“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” 2

ሼር ያድርጉ
444 Views

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

1. ስለ ነቢይነታቸው የተነገረ ትንቢት፡-

ከትላንት በፊት ስለ ረሱላችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይ ሆኖ መነሳት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር፡ የመጀመሪያውን ነጥብ፡ ቀደምት ነቢያት ስለ እሳቸው መናገራቸውን ተመልክተናል፡፡ ዛሬም የጌታችን አላህ ፈቃድ ከሆነ ሁለተኛውን ክፍል፡ ማለትም ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍት የተናገሩትን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-

ለ. በመጽሀፍት በኩል፡-

ነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይ ሆነው እንደሚነሱ ቀደምት ነቢያት ብቻ ሳይሆኑ ትንቢትን የተናገሩት፡ ከቅዱስ ቁርኣን በፊት የነበሩ ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት በተለይም ተውራትና ኢንጂል ስለ ነቢይነታቸው ተናግረዋል፡፡ በውስጣቸውም የሳቸውን ወደፊት ነቢይ ሆኖ መነሳት በመተንበይ ላመነ ሰው ብስራትን አቅፈዋል፡፡ እነሆ ማስረጃውም ይኸው፡-

“وَاكْتُبْ لَنَا فِي هَذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ إِنَّا هُدْنَا إِلَيْكَ قَالَ عَذَابِي أُصِيبُ بِهِ مَنْ أَشَاءُ وَرَحْمَتِي وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ فَسَأَكْتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَالَّذِينَ هُمْ بِآيَاتِنَا يُؤْمِنُونَ ” سورة الأعراف 156
“ለኛም በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም (መልካሟን) ጻፍልን፤ እኛ ወደ አንተ ተመለስን፤ (ሲል ሙሳ ጸለየ፤ አላህም) አለ፦ ቅጣቴ በርሱ የምሻውን ሰው እቀጣበታለሁ፤ ችሮታየም ነገሩን ሁሉ ሰፋች፤ ለነዚያም ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለነዚያም እነሱ በአንቀጾቻችን ለሚያምኑ በእርግጥ እጽፋታለሁ።” (ሱረቱል አዕራፍ 156)፡፡

በዚህ አንቀጽ ውስጥ የምናገኘው፡- ሙሳና ተከታዮቹ ወደ ጌታ አላህ ዱዓእ ማድረጋቸውን ነው፡፡ ዱዓውም፡- እኛ ወደ አንተ መንገድ ተመልሰናልና፡ በምድራዊ ህይወታችንና በመጨረሻው ዓለም መልካምን ነገር እንድትወስንልን ነው የሚል ነበር፡፡ ጌታችንም፡- የኔ ራሕመት (ጀነት) ሁሉን ነገር የሰፋች በመሆኗ፡ ለነዚያ የትም ስፍራ ሆነው እኔን ብቻ ለሚፈሩኝ፣ ግዴታ የሆነውን ምጽዋት የሚሰጡ፣ በአንቀጾቼም ለሚያምኑት እጽፋታለሁ አለ፡፡ ነገሩ በዚህ አልቆመም፡፡ አንቀጹም ይቀጥልና አሁንም ይህቺ ጀነት ለነማን እንደምትጻፍ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡-

“الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِنْدَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنْجِيلِ يَأْمُرُهُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنْزِلَ مَعَهُ أُولَئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ ” سورة الأعراف 157
“ለነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነብይ የሆነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለሆኑት (በእርግጥ እጽፋታለሁ)፤ በበጎ ስራ ያዛቸዋል፤ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፤ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፤ መጥፎ ነገሮችም በርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል። ከነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በነሱ ላይ የነበርሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) በርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው።” (ሱረቱል አዕራፍ 157)፡፡

በዚህኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ፡- አሁንም ጀነቴን ለነዚያ ማንበብና መጻፍ የማይችል የሆነውን ነቢይ ለሚከተሉት እጽፋታለሁ እያለ ነው ጌታችን፡፡ ደግሞም ይህ ማንበብና መጻፍ የማይችል የሆነው ነቢይ በነሱም ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ስሙና ባሕሪው ተጽፎ የሚገኝ ነው እያለን ነው፡፡ ታዲያ ተውራትና ኢንጂል እየተናገሩ ያለው ስለ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) አይደለምን? ይህ ማንበብና መጻፍ የማይችለው ነቢይ! የተባለው ማነው? ከተባለም፡ ያለ ምንም ማመንታት መልሱ፡- ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ናቸዋ! የሚል ይሆናል፡፡ ለዚህም ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-

“وَمَا كُنْتَ تَتْلُو مِنْ قَبْلِهِ مِنْ كِتَابٍ وَلَا تَخُطُّهُ بِيَمِينِكَ إِذًا لَارْتَابَ الْمُبْطِلُونَ ” سورة العنكبوت 48
“ከርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፤ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራሩ ነበር።” (ሱረቱል ዐንከቡት 48)፡፡

…”فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ ” سورة الأعراف 158
“…በአላህና በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነብይ በሆነው መልክተኛው እመኑ፤ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት።” (ሱረቱል አዕራፍ 158)፡፡

ተውራትና ኢንጂል ስለ እሳቸው ትንቢት መናገራቸውን ለማረጋገጥ፡ ዛሬ በክርስቲያኖችና አይሁዶች እጅ የሚገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተን፡ ከውስጡ ጥቅስ መፈለግ ግድ አይደለም፡፡ ጌታ አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ከነገረን በቂ ነው፡፡ እሱ እኮ ነው ተውራትንና ኢንጂልንም ያወረደው፡፡ ታዲያ ባለቤቱ የነገረንን ትተን ሰዎች በእጃቸው የበረዙትን መጽሀፍ ለማረጋገጫነት እንጠቀማለን እንዴ? ከነሱ መጽሐፍ መጥቀስ ያስፈለገው እኮ፡ ቢያንስ በቁርኣን ካላመኑ በያዙት መጽሀፍ እንኳ እውነቱን እንዲያዩ ለመርዳት እንጂ፡ ለምስክርነትማ ‹‹ወከፋ ቢላሂ ሸሂዳ›› (መስካሪነትማ በአላህ በቃ!) ፡፡ ተውራት ስለ እሳቸው ነቢይነት እንደሚናገር ሌላ ማጠናከሪያ ከሐዲሥ እንመልከት፡-

عنْ عَطَاءِ بْنِ يَسَارٍ قَالَ : لَقِيتُ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قُلْتُ : أَخْبِرْنِي عَنْ صِفَةِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي التَّوْرَاةِ. قَالَ أَجَلْ وَاللَّهِ إِنَّهُ لَمَوْصُوفٌ فِي التَّوْرَاةِ بِبَعْضِ صِفَتِهِ فِي الْقُرْآنِ {يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا} وَحِرْزًا لِلْأُمِّيِّينَ أَنْتَ عَبْدِي وَرَسُولِي سَمَّيْتُكَ المتَوَكِّلَ لَيْسَ بِفَظٍّ وَلَا غَلِيظٍ وَلَا سَخَّابٍ فِي الْأَسْوَاقِ وَلَا يَدْفَعُ بِالسَّيِّئَةِ السَّيِّئَةَ وَلَكِنْ يَعْفُو وَيَغْفِرُ وَلَنْ يَقْبِضَهُ اللَّهُ حَتَّى يُقِيمَ بِهِ الْمِلَّةَ الْعَوْجَاءَ بِأَنْ يَقُولُوا لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَيَفْتَحُ بِهَا أَعْيُنًا عُمْيًا وَآذَانًا صُمًّا وَقُلُوبًا غُلْفًا. رواه البخاري 2018

ዐጣእ ኢብኑ የሳር (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላል፡- “ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምሩ ኢብኑል-ዓስን (ረዲየላሁ ዐንሁማ) አገኘሁትና፡- ስለ አላህ መልክተኛ ባሕሪ በተውራት ውስጥ ያለውን ንገረኝ አልኩት፡፡እሱም፡- እሺ! ወላሂ እሳቸው በተውራት ውስጥ ከፊል ባሕሪያቸው በቁርኣን ውስጥ፡- “አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን ላክንህ።” ተብሎ እንደተገለጸው ተጠቅሶአል፡፡ (የተውራቱ ቃል ይቀጥልና እንዲህ ይላል) መሀይማኖችን ጠባቂ አድርጌ ልኬሀለሁ፡፡ መጥፎን ቃል ተናጋሪ ወይም ልበ ደረቅ አይደለህም፡፡ በገበያ ማእከሎችም ድምጽህን ከፍ በማድረግ የምትጮህ አይደለህም፡፡ መጥፎ ቢሰራብህ በመጥፎ የምትክስ ሳትሆን፡ ነገር ግን ይቅር ባይ እና መሐሪ ነህ፡፡ አላህ ባንተ ሰበብ የጠመሙ ጎዳናዎችን ቀጥ እስኪያደርጋቸውና ሰዎች ላ ኢላሀ ኢልለሏህ እስኪሉ ድረስ በፍጹም አይገድልህም፡፡ ባንተው ሰበብ የታወሩ አይኖች ሐቅን ለመመልከት፣ የደነቆሩ ጆሮዎች ሐቅን ለመስማት፣ የተዘጉ ልቦች ሐቅን ለመቀበል ይከፈታሉ” (ቡኻሪይ 2018)፡፡

ይህ ከላይ የተጠቀሰው በተውራት የተቀመጠው የነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ባሕሪ ነው፡፡ ተውራትና ኢንጂል አይደለም ስለሳቸው ስለ ተከታዮቻቸው (ሶሐቦች) እንኳ ባሕሪቸው ምን አይነት እንደሆነ ሲገልጹ እንዲህ ይናገራሉ፡-

“مُحَمَّدٌ رَسُولُ اللَّهِ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِمْ مِنْ أَثَرِ السُّجُودِ ذَلِكَ مَثَلُهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَمَثَلُهُمْ فِي الْإِنْجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْأَهُ فَآزَرَهُ فَاسْتَغْلَظَ فَاسْتَوَى عَلَى سُوقِهِ يُعْجِبُ الزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ الْكُفَّارَ وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنْهُمْ مَغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا ” سورة الفتح 29

“የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሐዲዎች ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፤ አጎንባሾች ሰጋጆች ሆነው ታያቸዋለህ፤ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፤ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊቶቻቸው ላይ ናት፤ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፤ በኢንጅልም ውስጥ ምሳሌአቸው ቀንዘሉን እንደአወጣ አዝመራና (ቀንዘሉ) እንዳበረታው እንደወፈረምና ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ሆኖ በአገዳዎች ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ፣ (አዝመራ) ነው፤ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሐዲዎችን በነሱ ሊያስቆጭ ነው፤ አላህም እነዚያን ያመኑትና ከነሱ በጎዎችን የሰሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል።” (ሱረቱል ፈትሕ 29)፡፡

ተውራትና ኢንጂልም ስለ እሳቸው መናገራቸውን በተወሰነ መልኩ እንዲህ ካየን፡ በቀጣዩ ደግሞ ወደ ሶስተኛው ነጥብ በአላህ ፈቃድ እንሸጋገራለን ኢንሻአላህ፡፡

Shortlink http://q.gs/EwnXL