታ የተባለው ሰው (ረሒመሁላህ) አነስ ኢብኑ ማሊክን (ረዲየላሁ ዐንሁ) (በወቅቱ ከጣታቸው ይፈልቅ በነበረው ውሀ ለዉዱእ የተጠቀማችሁት) ስንት ነበራችሁ? ብሎ ጠየቀው፡፡ አነስም ‹‹ሶስት መቶ ነበርን›› አለ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)፡፡
عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ: عَطِشَ النَّاسُ يَوْمَ الحُدَيْبِيَةِ وَالنَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بَيْنَ يَدَيْهِ رِكْوَةٌ فَتَوَضَّأَ، فَجَهِشَ النَّاسُ نَحْوَهُ، فَقَالَ: «مَا لَكُمْ؟» قَالُوا: لَيْسَ عِنْدَنَا مَاءٌ نَتَوَضَّأُ وَلاَ نَشْرَبُ إِلَّا مَا بَيْنَ يَدَيْكَ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي الرِّكْوَةِ، فَجَعَلَ المَاءُ يَثُورُ بَيْنَ أَصَابِعِهِ، كَأَمْثَالِ العُيُونِ، فَشَرِبْنَا وَتَوَضَّأْنَا قُلْتُ: كَمْ كُنْتُمْ؟ قَالَ: لَوْ كُنَّا مِائَةَ أَلْفٍ لَكَفَانَا، كُنَّا أَلْف وَأَرْبَع مِائَةٍ. رواه البخاري 3576
ጃቢር ኢብኒ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- “ሰዎች (ሶሓባዎች) የሑደይቢያ ጊዜ ተጠሙ፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ ደግሞ ከቆዳ የተሰራ ትንሽዬ የውሀ መያዣ እቃ ነበር፡፡ እሳቸውም ዉዱእ አደረጉበት፡፡ ሰዎቹም ወደሳቸው ዘንድ መጡ፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹ምን ሆናችሁ?›› ሲሏቸው፡ እነሱም፡- እርሶ ዘንድ ካለው ውጪ ለዉዱእም ሆነ ለመጠጥ የምንገለገልበት የሆነ ውሀ እኛ ዘንድ የለንም አሉ፡፡ መልክተኛውም እጃቸውን በእቃው ላይ አደረጉና ሲያነሱት፡ ልክ እንደ ምንጭ ከጣታቸው መሀል ውሀ መፍለቅ ጀመረ፡፡ እኛም ጠጣን፡ ዉዱእም አደረግን፡፡ (ዒምራን ኢብኑ ሑሰይንም) ለጃቢር፡- በወቅቱ ስትን ነበራችሁ? አልኩት አለ፡፡ ጃቢርም፡- ‹‹አንድ መቶ ሺህ ብንሆንም ይበቃን ነበር!!፡፡ እኛ ግን አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበርን›› በማለት መለሰ” (ቡኻሪይ 3576፣ አሕመድ 14522፣ ሶሒሕ ኢብኑ-ሒባን 6542)፡፡

በ/ ትንሽ ምግብ እጅግ መብዛቱ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እጅግ ተርበው ነበር፡- አቡ ጦልሐም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ጥቂት የገብስ ቁራሽ ይዞላቸው መጣ ነቢዩም እንዲፈተፈት አዘዙ ከዚያም ዱአ አደረጉበትና ሶሓባዎችም አስር አስር ሆነው በመቀመጥ እንዲበሉ አዘዙ ያቺን ጥቂት የገብስ ቁራሽ ሁሉ ጠግበው በሉ፡፡ ብዛታቸውም ሰማኒያ ነበሩ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
እንደዚሁ አንድ ጊዜ በነቢዩና (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሶሐቦቻቸው ላይ በዘመቻ ምሽግን እየቆፈሩ ሳለ ረሃብ ጠናባቸው፡፡ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ፍየል ለነቢዩና ለሶሓቦቹ አረደ፡፡ ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በእርዱ ላይ ዱዓእ በማድረግ የዘመቻውን ሰዎች እንዳለ በመጣራት እንዲበሉ ተደረገ፡፡ ሁሉም ጠግበው በሉ ብዛታቸው ግን አንድ ሺህ ነበር፡፡ (ቡኻሪ የዘገበው)፡፡

ተ/ የቴምር ግንድ መንሰቅሰቅ

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የጁሙዓህ ኹጥባ የሚያደርጉት የቴምር ግንድን በመደገፍ ነበር፡፡ ሚንበር ከተሰራላቸው በኋላ ግን ያንን የቴምር ግንድ ትተው ወደተሰራላቸው ሚንበር ሲወጡ ያ የቴምር ግንድ እንደ ግመል መንሰቅሰቅ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደርሱ በመምጣት እጃቸውን ሲያሳርፉበት ወዲያው ፀጥ አለ፡፡ (ቡኻሪ ነሳኢይና ቲርሚዚይ የዘገቡት)፡፡

ቸ/ የምግብ ተስቢሕ ማድረግ

የነቢያችን ባልደረባዎች (ሶሓቦች) ነቢዩ ባሉበት ስፍራ ላይ አብረው ሲመገቡ፡ ምግቡ ራሱ ተስቢሕ ሲያደርግ በጆሮዋቸው ይሰሙ ነበር፡፡ (ቡኻሪና ቲርሚዚ የዘገቡት)፡፡ ሌሎችም ብዙ ብዙ…

Shortlink http://q.gs/Ewltl