السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ሼር ያድርጉ
404 Views
ኢሊያህ ማህሙድ በመጀመሪያ የአላህ ሰላም በመልክተኛው በሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ቀጥሎም በሁላችንም ላይ ይሑን፡፡አሜን፡፡ ቀጥሎም የተለየ ሰላም በዚህ ግድግዳ ደንበኞች ላይና ሌላ ወፍራም ሰላም ግድግዳውን ባሰናዱ ላይ ይሁን፡፡ አሁንም አሜን፡፡ ወዳጄ ይህንን ጽኁፍ አስቀድመው ሌላ ግድግዳ ላይ አንብበውት ይሆናል፡፡ ከአነበቡት አይድከሙ ፤ ካልሆነ ግን ኢስላም ማለት ምንድን ነው? ቁርዐንና መጽኀፍ-ቅዱስን ዋቢ በማድረግ እናወራለን መልካም ንባብ ይሁንሎ !!!{ኢስላም፡- (1) ቋንቋዊ ትርጓሜው } ሊሳኑን አረብ በሚለው የአርብኛ መዝገበ ቃላት ላይ እንደሰፈረው ኢስላም ለሚለው ቃል መነሻ የሚሆነው ሰለመ ( سلم) የሚለው ባለ ሶስት ፊደል ግስ ሲሆን ከዚህም ግስ ሰሊመ የሚል ሌላ ግስ ይሰራል፡፡ ትርጓሜውም ሰላም ሆነ፣ተጥራራ ማለት ነው፡፡ሙሉ ቃሉ ኢስላም ደግሞ እጅ መስጠት ወይም መታዘዝ ማለትነው፡፡ {(2) ኢስላማዊ ትርጓሜውም ( معنى الأصطلاحي ) } هو الأستسلام لله بالتوحيد والأنقياد له والخلوص من الشرك
“ለአላህ እሱን ብቻ ጥርት አድርጎ በማምለክ እጅን መስጠትና በትዕዛዛቱም መመራት ብሎም ከማጀጋራት መጥራት” የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡በአጠቃላይ ቃሉ ለአንዱ ፈጣሪ ትዕዛዝ በመቀናት የሚገኝ ሰላምን ያመላክታል፡፡ይህን ቃል ሙስሊሞች ለእምነታቸው እራሳቸው ፈጥረው የለጠፉት አይደለም፡፡ይልቁንም ከዓለማት ፈጣሪ ለሀይማኖቱ የተሰጠብ ቸኛ የሀይማኖት ስያሜ እንጂ ሌላ አይደልም፡፡በሱረቱል አልዒምራን ምዕራፍ 3/18 አሏህ እንዲህ ሲል ይናገራል፡፡ (1)“አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡በዚሁ ሱራ 84 ኛው ጥቅስ ላይ እንዲህ በማለት ያክላል፡- (2) “ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡” በሱረቱል አሷፍ ምዕራፍ 61 /6 ላይም እንዲህ ይላል፡- (3)“ እርሱ ወደ ኢስላም የሚጠራ ሲኾን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰውም ይበልጥ በደለኛ ማንነው? አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡” (4) በሱረቱል አልማኢዳህ ምዕራፍ 5/2 እንዲህ ይላል “ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡” በእነዚህ አራት ጥቅሶች አሏህ እሱ ራሱ የሀይማኖቱን ስያሜ ራሱ በመረጠው ቃል መሰየሙን በግልጽ ማየት እንችላለን፡፡የዚህ እምነት ተከታዮች “ሙስሊም” ይባላሉ፡፡ትርጓሜውም በግርድፉ “ለፈጣሪ ትዕዛዝ የተቀና” እንደ ማለት ነው፡፡
ለሁለተኛ ግዜ ሊሰመርበት የሚገባው “ ሙስሊም” የሚለውም ቃል ቢሆን ሙስሊሞች ለራሳቸው የለጠፉት ታርጋ እንዳልሆነ ነው፡፡አሏህ በቁርዓኑ ውስጥ በበርካታ ቦታዎች ላይ ቃሉን ይጠቀመዋል፡፡ለአብነት ያህል የሚከተሉትን ማየት በቂ ይሆናል፡፡ (1) በሱረቱል አዙመር 39/11 «የሙስሊሞችም መጀመሪያ እንድኾን ታዘዝኩ፡፡» (2) በሱረቱል አልሀጀር ምዕራፍ 15/1 “እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾን ኖሩ (ብለው) በብዛት ይመኛሉ፡፡” (3) በሱረቱል አልበቀራህ 2/127 «ጌታችን ሆይ! ላንተ ታዛዦችም (ሙስሊሞች) አድርገን፡፡ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች (ሙስሊሞች) ሕዝቦችን (አድርግ)፡፡ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን)፡፡በኛም ላይ ተመለስ፤ አንተጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና፡፡»
አላህ ነቢያትን ሁላ ህዝቦቻቸውን “ኢስላም” ወደ ሚባል እምነት እንዲጠሩ ማለትም “ለፈጣሪ ትዕዛዛት ፈጽሞ ታዛዦች ሁኑ ብላችሁ አስተምሩ” ብሎ እንጂ አላከም፡፡ከመጀመሪያው ነቢይ አደም ጀምሮ እስከ ነቢያት መቀምቀሚያ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሁሉም አረብኛ ተናጋሪዎችም በሌላ አፍ የሰበኩትም ነቢያት፣ ሁሉም ጥሪያቸው ለዓለማት ጌታ ስለመታዘዝ ብቻ ነበር፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ ለክርሰቲያኑ ዓለም መለኮታዊ ወደ ሆነው መጽሀፍ ‘`ብሉይ ኪዳን ”ሶቶ እንበልና ሊደስኩራችን መደጋገፊያዎችን እንቃርም፡፡
(1) ዘሌዋውያን 4/2-3 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው።ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኃጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።“ (2) ዘሌዋውያን 16/14-16
“ነገር ግን ባትሰሙኝ ፥ እነዚህንም ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ ፥ሥርዓቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ ፥ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ነፍሳችሁ ፍርዴን ብትጸየፍ ፥እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ ፍርሃትን፥ ክሳትንም፥ ዓይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፥ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።” (3) መዝሙረ ዳዊት 119/4 “ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ።” ወደ አዲስ-ኪዳን እንዘልቅናም፡- (1) ማቴ 5/19 “እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥ ተሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።” (2) ማቴ 19/17 “እርሱም፦ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።” (3) ዩሀ 5/30 “እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤እንደሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።” እንግዲህ ልባችንን ከፍተን ጥቅሶቹን በጥሞና ካነበብንና ከተረዳናቸው አስቀድመን ከሰጠነው “ኢስላም” ከሚለው ተመጣጣኝ የአረብኛ ቃል ጋር ሲኋኋኑ እናያለን፡፡ያለጥርጥር፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ የተጠቀሱት ነቢያት ባጠቃላይ ለፈጣሪ መታዘዝንና ህገግጋትን መጠበቅን አስተምረዋል በሌላ አባባል ኢስላምን ሰብከዋል ስለሆነም የነቢያት ሁሉ ሀይማኖት ኢስላም ነበር በማለት መደምደም ይቻላል፡፡
“ክርስትና” እና “ክርስቲያን” የሚለው ስምና ስያሜስ ምንጫቸው ከየት ይሆን?በሚቀጥለው ጽኁፍ እስክንገናኝ በዝች ትንሽ ጽሁፌ ላይ አክላችሁ ወይም እሷኑ እያላመጣችሁ ጠብቁኝ፡፡في امان الله!!!