መጽሀፍ ቅዱስና ስህተቶቹ -1

ሼር ያድርጉ
407 Views

“እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ።” ዘፍጥረት 1፥3

በዚህና ቀጥሎ ባለው አንቀፅ እንደተነገረን ከሆነ ብርሀን የተፈጠረው በመጀመሪያው ቀን ነው።

“እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።” ዘፍጥረት 1፥5

ብርሀን በመጀመሪያው ቀን ተፈጠረ ካለ በኃላ ግን መልሶ ደግሞ የብርሀን መሠረት የሆነችው ፀሀይ ከብርሀን በኃላ እንደተፈጠረ ደግሞ ይነግረናል።

“እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።” ዘፍጥረት 1፥16

ሁለት ብርሀን የተባሉት ፀሀይና ጨረቃ ደግሞ የተፈጠሩት በ19ኛው አንቀጽ እንደተገለጸው በአራተኛው ቀን ነው። ይህ ደግሞ የሚከተለውን ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል።

❐ የብርሀን መሠረት የሆነችው ጸሀይ ሳትፈጠር በፊት ብርሀን እንዴት ሊኖሮ ቻለ?

Shortlink http://q.gs/Ey5Hs